Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ህገወጥ የውጭ ገንዘብ አምራቾች ተያዙ፤ ማንነታቸውና ስማቸው መደበቁ ጥርጣሬ ፈጥሯል
News

ህገወጥ የውጭ ገንዘብ አምራቾች ተያዙ፤ ማንነታቸውና ስማቸው መደበቁ ጥርጣሬ ፈጥሯል

Ethioreview newsEthioreview news—November 25, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ አጣቢዎችን ማንነት ለማወቅ ከባህር ማዶ ቢሮ ከፍተው ዶላር የሚሰበስቡትን ከመጠርሪያ ስማቸው በመነሳት መለያየት ቀላል ነው። በውጭ አገር ሆነው ፖለቲካ በመቀመርና ለፖለቲካ ቅመራው እርዳታ በመጠየቅ የዲጂታል ለማኝ የሆኑት ቢያንስ ይህን ስራ ቢሰሩ እንደሚሻላሸው ምክር የሚሰጡት ስራው እጅግ ከፍተኛ ገንዘው ወደ ሌላ አገር እያሻገረ በመሆኑ ነው።

በዚሁ የምንዛሬ አጠባ ሁለት አበይት ጉዳዮች ይነሳሉ። አንዱ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ኮንትሮባንድ ላይ የተሳተፉ ህዝብ የሚያውቃቸው “የውጭ ዜጎች” በህገወጥ ንግድ በሚሊዮኖች ብር ይሰበስባሉ። የአገሪቱን ኢኮኖሚ ያደቃሉ። ከውጭ ሆነው ምንዛሬ በመቀበል ኢትዮጵያ ውስጥ በኮንትሮባንድ በሚሰብሰበው ብር ከፍተኛ ምንዛሬ ይሰጣሉ።

በዚህ ስራ የተሰማሩት ክፍሎች ከውጭ ገንዘብ ለተላከላቸው ሰዎች ያለው ውድድር፣ ያለቀረጥ ክፍያ በኮንትሮባንድ ያፈሱትን ገንዘብ ወደ ውጭ ገንዘብ በመቀየር ለራሳቸው አገር የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እንደሆኑ ስራውን የሚያውቁ በተደጋጋሚ ያስረዳሉ። አዲስ አበባ ከትመው ኢትዮጵያን በሁለት ካራ የሚገዘግዙት እነዚህ ክፍሎች በህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ በስፋት ከሚሰሩት መካከልም ናቸው። ይህን የኋላ ጉዳይ ያስታወሰው ዛሬ የተሰማው የህገወጥ ዶላር ህትመትና አዘዋዋሪዎች መያዝ ነው።

በአዲስ አበባ በህገወጥ የታተመ የውጭ ምንዛሬ በድብቅ ሲያዘዋውር ነበር የተባሉ ተጠርጣሪ ተይዟል። የመንግስት መገናኛዎች ባሰራጩት በዚህ የሌብነት ዜና የተያዘው ተጠርጣሪ ማንነትና ስም አለመጠቀሱ ጥርጣሬ አስነስቷል። ዜናውን ተከትሎ ” ባትነግሩንም አውቀናቸዋል። ገንዘብ ዝውውር ስር የሚራወጡት ይታወቃሉ” የሚል አስተያየትም ተሰጥቷል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ከ28ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሲያስታውቅ፣ ይፋ የተደረገው ተጠርጣሪው ሲጠቀምበት የነበረ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2- C 32496 አ/አ በሆነ ተሽከርካሪና ኤግዚቢት የተያዘውን ብር ነው።

ስሙ እንዲገለጽ ያልተፈለገው ተጠርጣሪ 284 ባለ መቶ ኖቶች(28 ሺህ 400) ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 መክሊት ህንፃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። በተደረገ ፍተሻ ከሃሰተኛ ዶላሩ በተጨማሪ ስታር ሽጉጥ ከ 8 ጥይቶች ጋር ተገኝቶበታል።

