Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  FEATURED  አጭበርባሪው ፓስተር ጆሽዋ ሚሊዮኖችን ያታለለባቸው ተአምራዊ የፈውስ ዘዴዎች – ከምርመራ ማህደር
FEATUREDSOCIETY

አጭበርባሪው ፓስተር ጆሽዋ ሚሊዮኖችን ያታለለባቸው ተአምራዊ የፈውስ ዘዴዎች – ከምርመራ ማህደር

Ethioreview newsEthioreview news—January 21, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

– ከኢትዮጵያ እዚሁ ፓስተር ጋር በመመላለስ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ምን አሉ? ወይም ምን ተባሉ?

ወንጌልን በገባቸው መጠንና በተረዱት ልክ የሚያሰርጩ “ቅን እረኞች” አሉ። እንደየ ዕምነቱ ይለያይ እንጂ ሁሉም ጋር ባመኑበት “ለጽድቅ” ሲሰሩና ሲያገለግሉ የኖሩ አሉ። አሁንም ድረስ በዚህ በቀናነት መንገድ ለፈጣሪያቸው በቅናት ደፋ ቀና የሚሉ ጥቂት እንዳሉት ሁሉ መጽሃፍ ቅዱስ ተሸክመው ማጅራት የሚመቱ ወስላቶች፣ ዓይን አውጣዎች፣ ፍጹም ሌቦችና አጭበረባሪዎቹ በዝተዋል።

እርስ በርስ እየተሿሿሙ በቅባት፣ በፈውስና በተዓምራት በአደባባይ ማጅራት የሚመቱ የተደራጁ ሿሿ ሰሪ ፓስተሮች፣ ነብዮች፣ መጋቢዎች፣ ሃዋሪያ ተብዬዎች ጉድ እንደ ቢቢሲው የምርመራ ጋዜጠኛ የሚከፍታቸው ተፍቶ እንጂ በዝርፊያ የተጨማለቁ ናቸው።

በአንድ ወቅት ኢህአዴግ የፓስትሮችን የባንክ አካውንት ምርመራ ማድረግ በጀመረበት ወቅት ከዛሬ አስራ አምስትና አስራ ስድስት ዓመት ገደማ በፊት አስራ አንድ ሚሊዮን፣ ሰባት ሚሊዮንና ከዛው ጋር ተቀራራቢ የሆነ ብር በስማቸው የተገነባቸው ነበሩ። ምርመራው ለምን እንደተቋረጠ ባይታወቅም በወቅቱ ምርመራው ድንጋጤ ፈጥሮ ነበር።

በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምዕመናን መቆሚያ እስኪያጡ ድረስ አውደ ምህረቷን በመቸርቸር በብር የናጠጡ፣ የራሳቸውን ጡንቻ የገነቡና ሲያሻቸውም ደጋፊ እየነዱ የሚናኙ ጥቂት አይደሉም።

አሁን በየስርቻውና በየአደባባዩ በተከፈቱ፣ በየክልል ከተሞች በተቋቋሙ የፕሮቴስታንትና የወንጌላዊያን ቤተክርስቲያን ውስጥ ድህነት ላይ ያተኮረ “የተደራጀ” ስብከት እንዴት ያለ ማጅራት መቺነት እንደሆነ ራሳቸው ለቅስቀሳ በአቋቋሙዋቸው ሚዲያዎች እየታየ ነው። ሃፍረት በጎድለው መልኩ መረን ወጥቶ ምስኪኖችን በማጭበርበር ኪስ የሚያወልቁት የተደራጁ “ባለ ማዕረግ ወጠጤዎች” የራሳቸው ጋርድ፣ የራሳቸው ድንበርና የዝርፊያ ቡድን በአደባባይ መስርተው ሲዘርፉ ምንም አለመባላቸው አሳዛኝ ነው።

እንደ ታዋቂው ሌባ ጆሽዋ ባይሆንም እሱ ጋር እየተመላለሱ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ በወቅቱ ጉራ መስሏቸው ” እሱ ጋር ሄጄ” በማለት ፎቶ ሳይቀር ይለጥፉ ነበር። ሰርቶ መብላት የማያውቀው የኢትዮጵያ አሸን ሚዲያ ሃያ አራት ሰዓት ቁጭ ብለው “ሁሉንም እናውቃለን” በሚል ስሌት ከመለፍለፍ ይልቅ እንዲህ ያሉትን የቀትር ማጅራት መቺዎች በምርመራ ስራ ማጋለጥ ስራቸው በሆነ ነበር።

