Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News2  ኦሮሚያ በወረዳዎች፣ከተሞችና ዞኖች ስር ነቀል ለውጥ አደረገ
News2

ኦሮሚያ በወረዳዎች፣ከተሞችና ዞኖች ስር ነቀል ለውጥ አደረገ

Ethioreview newsEthioreview news—February 27, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ህዝብ ኑሮና ተጠቃሚነት በመሰረታዊነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ፈጣን፣ ዘላቂና ሰፊ መሰረት ያለው ልማት በማስመዝገብ የተለያዩ የልማት ስትራጂዎችን በማመንጨት ስትራቴጂዎቹን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አደረጃጀቶችንና አሰራሮችን በመዘርጋት ስሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ባለፉት አመታት ውስጥ የህዝባችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የከተማ ልማት ለማካሄድ በከተመዎቹ የእድገት ደረጃ መሰረት በርካታ ከተሞችን በመመስረት ሰፋፊ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም አሁን በደረስንበት የእድገት ደረጃ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ በመሆን ህዝባችንና ክልላችን የሚመጥኑ ከተሞችን ለመፍጠር እንዲሁም ህገ ወጥነትን በመቆጣጠር በከተሞች ውስጥ እየታዩ ያሉ ውስብስብ ሁኔታዎችን ለማስተዳደር ያለውን አደረጃጀት እየፈተሹና እያሻሻሉ መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡ 
በመሆኑም ከተሞቹ ያላቸውን መልካም እድል ወደ አንድ በማምጣት አብሮ እንዲለሙና የጋራ ዓላማ እንዲኖራቸው፣ በአንድ ፕላን በመተዳር ሁለንተናዊ እድገት እንዲኖራቸው፣ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት ኖሯቸው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ሙያን ለማስፋፋት፣ የብዝነስ አስተሳሰብን ለማዳበር እና የአገልግሎትን ለማሻሻል የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ሁለትና ከዛ በላይ ከተሞችን አንድ ላይ ለማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ለአስተዳደር በሚያመች መንገድ የከተሞቹ አደረጃጀት እንደሚከተለው ተከናውኗል፡፡
1.  ቢሾፍ ከተማ፡ የቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እንዲሁም የመዘጋጃ ቤት ከተሞች ሂዲ፣ ኡዴ ደንካካ እና ድሬ በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ10 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
2.  ሻሸመኔ ከተማ፡ የሻሸመኔ ከተማ እና የብሻን ጉራቻ ከተማ በመቀላቀል በ4 ክ/ከተሞች እና በ12 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
3.  አዳማ ከተማ፡ የአዳማ ከተማ እና የወንጂ ከተማን በመቀላቀል በ6 ክ/ከተሞች እና በ19 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
4.  ሮቤ ከተማ፡ የሮቤ ከተማ እና የጎባ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
5.  ማያ ከተማ፡ የሀረማያ ከተማ፣ የአወዳይ ከተማ እና የአዴሌ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
6.  ባቱ ከተማ፡ የባቱ ከተማ እና የአዳሚ ቱሉ ከተማን በመቀላቀል በ7 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የመልማት እድል ያላቸው ከተሞቻን በተሟላ መንገድ በመጠቀም ሁለንተናዊ የሆነ ልማት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉትን ከተሞች ወረዳዎችን ልማት እንዲያፋጥኑ ለማድረግና የአመራን ትኩረት እንዲያገኙ ለማስቻል የሚከተሉት ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግስት እንዲሆን ተወስኗል፡፡
1.  መቱ ከተማ
2.  አጋሮ ከተማ
3.  ቡሌ ሆራ ከተማ
4.  ነጆ ከተማ
5.  ሰንዳፋ በኬ ከተማ
6.  ሸኖ ከተማ
7.  ሞያሌ ከተማ
8.  ዶዶላ ከተማ
9.  ሻክሶ ከተማ

