Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Monday 18 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ባለሀብቶች ብድር ከመስጠት አንስቶ ሌሎችም ድጋፎች እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

    February 9, 20220

    ሹፌሮችን በመግደል ተሽከርካሪ ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች የሞት ቅጣት ተወሰነባቸው

    October 21, 20240

    የአማራ ክልል ከትግራይ ጋር ሁሉንም ጉዳይ በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመጨረስ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

    March 31, 20230

    Sudan official: ‘Mediation between Khartoum and Addis Ababa faces obstacles’

    February 14, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    መላው አማራ ከነገ ጀምሮ ለህልውና ዘመቻ እንዲነሳ ክተት ተጠራ

    July 25, 20210

    የጆ.ባይደን አስተዳደር የሰላም አማራጭ ንግግሩን ቀድሞ የትህነግን ፍላጎት አቋም አድርጎ አቀረበ

    November 1, 20220

    በሽረ አዲስ ተስፋ፤ ሕዝብ በነጻነት ስለቀጣዩ ዕጣው አየመከረ ነው

    December 26, 20220

    እውነትን ለሥልጣን መናገር ፣ ሳማንታ ፖወር ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

    March 1, 20210

    በአዲስ አበባ ከ27ሺህ በላይ ወጣቶች ተደራጅተው ከተማዋን እየጠበቁ ነው

    November 11, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  OPINION  የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም – መልዕክት “ለመንፈሳዊው መንጋ” መሪ ዘመድኩን በቀለ!
OPINION

የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም – መልዕክት “ለመንፈሳዊው መንጋ” መሪ ዘመድኩን በቀለ!

Ethioreview newsEthioreview news—February 10, 20230
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጃዋር መሐመድ “የኦሮሞ ፕሮቴስት” ብሎ የጀመረ ሰሞን ብዙ የፌስቡክ ተከታታይ አልነበረውም። ወዲያው አገር ቤት ከኦህዴድ ጋር በነበረው ግንኙነት የተቃውሞ ሰልፎችንና የፖሊስ ግፎችን የሚያሳዩ ፎቶዎችን መለጠፍ ሲጀምር የተከታታዩ መብዛት ጀመረ።ዝግጅቱም፣ ትምህርቱም፣ ሥራውም፣ በሚዲያ ዙሪያ ስለነበር ሚዲያን እንዴት እንደሚቆጣጠርና የሕዝቡን ቀልብ እንዴት እንደሚስብ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። በመሆኑም ከማኅበራዊ ሚዲያ እስከ ዋንኛ (mainstream) ያለውን በቀላሉ ተቆጣጠረው። ለመረጃ፣ ለዘገባ፣ ለዜና፣ … እንደ ምንጭ የሚጠቀስ ሆነ። ትልልቅ የሚባሉት የውጪዎቹ የሚዲያ አውታሮች እሱን ሳያናግሩ ዜና መሥራት አልታያቸው አላቸው። በፍጥነት ወጣ፣ ተመነደገ፣ ከፍ አለ! የዚያኑ ልክ እሱም እያበጠ መጣ።

ዕብጠቱ ገና አፍላ በነበረበት ጊዜ ባደባባይ የዕብሪት ንግግር ለጠፈ። አሁን በማላስታውሰው አንድ ከተማ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ተማሪዎች ወጥተው ነበር። ትህነግ አሰልጥኖ ያሰማራቸው የአጋዚ ፖሊሶች ለደረታቸው ተኩሰው የተወሰኑትን ይገድላሉ። የሞቱትን ልጆች ፎቶ እንደተላከለት ጃዋር ወዲያው በፌስቡክ ገጹ ለጠፈው። ፎቶው መሬት ላይ የተዘረሩ በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶች በደማቸው ተነክረው የሚያሳይ እጅግ ዘግናኝ ነበር። ከፎቶዎቹ ጋር  እንዲህ በማለት በእንግሊዝኛ ለጠፈ፤ “ጨምራችሁ ግደሉ ሒሳቡ በእኛ ነው”። ይህንን ሲል እርሱ በሞቀ ቤቱ በአሜሪካ ሜነሶታ ጠቅላይ ግዛት ደኅንነቱ ተጠብቆ እየኖረ ነበር።