የሰዎችን ንግግርና አስተያየት እየቆራረጡ ከሚበልቱት በቀር እንዲህ ባለው ዕልህና ጽናት በሚጠይቅ ስራ ላይ ማተኮር የማይፍለጉት የአገራችን ሚዲያዎች ለተደራጁት “መንፈሳዊ ተብዬ” ማጅራት መቺዎች የተመቻቸ ዕድል ፈጥረውላቸዋል። ወይም ሌላ ግንኙነት አለ። ለሁሉም ግን ቢቢሲ ጆሽዋ እንዴት ሲያጭበርብር እንደነበር ዘክዝኮታል ያንብቡ። እነዛ እሱ ጋር ኮርስ ወስደው የነበሩትስ የት ደረሱ? ቢቻል ራሳችሁ ተናዘዙ

ቢቢሲ ገናና የነበረውን ፓስተር ጆሽዋን እና በሴቶች ላይ መድፈርን ጨምሮ ያደርስ የነበረውን ስቃይ በምርመራ ጋዜጠኝነት ማጋለጡ ይታወሳል።

ፓስተር ጆሽዋ ሚሊዮን ተከታዮቹን የ‘’ተአምራት’’ ድርጊትን እፈጽማለሁ በማለት ሲያታልል ኖሯል።

ለ20 ዓመታት ሚሊዮኖችን እንዴት ሊያታልል ቻለ?

‘ሽባዎችን’ ከዊልቸራቸው ተነስተው እንዲዘሉ ያደርግ የነበረው እንዴት ነው?

ሙታንን አስነሳሁ ያለውስ ምን ዘዴ ተጠቅሞ ነው?

በ2004 የናይጄሪያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እነዚህ ‘ተአምራት’ በቴሌቪዥን ለሕዝብ እንዳይተላለፉ አግዶ ነበር። በዚህን ጊዜ ነበር ዝነኛው ፓስተር ጆሽዋ ኢማኑኤል ቲቪን ከሳተላይት ማሰራጨት የጀመረው።

ይህ ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን የስብከትና ተአምራት ቴሌቪዥኑ በዓለም ላይ እጅግ ስኬታማ ከሚባሉት አንዱ ነበር።

ፓስተር ጆሽዋ ‘’ተአምራቱን’’ በዚህ ጣቢያ ለዓለም ሲያሰራጭ ከሩቅ ምሥረቅ እስከ አውሮፓ፣ ከሰሜን አሜሪካ እስከ ደቡብ ሚሊዮኖችን መድረስ ችሎ ነበር።

በመቶ ሚሊዮኖች መታየት የቻሉለት ተአምራቱ ለፖስተር ጆሽዋ አይነኬ እንዲሆን ምክንያት ነበሩ።

በ2021 ዓ/ም በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ፓስተር ጆሽዋ የተዋጣለት ‘አጭበርባሪ’ ነበር።

የቢቢሲ ምርመራ እንዳጋለጠው ይህ የማጭበርበር ጥበቡ ከናይጄሪያ አልፎ በዩኬ፣ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካና ጀርመን ጭምር የተቀነባበረ ነበር።

የሚከተሉት 6 የጆሽዋ ማጭበርበሪያ ስልቶችን እናስተዋውቃችሁ።

1- የድንገተኛ አደጋ ክፍል

በቤተ ክርስቲያኑ የድንገተኛ አደጋ ክፍል የሚባል አለ። የዚህ ክፍል ዋና ሥራው ሐሰተኛ ተአምራቱ እውነተኛ እንዲመስሉ ማስቻል ነው።

ይህ ክፍል ታመው የሚመጡ የሚለዩበትና ለጆሽዋ ጸሎት የሚዘጋጁበት ነው።

ለ10 ዓመታት ይህን ክፍል የመራው አጎሞህ ፖል ለቢቢሲ እንደተናገረው የዚህ ክፍል አባላት በሕክምና የሰለጠኑ ዶክተሮች ናቸው።

ለምሳሌ እውነተኛ ካንሰር ያለበት ሰው ይባረራል። ሆኖም ግን የሚድን መለስተኛ ቁስል ያለበት ግን በካንሰር ስም ተማሚ ተደርጎ ይመዘገብና ወደ ጆሽዋ ክፍል ይተላለፋል።

ለታማሚዎቹ ልዩ ኮድ ይሰጣቸዋል። ለጆሽዋ ፍጹም ታማኝ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው እዚህ ክፍል መግባት የሚችሉት። ከዚያ በቀላሉ መዳን የሚችሉትን ጆሽዋ እንዲያውቃቸው ይነገረዋል። ከዚህ በኋላ ካሜራ እንዲመጣ ይደረጋል። እጁን ይጭንባቸዋል። ከዚያ ዳኑ ተብሎ እልል ይባላል።

“ነገሩ ውስብስብ ሂደት አለው። ጥቂት ምእመናን ብቻ ናቸው የማጭበርበሪያ ስልቱ የሚነገራቸው” ይላል ለ10 ዓመታት ይህን ክፍል የመራው ፓል ለቢቢሲ።