በተመሳሳይ መልኩ የከተሞች የማስፈፀም አቅማቸው ተሻሽለው ፈጣንና ከእንግልት የፀዳ አገልግሎት በሙሉ አቅም እንዲሰጥና ሁሉአቀፍ  የሆነ ልማት  እንዲመዘገብ ለማድረግ  እንደ አጠቃላይ  እየተደረገ ያለውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣዎን የከተሞችን እድገት  መሠረት በማድረግ የከተሞችን ደረጃ እንደሚከተለው እንዲሻሻል ተወስኗል።

1. አዳማ፣ ሻሻመኔና ቢሾፍቱ ከተሞች፡- የሬጂዮ-ፖሊስ ከተማ
2. የሮቤ ከተማና የማያ ከተማ፡- ዋና ከተማ
3. የመቱ፣ አጋሮ፣ ቡሌ ሆራ፣ ነጆ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ሞያሌና ሻክሶ ከተማ፣- ወደ ከፍተኛ ከተማነት እንዲያድጉ ተወስኗል።

በሌላ መልኩ ለረጂም ጊዜ ስነሳ የቆየውን የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ፈጣን የሆነ የኢኮኖሚያና ማህበራዊ ለማስመዝገብ፣ በድንበር አካባ ያለውን ህገ ወጥነትን ለመቅረፍ፣ በድንበር አካባ ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚከሰተውን የሰላም ሁኔታን ለመፍታት እንዲሁም ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለማቅረብ ውጤታማ የሆነ አደረጃጃትና አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የምስራቅ ቦረና ዞን አዲስ ዞን ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል፡፡

More stories

ጓደኛቸውን ገድለው  ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው የተሰወሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

May 21, 2024

የብሪክስ ፕላስ የመረጃና እና የባህል ሚዲያ ማዕከል ተመሰረተ

October 15, 2024

” የሎንግ ኦነግ ሸኔን መክዳት ከዜና በላይ ነው” – የሸኔ የሎጂስቲክ መረጃ መንግስት እጅ ገባ

February 18, 2024

“የቴህራን የአየር ክልል በኛ ቁጥጥር ስር ሆኗል” እስራኤል

June 16, 2025

በአዲስ መልክ 21ኛ ዞን ሆኖ የተደራጀው የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና ከተማው ነጌሌ ቦረና ሆኖ፡-
•  ከቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ፣ ሞያሌ ከተማ፣ ጉቺ ወረዳ እና ዋችሌ ወረዳ፣
•  ከጉጂ ዞን ሊበን ወረዳ፣ ጉሚ ኤልደሎ ወረዳ፣ ነጌሌ ቦረና ከተማ፣
•  እንዲሁም ከባሌ ዞን መደወላቡ ወረዳ፣ ኦቦርሶ ወረዳ እና ሀረና ቡሉቅ ወረዳ በመጨመር እንደ ዞን 10 ወረዳዎችን በመያዝ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡
በአዲሱ አደረጃጀት የምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የጉጆ ዞን ዋና ከተማ አዶላ ሬዴ ሆኖ የቦረና ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ያቤሎ ከተማ እንዲሆን ተወስኗል

በልላ በኩል ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሆነ አደረጃጀት ለመፍጠር የመሬት ስፋት፣ የፀጥታ ችግር የመልካም አስተዳደር ጥያቄና ፈጣን ልማት ጥያቄን ለማረጋገጥ የመደ ወላቡ ወረዳ የነበረ  በሁለት ቦታ ማለትም የመደ ወላቡ ወረዳና ኦቦርሶ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅና የጭናክሰን ወረዳ የነበረ በሁለት ወረዳ ማለትም የጭናክሰን ወረዳና የመከኒሳ ኦሮሞ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል።,

home
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
እስክንድር ነጋ ተፈታ፤ “ትግሉ ይቀጥላል” ብሏል
African media: Well deserved, real time concern
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2