ዕብሪተኛው በዚሁ ቀጥሎ አገር ቤት ከገባ በኋላ “ሁለት መንግሥት ነው ያለው” ብሎ እስከመናገርና ራሱን እንደ አገር መሪ እስከ መቁጠር ደርሶ ነበር። ሌላም ብዙ መጥቀስ ይቻላል። ወደ አገር ሲገባ ከነበረው ወደ አንድ ቢሊዮን የሚጠጋ ጥሬ ብር በተጨማሪ ሌሎች በርካታ የገቢ ምንጮች ነበሩት። ይህም የእብሪት ፊኛውን ለመወጠር አዎንታዊ አስተዋጽዖ ያደረገ ነበር።

የ21ኛው ክፍለ ዘመን አሕመድ ግራኝ ነኝ ሲል የነበረው ጃዋር አሁን የት ነው? ገና በወጣትነቱ የተጠናወተውን በሽታ እያስታመመ፤ አመጋገቡን እየተቆጣጠረ፤ ደግ ደጉን እያወራ ተራራ የሚወጣ (ኪሊማንጃሮን ማለቴ ነው) ኃላፊነቱን የተገነዘበና በትጋት የዜግነት ድርሻውን የሚወጣ “መልካም ወጣት”፣ ጥሩ የሕግ ታራሚ ሆኗል።

More stories

ይብላኝ_ለእናንተ! ዓሳ ስለውኃ ያለው አረዳድ ከኮረት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን

January 31, 2022

መለስ ከመቃብር ይጮሃሉ … ” በሁዋላ ላይ አሰብን ከኢትዮጵያ ከመውሰድ ይልቅ ከኤርትራ ላይ መውሰድ ስለሚቀል ነው”

June 1, 2022

አንድ ሃቅ! – ጦርነት የሚያቀጣጥሉ ለዋጋ ንረት ተቆርቋሪዎች

January 9, 2025

የታሪክ ወዝ: ጎልያድና ታሪኩ በሳይንሳዊ መላምት ዐይን

July 31, 2024

ዘመድኩን ይህንን ሁሉ እንደ መግቢያ የጻፍኩት አንተ ራስህን ልክ እንደ ጃዋር ጊዜ “የኦሮሞ ፕሮቴስት” የሰሞኑ “የኦርቶዶክስ ንቅናቄ” ተብሎ በተሰየመልህ አጀንዳ ራስህን መሪ እያደረግህ በመምጣትህን በማየቴ ነው። በነገራችን ላይ ስሜን ያልነገርኩህ ፈርቼ ወይም በሃሰት መረጃ በድብቅ አንተን ለማጥቃት ሳይሆን ያንተን ያህል ባይሆንም የተወሰነ የሚያውቀኝ ሰው ስላለ ነገር ላለማባባስ ነው። እኔና አንተ ግን በደንብ ነው የምንተዋወቀው። አሁንም በአጻጻፌ በደንብ ልታውቀኝ ትችላለህ። በበርካታ ጉዳዮች ላይ ብዙ ተከራክረናል፤ “ተው ተጠንቀቅ፤ እንዳትጠለፍ” እያልኩ መክሬሃለሁ፣ አስመስክሬሃለሁ።

በቤተክርስቲያናችን የደረሰውን አስከፊና አንገት አስደፊ ነገር የእኔን እና የበርካታ ተዋህዶ ልጆችን ቅስም የሰበረ ነው። እንዳንተ እየወጣን አዛኝ ተቆርቋሪ መስለን አጀንዳ ፈጻሚ ባንሆንም መከራና ስቃያችንን ለሚያይ አምላክ በየሰዓቱ እንቃትታለን። አንተ ግን ለተዋህዶ ቤታችን የተጨነቅህ መስለህ የምትጽፋቸው እጅግ ዘግናኝ ልጥፎች እጅግ የዘቀጡ ናቸው።

በቴሌግራም ብዙ ተከታዮች አሉህ። ሰሞኑን በቲክቶክ ደግሞ ዝነኛ ሆነሃል፤ ተከታዮችህ እና የቀጥታ ሥርጭቶችህ ተመልካች ቁጥር በሚያስገርም ሁኔታ በፍጥነት አድጓል። እንዲያውም በቲክቶክ መንደር የአንደኛነትን ደረጃ መጎናጸፍህን ራስህ በቴሌግራምህ ላይ ለጥፈሃል። እንኳን ለዚህ በቃህ። ግን አትርሳ የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም።

