Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የዲጂታል መለያና የዲጂታል ግብይት በኢትዮጵያ በስፋት ሳይዳረስ ከወዲሁ ጥርሱን እየሳየ ነው፤ የኢትዮጵያን ማንነት የገዙ ተጨንቀዋል
News

የዲጂታል መለያና የዲጂታል ግብይት በኢትዮጵያ በስፋት ሳይዳረስ ከወዲሁ ጥርሱን እየሳየ ነው፤ የኢትዮጵያን ማንነት የገዙ ተጨንቀዋል

Ethioreview newsEthioreview news—November 10, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የዲጂታል ግብይትና የመታወቂያ ስርዓት በኢትዮፕያ ለማስፈን መንግስት ቁርጠኛ አቋም መያዙን ተከትሎ አገልግሎቶቹ ብዙም ስራ ላይ ሳይውሉ ገና ከጅምሩ ጥርሳቸው የሰላ መሆኑን በሌብነት ለተሰማሩ እያሳያቸው ነው። ህዝብ ንቁ ድጋፍ ካከለበት ብዙ ወንጀሎች በኢትዮጵያ ” ደህና ሰንብቱ” ይባላሉ።

በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ሙሉ በሙሉ ተጋራዊ ሲሆን ኢኮኖሚው ወዲያውኑ እስከ ሰባት ከመቶ እንደሚያድግ መንግስት ያስታወቀው ባደጉት አገሮች እንደሚደረገው የንግድ ስርዓቱ ላይ እዛና እዚህ በጨበጣ ማንነት እየተቀሸበ የሚሰራው ወንጀል ስለሚመክን ነው። በዚህም አገሪቱ በቀረጥ ገቢ የምታጣው ከፍተኛ መተን ያለው ሃብት ይድናል።

በቅርቡ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ስርዓት እንዲሆን ሲደረግ በአገር አቀፍ ደረጃ በገፊና ጎታች ትስስር አሰራሩ ተግባራዊ እንዳይሆን ያኮረፉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች፣ የነዳጅ ቀጂዎች ማህበር የሚባለው አካል ባገኘው ሚዲያዎች ተባብረው ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩበት ምክንያት አሁን ይፋ መሆኑን ለአብነት በማንሳት አሰራሩ ከወዲሁ ጥርሱን እያሳየ መሆኑን አመልክተዋል።

በዚሁ የዲጂታል ግብይት ወጥመድ የተያዙትን ከነቅጣታቸው ይፋ ያደረው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መንግስት የተሰጣቸውን ወይም የገባላቸውን ነዳጅ በወጉ ባልሸጡ ላይ መረጃ ማሰባሰቡንና የቁጥትር ስልቱ ራስን በራስ የማሰር እንደሆነ አመልካች ነው ተብሏል። ነዳጅን ከግብይት ስርዓት ውጭ በተገበያዩ ማደያዎች ላይ ዕገዳ መጣሉን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ሲያስታውቅ በሙሉ ዝርዝር ሳይሆን በግርድፍ ሲሆን በቅርቡ ከከፍተኛ ቅጣትና ማዕቀብ ጋር ይፋ የሚሆን መረጃ እየተዘጋጀ እንደሆነም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አመልክተዋል። በሁለተኛው ዙር ቅጣት ርህራሄ እንደማይኖርም ተመልክቷል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ከዲጂታል ነዳጅ ግብይት ስርዓት ውጪ ነዳጅን በመሸጣቸውና በስማቸው ከተጫነላቸው ነዳጅ በላይ በማደያቸው በሸጡ በአዲስ አበባና እና ሸገር ከተሞች በሚገኙ 97 ማደያዎች ላይ የአንድ ወር እገዳ እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ የዲጂታል ግብይት ቁጥጥሩን ያጠበቀ ለመሆኑ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ከዚህ ውስጥም 40 የነዳጅ ማደያዎች ላይ የአንድ ወር የነዳጅ ጭነት ዕገዳ የተጣለ ሲሆን፥ 57 ነዳጅ ማደያዎች ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዕገዳ የተጣለባቸው ማደያዎች ለባለስልጣኑ ከመስከረም10 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ በደረሰው ሪፖርት መሠረት በስማቸው ከተጫነላቸው ነዳጅ በላይ መሸጣቸው ተጠቁሟል፡፡ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ደግሞ ከተጫነላቸው ነዳጅ ከ50 እስከ 80 በመቶ የሚሆነውን ነዳጅ ብቻ በዲጂታል ግብይት መፈጸማቸው ተጠቅሷል፡፡

የነዳጅ ሕገ-ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባና እና ሸገር ከተሞች ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የዲጂታል መታወቂያ ለመውሰድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን መመዝገባቸው የሚታወቅ ነው። ይህን ተከትሎም ስራው ከተጀመረ በሁዋላ እየወጡ ባሉ መረጃዎች መንግስት ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ ፓስፖርትን ጨምሮ ኢትዮጵያዊ ማንነት የታደላቸውን የውጭ ዜጎች ዝርዝር እንደሚሰበስብ ታውቋል። በስደተኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው በሁለት ማንነት የሚንቀሳቀሱትን መለየት የሚያስችለውን ስራ ለመስራት ከሚመለከተው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ጋር የጋዊነት ስምምነት ውል አስሯል።