በአዲስ አበባ የዶላር አጠባ ላይ በብዛት የተሰማሩ ወገኖች እነማን እንደሆኑ የሚታወቅ በመሆኑ፣ የስም ስወራው ጉዳዩን ለማድበስበስና ታልሞ ሊሆን ይቻላል የሚል ስጋት ያላቸው ” ማንነቱና ስሙ ይገለጽ። ሌብነት ላይ የተተከለ ዲፕሎማሲ ጥንቅር ብሎ ይቅር” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። የአገር ስም ጠርተው ” ሚስጢር አይደለም” ያሉም አሉ።

ሀሰተኛ ገንዘቦችን በማተምና ወደ ገበያ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ የሚፈፀም ወንጀል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ይህንን ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት የሚሰጠውን መረጃና ጥቆማ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና ሐሰተኛ የውጭ ሀገራትና የኢትዮጵያን ብር በማተምና በማሰራጨት የተጠረጠሩ የካሜሩንና የጊኒ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦቸ በቁጥጥር ስር ዋሉ። ፖሊስ ስማቸውንና ማንነታቸውን ይፋ አደጓል።

ሐሰተኛ የገንዘብ ሕትመትና ስርጭት እንዲሁም ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉና የወንጀል አፈጻጸም ሂደቶቻቸውም እየተወሳሰበ መምጣቱን ተከትሎ በጥናት ላይ የተመሰረተ ምስጢራዊ ክትትል ሲደረግ መቆየቱንና በጸጥታ አካላት እርምጃ መወሰድ መጀመሩን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ሐሰተኛ የውጭ ሀገራትና የኢትዮጵያን ብር በማተምና በማሰራጨት የተጠረጠሩ የካሜሩንና የጊኒ ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች እንዲሁም በተባባሪነት ስትሳተፍ የነበረች አንዲት ኢትዮጵያዊት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ ላይ ይገኛል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 እና 04 እንዲሁም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የግለሰቦችን ቤት በመከራየት ሐሰተኛ የገንዘብ ሕትመትና ስርጭቱን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ለረጅም ጊዜ በተደረገው ክትትል በመረጃና በማስረጃ በመረጋገጡ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

አልበርት ናዲፎን በሚል ስም የሚጠራው ካሜሩናዊና መሀመድ ጉኒ የተባለው የጊኒ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ከስድስት ወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ማህሌት ጥላሁን ከተባለች ኢትዮጵያዊት ጋር ሕገወጥ ድርጊቱን ሲያከናውኑ መቆየታቸው ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከግለሰቦች ተከራይተው ሐሰተኛ የገንዘብ ሕትመቱን ሲያከናውኑባቸው የነበሩ ሦስት የመኖሪያ ቤቶች በጥናት ተለይተው ሕጋዊ እርምጃ በተወሰደባቸው ወቅት ለወንጀል ድርጊቶቹ የሚጠቀሙባቸው በርካታ ኤግዚቢቶች ተይዘዋል፡፡

ሐሰተኛ ገንዘቦቹን ለማተም የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ቁሶች፣ ፈሳሽ ኬሚካሎች፣ፓውደሮች፣ሐሰተኛ ገንዘቦች፣ የዶላር ማረጋገጫ ቴስት ላይት፣ ፓስፖርቶች፣ የባንክ ደብተሮች እንዲሁም አደንዛዥ እፅና ሌሎችም ማስረጃዎች ከተያዙት መካከል ይገኙበታል ሲሉ የመንግስት መገናኛዎች ዘግበዋል።


  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት”… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
እጅግ ግዙፍ የበረዶ ግግር ተገምሶ ስፍራውን በመልቀቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴ አስግቷል
አዲስ አበባ – ሙስና በገሃድ፤ የትራንስፖርት ፣ የመሬት፣ የካርታ፣ የግንባታ ፍቃድ ፣ የመታወቂያ … አገልግሎቶች ምሬት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2