የመረጃ ድርቀት ስላለብህና ከስድብ በስተቀር ከዕውቀትም የጸዳህ ስለሆነ አንዲት ነገር ልጥቀስልህ። የዛሬ 11 ዓመት አካባቢ በመጋቢት ወር ውስጥ (እኤአ 2012) አንድ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ የዩጋንዳ አማጺ ቡድን መሪ የሆነው ጆሴፍ ኮኒ እንዴት ሕጻናትን ለውትድርና መልምሎ ግፍ እንደሚሰራባቸው የሚያሳይ ቪዲዮ ለቀቀ። በሁለት ቀናት ውስጥ 30 ሚሊዮን ተመልካች አገኘ። ይህ በዕቅድ የተለቀቀው ቪዲዮ በኋላ ለእንዴት ዓይነት መሰሪ ተግባር ታቅዶ ለዕይታ እንደቀረበና የተሠራውም ለህጻናቱ ታስቦ ሳይሆን ወረራ ለመፈጸም እንደሆነ በኋላ የታወቀ ሆኗል። አትርሳ የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም።                

በማኅበራዊ ድረገጾችህ ያለማቋረጥ ትጽፋለህ፤ ስትጀምር በተለመደው ኦርቶዶክሳዊ ቡራኬ ነው፤ ከቡራኬው በኋላ ግን በአማርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያሉት ለስድብህ ስለማይበቁህ የራስህን ጨምረህ እጅግ ጸያፍ ስድብ ትሳደባለህ። ተከታዮችህን በመንፈሳዊ ትምህርት እና ክርስቶሳዊ በሆነ ትህትና ከማነጽ ይልቅ ስድብ ስትግታቸው ትውላለህ። አስበኸዋል አንድ ቀን ልጆችህ አድገው ምን ስታደርግ እንደነበር ቢረዱ ምን እንደሚሉህ? ባለቤትህስ? የሚያውቁህ ዘመዶችህስ? በዚህ ላይ ይህንን ስድብህን ለመትፋት “አገልግሎቴን በገንዘብ ደግፉ” እያልህ ሳንቲም ትለቃቅማለህ። ጊዜ ያልፋል፤ ኢንተርኔት የያዘው ግን አያልፍም። ለቤተሰብህ የውርደት ስንቅ በየቀኑ እየቋጠርህላቸው እንደሆነ እወቅ።

የወሊሶው ቡድን አስነዋሪውን ተግባር በፈጸመ ዕለት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተግባሩን ፍጹም ካወገዘ በኋላ ጉዳዩ በውይይት ይታይ፤ እንነጋገር ቢል ተሰምቶ የማያውቅ የስድብ ዶፍ አወረድህበት። ግን የደቡብ ካሊፎርኒያው አባታችን ብጹዕ አቡነ በርናባስ መድሎት ሚዲያ ላይ ባደረጉት ውይይት መፍትሔው ውይይት እና ንግግር እንደሆነ በግልጽ ተናግረዋል። አንተ በመንፈሳዊ ተግባር ስም ቤተክርስቲያናችንን ልታፈርስ የተነሳህ ቅጥረኛ ፖለቲከኛ ካልሆንህ በስተቀር ምን ቤት ሆነህ ነው ውይይት የለም የምትለው? ቀጠልህና አባታችን አቡነ ኤርምያስን ከፍ ዝቅ አድርገህ አጥረገረሃቸው። ወጥተው እንዲናገሩና ሚናቸውን እንዲለዩ የምትመራውን “መንፈሳዊ ቄሮ” መንጋ ላክህባቸውና አዋረድኻቸው። እርሳቸውም በነጋታው በዩትዩብ ቀርበው ቃላቸውን ሰጡ።