ከዓለም የስደተኞች ድርጅት ከናሽናል አይዲ ፕሮግራም ጋር በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ወይም በድርጅቱ ስር ያሉ የውጭ ዜጎችን ለመመዝገብ ስምምነት መድረሱ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ዜናው የገባቸው መረጃውን ” የወሩ ታላቅ ዜና” ብለውታል።

በቅርቡ በኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፓስፖርትን በገንዘብ ወይም በሌብነት ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ማደላቸው በመረጃ የተደረሰባቸው ተጠርጣሪዎች የኢትዮጵያዊ ማንነት ማረጋገጫ ፓስፖርት የሰጡት በአብዛኛው ለውጭ ዜጎች ነው። መንግስት ባደረገው ክትትልና በአርተፊሻል ኤጀንሲ በኩል በተሰበሰበ ዳታ ኢትዮጵያዊ ፓስፖርት የታደላቸው አካላት ተለይተዋል። ጉዳዩን የሚያውቁ እንዳሉት ከዓለም አቀፉ የሰደተኞች ድርጅት ጋር በተገባው ውል መሰረት ስደተኞቹ ሙሉ በሙሉ ወደ መረጃ ቋቱ ማንነታቸው ሲካተት የያዙት በብር የተሸመተ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እጃቸው ላይ እንዳለ ይመክናል። ሊጠቀሙበት ከፍለጉ ሲስተሙ በየበሩ ጥርስ ሆኖ ይይዛቸዋል። ስለሆነም ይህ ተግባራዊ ሲሆን በሃሰተኛ ሰነዶቹ ለመጓጓዝም ሆነ ያልተፈቀደ ተግባር ህጋዊ መስሎ ለመፈጸም ቢሞከር ትርፉ ተጨማሪ ቅጣትን በጎናጸፍ ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል።

በሶስት ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ ዜጎቿንም ሆኑ በስደት የሚኖሩትን በገቡበትና በወጡበት ቦታ ሁሉ ማንነታቸውን መሰወር ባማይችሉበት ደረጃ በመረጃ ቋቷ ውስጥ እንደምታስገባ ተመልክቷል። ይህ እንቅስቃሴ ስጋት ያሳደረባቸው ዓለም ሁሉ መዘመን ሲጀምር ድሮ የጀመረውንና እየሰራ የሚገኝበትን ሲስተም እየተቃወሙ ነው። ከምንም በላይ በውጭ አገር በዚሁ ስርዓት ውስጥ ግብር፣ ቀረጥ፣ ግዢና ሽያጭ፣ እንዲሁም አገልግሎት እየሰጡና እየተቀበሉ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ይህን ለምን ተግባራዊ ታደርጋለች በሚል የሚያካሂዱት ዘመቻ ለበርካቶች እጅ በአናት የሚያስጭን ሆኗል።

” መንግስት ዲክታተር ሊሆን ስላሰበ ሁሉን ለምቆላለፍ ሲል ነው ይህን የሚያደርገው” በሚል የአክቲቪስትነት ካባ የተደረበላቸው ዕለት ዕለት ሲተቹ የሚያደምጡ ” አናሎግና ዲጂታል ለተቀላቀለባቸው የሚገባቸው አንዳችም በጎ ነገር የለም” ሲሉ ይተቻሉ።

በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታትም 70 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የመመዝገብ እቅድ እንደተያዘም ብሔራዊ የመታወቂያ ፕሮግራም የኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ አቤኔዘር ፈለቀ  መናገራቸው ይታወሳል። አሁን ላይ ግን በሶስት ዓመት ድፍን አገሪቱን ለማዳረስ እየተሰራ ነው።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት ህግን ተከትለው ባልሰሩ 37 የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ንግድ ድርጅቶች ከተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ መስኮችና ዓላማ ውጪ የሰሩ፣ ባልታደሰ ንግድ ፊቃድ ሲነግዱ የተገኙ፣ ባስመዘገቡት የስራ አድራሻ ያልተገኙና የቅርንጫፍ አድራሻ ያላስመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በበጀት ዓመቱ መጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 402 የንግድ ድርጅቶች ላይ በተደረገው የክትትልና የቁጥጥር ስራ 365 ንግድ ድርጅቶች በህግ አግባብ የሚሰሩና 37 ንግድ ድርጅቶች ደግሞ ህግን ተከትለው የማይሰሩ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡


  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    by Ethioreview news
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    by Ethioreview news
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    by Ethioreview news
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    by Ethioreview news
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
    by Ethioreview news
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የፕሮስቴት እጢ ምልክቶችና ህክምናው
፸ ዓመት አይበቃም ወይ? ዳንኤል ክብረት የአመክንዮ በትር …
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2