” በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል ” ሲል ቀይ መስቀል በድርጊቱ ግራ መጋባቱን ጠቅሶ ዜናውን ይፋ አድርጓል።
ቀይ መስቀል ብቻ ሳይሆን ዜናውን የሰሙ ከየአቅጣጫው “ምን የሚሉት ፖለቲካ ነው? ዓላማውስ ምንድን ነው? ህዝብ በተለይም ወላድ እናቶች በወሊድ እንዳይሞቱ በፍጥነት ህክምና ስፍራ ለማድረስ የሚያገለግል ተሽከርካሪ ማንደድ ለየትኛው ህዝብ የሚደረግ ትግል ነው? እስከመቼ በዚህ ዓይነት ድንቁርና ተቀጥላላችሁ?” በሚሉና እጅግ ብስጭትን በሚገልጹ ቃላቶች ተቃውሞ ተሰንዝሯል።
እየተደበቁና እያደቡ ማህበራዊ መገልገያዎችን ማውደም ልዩ ምልክቱ አድርጎ በየአቅጣጫው የሚካሄደው የትጥቅ ትግል ምግባር የጎደለው፣ ስርዓት የነጠፈበት፣ ዓላማ ቢስ፣ ለማንና ለምን እደሚታገል የማይለይ፣ የሚምልበትን ህዝብ መልሶ የሚበላና የሚጎዳ፣… እንደሆነ የሚያሳዩ በርካታ አስነዋሪ ተግብራት እየታዩበት ነው።
ነጹሃን ከመግደል፣ ከማፈናቀል፣ መኖሪያቸውን ከማንደድና ከማፈናቀል በዘለለ ይህን አስነዋሪ ድርጊት እንደ ቅዱስ የትግል አማራጭ አድርገው የሚያቀርቡ የንቅናቄና ነጻ አውጪ መሪዎችና አክቲቪስቶ በየቀኑ መፍላታቸው ” አገርቱን ለመረከብ በመናበብ እየተረባረቡ የሚሰሩት ሃይሎች በታሰቡ ቁጥር ተስፋ የሚያስቆጥር ነው” ሲሉ በሚሰሙትና በሚያዩት ግራ የተጋቡ እየተናገሩ ነው።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የምዕራብ ወለጋ ዞን ሀሩ ወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ንብረት የሆነና ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምበት ታርጋ ቁጥሩ ET05-01939 አምቡላንስ ተሽከርካሪ በዛሬው ዕለት ማለትም ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት በሀሩ ወረዳ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ በቆመበት በታጣቂ ኃይሎች ተቃጥሏል፡፡
ማኅበሩ መሰል ድርጊቶች ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶች የሚጥሱና በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ የሚያስጠይቁ መሆናቸውን ገልጿል።
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎቹ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች በሰብዓዊ አገልግሎቱ ላይ እንቅፋት እየፈጠሩበት እንደሚገኙ ማህበሩ አመልክቷል።
በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል ሲል አስገዝቧል።
ማህበሩ ” አሁንም በድጋሚ በመላው አገራችን በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ሠራተኞችና በጎፈቃደኞች እንዲሁም አምቡላንሶችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ መሰል ድርጊቶችን የሚፈፅሙ አካላት ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን ” ብሏል።
ዜናው ከቲክቫህ፣ ከማህበራዊ ገጾችና በዚያው ላይ ከተገኙ አስተአየቶች የተሰባሰበ ነው
- የታሪካዊው ምክክር ፈተና እና ዕድል፤ አገራዊ ውህደት ወይስ የተራራቁ መስመሮች ስምምነት?VOE OPINION | ADDIS ABABA | July 31, 2026 – በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ… Read more: የታሪካዊው ምክክር ፈተና እና ዕድል፤ አገራዊ ውህደት ወይስ የተራራቁ መስመሮች ስምምነት?
- የትግራይ የሰላም ኃይሎች አዛዥ የእነ ሞኖጆሪኖን ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስታወቁቪኦኢ ዜና | Addis Ababa | July 30, 2026 ራሱን የትግራይ የሰላም ኃይሎች ብሎ የሚጠራው ቡድን ትህነግን ከመቀሌ በማስወጣት ከተማዋን ለመቆጣጠር… Read more: የትግራይ የሰላም ኃይሎች አዛዥ የእነ ሞኖጆሪኖን ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስታወቁ
- Ethiopian Minister Says Egypt Should Pay for Nile Water UseVOE | Addis Ababa | July 30, 2026 – Ethiopia’s Minister of Water and Energy, Habtamu Itefa, has argued that Egypt… Read more: Ethiopian Minister Says Egypt Should Pay for Nile Water Use
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘBy VOE News ADDIS ABABA – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 የሥራ ዘመን ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ (9.1 ቢሊዮን ዶላር) ገቢ… Read more: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ
- Egypt’s Losing Game over the GERD Has Never Been About Hydro-Technical EngineeringVOE NEWS | ADDIS ABABA | July 29, 2026 Egyptian politicians have repeated the same familiar refrain for years that Ethiopia is… Read more: Egypt’s Losing Game over the GERD Has Never Been About Hydro-Technical Engineering






