በ2012 ከነበሩት 46 ሺህ በላይ መምህራን አሁን ላይ ከ14ሺህ በላይ የሚሆኑት ከስራ ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የትምህርት ቢሮው ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ግዑሽ በጦርነት ሳቢያ መምህራን ሞተዋል። ራሳቸውን ለማኖር ተሰደዋል። የኑሮ መመሳቀል ደርሶባቸዋል ብለዋል።
በጦርነቱ ምክንያት የተሰደዱ ፣ የተፈናቀሉ ፣ አካላቸው የጎደለ እንዲሁም የሞቱ መምህራን መኖራቸውን አንስተው፤ ከ 2 ዓመት በላይ ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ህይወታቸውን ለማትረፍ የተለያዩ ስራዎች ውስጥ የተሰማሩ መኖራቸውንም ሃላፊውን ጠቅሶ የዘገበው ኢትዮኤፍ ኤም ነው።ሃላፊው የተቀሩት መምህራንም ቢሆኑ በጦርነቱ ምክንያት ብዙ የስነልቦና ጉዳትን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ችግር እንደደረሰባቸው አመልክተዋል።
በክልሉ የነበረው ጦርነት በትምህርት ዙሪያ ሶስት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷልም ነው ያሉት ሃላፊው። የት/ቤቶች መቃጠል ፣መፍረስ፣ መውደም አንደኛው ሲሆን ፤ በሰው ሃይሉ ላይ ያደረሰው ጉዳት ቀጥሎ የሚነሳ ጉዳይ ነው።
በሶስተኛነት የተነሳው ጉዳይ ደግሞ ስርዓተ ትምህርቱ ሲሆን ብዙ ተማሪዎች በእድሜያቸው ልክ ማግኘት ያለባቸውን ትምህርት ባለማግኘታቸው አሁን ላይ 5ኛ ክፍል እና ከዛ በላይ መሆን የነበረባቸው ልጆች ገና የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በ2012 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ቢወስዱ ምናልባት አሁን ላይ የ4ኛ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሚሆኑ ከ9ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ4 አመታት በኋላ ባለፈው ሳምንት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰዳቸው የሚታወስ ነው።
በሌላ ዜና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ቁመና እንደሌለ ተገልጿል። ክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ በተጎዳበትና ዜጎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ በርካታ ቦታዎች በወራሪ ሀይሎች በተያዙበት ሁኔታ፣ ምርጫ ማካሄድ የማይታሰብ ነው ሲሉ መናገራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል። ዜናው “ወራሪ” ያላቸውን አላብራራም።
ክልሉን እየመራ የሚገኘዉ ግዚያዊ አስተዳደር ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁነት የለዉም የሚሉት የዉድብ ናፅነት ትግራይ ዉናት ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገቦ፣ አስተዳደሩ ወደ ምርጫ ገብቶ ለዉጥ እንዲመጣ ፍላጎትም ዝግጁነትም የለዉም ብለዋል።
በትግራይ ክልል በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ጥሩ ቅርርብ መኖሩን የሚናገሩት የዓረና ሉአላዊነትና ዲሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ አንዶም ገ/ስላሴ ፣ በሳልሳይ ወያኔ ትግራይ፣ውድብ ናፅነት ትግራይ እና ባይቶና አባይ ትግራይ ጥምረት ፈጥረዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፣ አረናም ጥሩ መቀራረብ ስላለዉ ምን አልባት መልካም ሁኔታ ተፈጥሮ ምርጫ ከተካሄደ በጋራ ለመወዳደር ዉይይት ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ምርጫ ቦርድ ባለፈዉ ዓመት በ2016 ምርጫ ከሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች አንደኛዉ የትግራይ ክልል መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም። የትግራይ ክልልን ጨምሮ የስድስተኛው ዙር ቀሪ ምርጫዎችን በተለያዩ ጊዜያት ለማከናወን ዝርዝር ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳቀረበም አስታውቋል፡፡
- ታ94 በመቶ ታራሚዎች ከ5 አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሌላ ወንጀል በድጋሚ ይታሰራሉቪኦኢ ዜና – በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ ሥርዓት ውስጥ ወንጀል ፈጽመው የታረሙ ግለሰቦች በድጋሚ ወደ ወንጀል ድርጊት የመመለሳቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ… Read more: ታ94 በመቶ ታራሚዎች ከ5 አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሌላ ወንጀል በድጋሚ ይታሰራሉ
- በወጣቶች ህይወት የሚቆምረው ህገ ወጡ ህወሓትቪኦኢ ዜና ነሐሴ – የህገ ወጡ ህወሓት የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳና እና የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ ለትግራይ ክልል ወጣቶች ስደት፣ እስር፣ ጭንቀትና ተስፋ መቁረጥ… Read more: በወጣቶች ህይወት የሚቆምረው ህገ ወጡ ህወሓት
- ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ወደ አፍሪካ ኃያልነት እየተሸጋገረች መሆኗን የህንዱ ፈርስት ፖስት ገለጸቪኦኢ ዜና – ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የመጪው ዘመን የአፍሪካ ኃያል ሀገር ወደመሆን እየተሸጋገረች መሆኗን ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ፈርስት… Read more: ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ወደ አፍሪካ ኃያልነት እየተሸጋገረች መሆኗን የህንዱ ፈርስት ፖስት ገለጸ
- «የዋስትና መብታቸው ይውረድና ጉዳያቸውን በማረሚያ ሆነው ይከታተሉ» ዐቃቢ ሕግ“ወደ ሚድያ የመጣነው በሚድያ የጠፋ ስማችንን ለማደስ ነው” ተከሳሾች “የዋስትና መብታቸው ይውረድና ጉዳያቸውን በማረሚያ ሆነው ይከታተሉ ” ዐቃቢ ሕግ በፊንቴክ የማጭበርበር ወንጀል… Read more: «የዋስትና መብታቸው ይውረድና ጉዳያቸውን በማረሚያ ሆነው ይከታተሉ» ዐቃቢ ሕግ
- መንግሥት በሙስና፣ በሌብነትና በኢኮኖሚ አሻጥር ላይ ሰፊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀአዲስ አበባ | VOE News | የፌዴራል መንግሥት በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ የተንቀሳቀሱ እና በሕዝብ ሀብት ላይ ሙስና፣ ሌብነትና… Read more: መንግሥት በሙስና፣ በሌብነትና በኢኮኖሚ አሻጥር ላይ ሰፊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ






