Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News2  የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
News2

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

Ethioreview newsEthioreview news—January 14, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ::

16ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

  1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ለሁለተኛው ምዕራፍ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገ 107,174,255.00 (አንድ መቶ ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰባ አራት ሺ ሁለት መቶ አምሳ አምስት) የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት ላይ ነው፡፡

ብድሩም የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት እና የመሬት ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ገቢና አኗኗር ለማሻሻል መንግስት የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ፤ ወለድ የማይታሰብበት እና በ40 ዓመታት ተከፍሎ የሚያልቅ መሆኑ ከአገሪቱ የብድር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ምክር ቤቱ ስምምነቱን በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

  1. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ከየካቲት 2012 ጀምሮ ስራ ላይ በዋለው የኤክሳስ ታክስ አዋጅ ያስገኘውን ጠቀሜታ እንዲሁም የታዩትን ክፍተቶች በመገምገም በአንዳንድ ምርቶች ላይ የተጣለውን የማስከፈያ ምጣኔ ማስተካከል ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ የአዋጁ ማሻሻያ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
More stories

ጓደኛቸውን ገድለው  ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው የተሰወሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

May 21, 2024

የብሪክስ ፕላስ የመረጃና እና የባህል ሚዲያ ማዕከል ተመሰረተ

October 15, 2024

” የሎንግ ኦነግ ሸኔን መክዳት ከዜና በላይ ነው” – የሸኔ የሎጂስቲክ መረጃ መንግስት እጅ ገባ

February 18, 2024

“የቴህራን የአየር ክልል በኛ ቁጥጥር ስር ሆኗል” እስራኤል

June 16, 2025

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

  1. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡

የኢንስቲትዩቱን ተግባርና ኃላፊነት ግልጽ ማድረግ፣ እያከናወነ ያለውን የምርምር ምህዳር በሌሎች የጤና ምርምር ስራዎች አስፍቶ እንዲሰራ ለማስቻል፣ ቅንጅትን የሚያጎለብት፣ ብክነትን የሚቀንስና ውጤታማነትን የሚያበረታታ አደረጃጀት እንዲኖረው የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ተወያይቶ ግብአቶችን በማከል በሙሉ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

  1. ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው የኢትዮጵያ የደም እና ቲሹ ባንክ አገልግሎትን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡

ቀደም ሲል ብሄራዊ የደም ባንክ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በማስፋት የደም ተዋፅኦዎችን፣ ሪኤጀንቶችን እና የደም ውሃ በአገር ውስጥ ማምረት እንዲሁም የቲሹ (ህብረ-ህዋስ) ንቅለ ተከላ ህክምና አገልግሎትን የመደገፍ፣ የህብረ-ህዋስ ለጋሾችን የማስተባበር እና ተያያዥ ተግባራትን እንዲያከናውን የሚያስችል ስልጣን ያለው ተቋም በማስፈለጉ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ተወያይቶ ግብአቶችን በማከል በሙሉ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

  1. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ ደንብ ነው፡፡

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን አስቀድሞ የመተንበይ፣ የመከላከል እና ምላሽ የመስጠት ውጤታማ ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤ የሀገሪቱ የጤና ላቦራቶሪ ዘርፍ ለህብረተሰብ ጤና ክብካቤ፣ ህክምና እንዲሁም ለስርዓተ ምግብ ምርምሮች ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ማስቻል የሚገባ በመሆኑ፤ የማህበረሰብ ጤና ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን አፈፃፀም በጥልቀት የሚከታተልና የሚገመግም ተቋም በማስፈለጉ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ተወያይቶ ግብአቶችን በማከል በሙሉ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

  1. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለስልጣንን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡

የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የህክምና መሣሪያ፣ የባህላዊ መድኃኒት፣ የትምባሆ እና ተያያዥ ምርቶችን አመራረት፣ ዝውውር፣ አቅርቦት እና አጠቃቀምን በሚመለከት የቁጥጥር እና ክትትል ስርዓት መዘርጋት፣ የቁጥጥር ተግባሩን ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ ላቦራቶሪዎችን የማደራጀት፣ ህገ ወጥ ተግባራት ሲፈጸሙም ተገቢውን እርምጃ የሚወስድ እንደሁም ቁጥጥር የሚደረግባቸው ምርቶች አመራረትና አጠቃቀም በአለም አቀፍ ስታንዳርዶች መሰረት መከናወናቸውን የሚያረጋግጥና የሚያስፈጽም ስልጣን እና አደረጃጀት ባለስልጣኑ እንዲኖረው የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ተወያይቶ ግብአቶችን በማከል በሙሉ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

  1. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው ከቱርክ ሪፐብሊክ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስታት ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ የመስጠት እና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ለማድረግ በተፈረሙ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡

በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት የሁለትዮሽ ስምምነቶቹ በወንጀል ጉዳይ የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ በመስጠት ረገድ ለሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር የሕግ ማዕቀፍን የሚፈጥሩ ከመሆኑም በላይ በተዋዋይ ሃገራት የህግ የበላይነት መረጋገጥ ፋይዳቸው የጎላ ነው፡፡

በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትህ ትብብር ስምምነቶቹም በተደራጁ፣ ድንበር ዘለል በሆኑ እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት ግዛቶች ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን አስመልክቶ በሚከናወኑ የምርመራ፣ የክስና የፍርድ ሂደቶች መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ለመለዋወጥ እንዲሁም የወንጀል ፍሬዎችን ዝውውር በመግታት ረገድ ፋይዳቸው የላቀ የትብብር የሕግ ማዕቀፎች በመሆናቸው የሁለትዮሽ ስምምነቶቹ ለምክር ቤቱ ቀርበዋል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረቡት የሁለትዮሽ ስምምነቶች ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ይጸድቁ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

OBN

home
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ቻይና ለኢትዮጵያ 30 ሚሊዮን ዩዋን የእዳ ስረዛ አደረገች
ታከለ ኡማን ጨምሮ አራት ሚኒስትሮች ከሃላፊነታቸው ተነሱ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2