በዚህም አላበቃህ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጉዳዩ መንፈሳዊ ነው እንጂ ምንም የፖለቲካ ዓላማ የለውም በማለት በተደጋጋሚ ቢናገርም አንተ ግን ፖለቲካዊ በማድረግ መንግሥትን በኃይል የመናድ ተግባር በገሃድ እንዲፈጸም እየጎተጎትህ ነው። አንተ ጀርመን ተቀምጠህ ነው ይህንን የምትለው፤ ለሚሞቱም “ሰማዕትነት ነው፤ ገነት ትገባላችሁ” እያልህ “ክርስቲያናዊ ጂሃድ” ታውጃለህ። ልክ ጃዋር ተመሳሳይ ተግባር ይፈጽም የነበረው ከሞቀ ኑሮው፤ ደህንነቱ ከተጠበቀበት ሚነሶታ እንደ ነበር ማለት ነው። አንተን ከጃዋር እንዴትና በምን ልለይህ?

አሁን ብዙ ተከታይና ደጋፊ አለህ። አንተ ከዕውቀት የራቅህ ስለሆነ ነው እንጂ ማኅበራዊ ሚዲያ ለትራምፕም አልበጀው። ባንዴ ሁሉንም ሲዘጉበት ያንን ሁሉ በሚሊዮን የሚቆጠር ተከታዩን በሰከንድ ውስጥ ነው ያጣው። ስለዚህ ትንሽ ቆም ብለህ አስብ! ቀን ያልፋል፤ ገናና መንግሥታትም አልፈዋል፤ ከፈለግን በጥቂት ደቂቃ መንግሥትን መቆጣጠር እንችላለን ያለው ጃዋርም የተነፈሰ ፊኛ ሆኖ ልክፍት እንደያዘው በየተራራው ይሽከረከራል።

ስለዚህ ወዳጄ ልምከርህ፤ የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም። ከወዳጅ ይልቅ ብዙ ጠላቶች ይከተሉሃል፤ ይፈልጉሃል፤ ምክንያቱም አጀንዳቸውን ታስፈጽምላቸዋለህ። ወዳጅ መስለው ያበረታቱሃል፤ “ወጥር ዘመዴ” ይሉሃል፤ ስታወራ ያዳምጡሃል፤ “እግዚአብሔር ይመስገን” በሉ ብለህ ስትጀምር ማኅበራዊ ሚዲያህን ያጧጡፍልሃል፤ ምክንያቱም ሥራቸውን በነጻ እየፈጸምህላቸው ስለሆነ። አጀንዳቸውን አስፈጽመህ ስታበቃ እንደ ሸንኮራ መጥጠው ይወረውሩሃል፤ እንደ ሲጋራ አጭሰው ይረጋግጡሃል። አትርሳ የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም።

ገና ለገና ሽምግልና ውስጥ ገብታለች ብለህ ከፍ ዝቅ አድርገህ የሰደብሃት ኮማንደር ደራርቱ በርግጥም በሒደቱ ውስጥ እንዳለች የሲኖዶሱ የሕዝብ ግንኙነት ሲሳውቅ አንተም “ደርዬን አገኘኋት” ብለህ ብቻ ነው የፖሰትኸው። ቢያንስ እሷንም፣ ተከታዮችህንም ስለፈጸምኸው ነውር ይቅርታ ልትጠይቅና ምሕረት ልትለምን ይገባሃል። ደራርቱን በስልክ ደውዬ አነጋገርኋት፤ እንደለመደቸው መልካም ነገሮችን ነገረችኝ ካልህ በኋላ አንድ ቃል ከሷ ንግግር ጠቀሰህ። እኔም በዚያች የደራርቱ ቃል ልሰናበትህ “አንተም ዘመዴ ተረጋጋ” ነበር ደራርቱ ያለችህ! አትርሳ የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም።

ባለማተቡ ነኝ (trinity123@aol.com)

ከጎልጉል አማርኛ ኦንላይን የተወሰደ

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የሶማሌ ክልል በሃይማኖት ስም የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ እንደሚቃወም አስታወቀ
ከ997 ሚሊዮን ብር በላይ ከመመዝበሩ በፊት በጥቆማና በክትትል ዳነ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
OPINION

እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

April 8, 20260
OPINION

ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

April 8, 20260
OPINION

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – የሃሰት ትርክ ዘመቻ በደቦ

March 28, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
ART and CULTURE

አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ

May 17, 20260
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ May 17, 2026
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news