የአፍሪካ አገራት ወደ ብሪክስ የመጉረፍ ስሜት ይፋ ሲሆን የቡድን 20 አባል ሀገራት ሃምሳ አምስት አባል አገራትን ያቀፈውን የአፍሪካ ህብረትን ቋሚ አባል አድርጎ መቀበሉ ይፋ አደረገ። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኒው ደልሂ እየተካሄደ ባለው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ህብረት ቡድኑን መቀላቀሉን ገልጸዋል። ውሳኔው ለአፍሪካ የጸጥታው ምክር ቤት አባልነት ምልክት ሆኖ ተወስዷል።
የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ቋሚ አባል እንዲሆን የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ሁሉም የአባል ሀገራቱ መሪዎች እንደተስማሙበት ተመልክቷል። በኢንደስትሪ የበለጸጉና ከአዳጊ አገራት የላቀ የምጣኔ ኃብት ዕመርታ ያስመዘገቡት አገራት መሰባሰቢያ የሆነው ህብረቱ አፍሪካ በአንድ ድምጽ መወከሏን በሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ በኩል ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረትን ሊቀመንበር የሆኑትን የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ በቡድን 20 ለህብረቱ የተዘጋጀውን መቀመጫ እንዲይዙ ተጋብዘው ስፋራቸውን ወስደዋል።
ደቡብ አፍሪቃ የተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ኢትዮጵያን ጨመሮ ስድስት አገራትን መቀበሉን ተከትሎ የቡድን ሃያ አገራት አፍሪኪአን በአባልነት ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውንና ግብዣ ማቅረባቸውን የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ አስታውቀው እንደነበር ይታወሳል።
ቢቢሲ ይህን ዜና አስታኮ የሚከተለውን ዘገባ አካቷል። በቡድን 20 አገራት ጉባኤ ላይ ከሚነሱ ነጥቦች አንዱ የዩክሬን ጉዳይ የነበረ ሲሆን፣ ቢቢሲ ይፀድቃሉ ከተባሉ ሰነዶች መካከል የተመለከተው ሰነድ እንደሚጠቁመው ስለ ዩክሬን እስካሁን የተጠቀሰ ነገር የለም። ሰነዱ የባንክ ዘርፍን ማሻሻልና ክሪፕቶከረንሲን መቆጣጠር ጨምሮ ሌሎችም ነጥቦችን ያካተተ ነው።
በሌላ በኩል የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሕንድን ‘ባሐራት’ በሚል ስም መጥራታቸው ውዝግብ ፈጥሯል። አገሪቷ ስሟን በይፋ ስለመቀየሯ እስካሁን የተባለ ነገር ግን የለም።
ሌላው በጉባኤው የሚነሳው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ነው። ታዳጊ አገራት የበለጠ ተጎጂ ስለሚሆኑ ካደጉ አገራት አንዳች መተማመኛ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ሲገለጽ ቆይቷል። የመጀመሪያው የቡድኑ ውይይት አንድ ምድር ወይም ‘One Earth’ የሚባል ሲሆን የአካባቢ ጉዳይን የተመለከተ ይሆናል።
ታዳጊ አጋራት በሕንድ ተወክለው በሚካሄደው ውይይት ሃብታም አገራት የካርበን ልቀትን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት በገንዘብ፣ ቴክኖሎጂና መሠረተ ልማት እንዲደግፉ እንደሚጠይቅ ተገልጿል።
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