2- በሐኪም የሚታዘዝ መድኃነኒት

ከውጭ አገር ታመምን ብለው የሚመጡ ሰዎች ጆሽዋ ማረፊያ ሲደርሱ የያዟቸውን መድኃኒቶች እንዲጥሉ ይደረጋል።

ከዚያ ሙሉ የበሽታቸውን ሁኔታ የሚገልጽ ፎርም እንዲሞሉ ይደረጋል።

ከእንግዲህ መድኃኒቶቹን በፍጹም እንዳይወስዱ ይነገራቸዋል። ነገር ግን ጆሽዋ ፋርማሲ ባለሙያዎቹን ተመሳሳይ መድኃኒት እንዲያዘጋጁ ያደርጋል።

ከዚያ ተአምራዊ መጠጥ በሚባለው የፈውስ አገልግሎት ውስጥ መድኃኒቶቹ ይሰጧቸዋል። በሽተኞቹ ይህን አያውቁም። የሚያውቁት ጆሽዋ እንደጸለየባቸው ብቻ ነው።

ለምሳሌ በ1990ዎቹ ኤች አይ ቪ በአፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ በሚዛመትበት ዘመን ጆሽዋ ምእመኑን ወደ ቤት ሲመለሱ አንቲቫይራል መድኃኒት እንዳይወስዱ ይነግራቸው ነበር። ለጊዜው የተፈወሱ የሚመስላቸው ምእመናኑ ወደ አገራቸው ከተመሰሉ በኋላ ይሞታሉ።

ጆሽዋ በርካታ ሴቶችን መድፈሩን ቢቢሲ በምርመራ ጋዜጠኝነት ደርሶበታል
የምስሉ መግለጫ,ጆሽዋ በርካታ ሴቶችን መድፈሩን ቢቢሲ በምርመራ ጋዜጠኝነት ደርሶበታል

3- ‘የአእምሮ እጥበት’

የጆሽዋ ዋናው ጥበብ የሰዎችን አስተሳሰብ ማጠብ ነው። የሚያዩትን ነገር እንዳይጠራጠሩ አድርጎ ማታለል።

ሚስ ፎርድ ስትናገር ‘በዚያ ወቅት የማየውን በሙሉ አምን ነበር። ለምሳሌ ከዊልቸር ተነስቶ ሲዘል ሲራመድ ስመለከት አእምሮዬ በሱ አመነ’ ትላለች።

ይህ በጥንቃቄ የሚዘጋጀው የፈውስ ቴአትር ጆሽዋን ስኬታማ አድርጎታል።

የጆሽዋ ረዳት የነበረ አንድ ግለሰብ ይህን ሲያስረዳ ወደ አደባባይና ወደ ካሜራ ከመውጣታቸው በፊት ፈውስ ፈላጊዎች ችግራቸውን እንዲያጋንኑ ይነገራቸዋል ይላል።

“ችግራችሁን አተልቃችሁ ተናገሩ፤ ፈጣሪ ትልቅ በረከት እንዲሰጣችሁ፤ ፈውሳችሁም ትልቅ እንዲሆን ይረዳል” ተበሎ ይነገራቸዋል።

በዚህ ስሌት መሰረት መጠነኛ ችግር ያለባቸው በተቻለ አቅም ችግራቸውን አጋንነው እንዲያወሩ ይሆናሉ።

የጆሽዋ ቤተ ክርስቲያን የራሱ በቂ የሆኑ ዊልቼሮች አሉት። ተራምደው የመጡ ሰዎች እንኳ ቢሆኑ ዊልቸሩ ላይ ተቀምጠው ወደ መድረክ እንዲወጡ ይደረጋል።

“በዚህ ተአምራዊ ዊልቸር ካልተቀመጣችሁ ጆሽዋ አይጸልይላችሁም፤ ችግራችሁን አይፈታም እንላቸዋለን፤ ከጸለየላቸው በኋላ ደግሞ ዊልቸሩን ጥለው እንዲጮኹ እንነግራቸዋለን” ይላል የጆሽዋ ረዳት።

ቢሶላ የምትባልና 14 ዓመት ለጆሽዋ የሠራች ሴት ስትናገር በአንድ ወቅት በቂ ማጣራት ሳይደረግ የእውነት ሽባ የሆነ ሰው በዊልቸር ወደ ስቴዲየም ገባ። ጆሽዋ ፈውሻችኋለሁ ሲል ለመነሳት ሞክሮ ሲወድቅ አየሁት” ትላለች።

በአንድ ወቅት ጆሽዋ እንዲህ አለኝ ትላለች ቢሶላ፤ “አትጨነቂ ይህን የማደርገው (ለክፋት ሳይሆን) ብዙ ሰዎች ጌታ ላይ እምነት እንዲያሳድሩ ብዬ ነው።”

  • ዝነኛው ፓስተር ቲቢ ጆሽዋ ምዕመናንን መድፈሩን እና ማሰቃየቱን የቢቢሲ ምርመራ አጋለጠ8 ጥር 2024

4- በጉቦ የሚተውኑ ምንዱባን

የጆሽዋ የቀድሞ ምእመናን እና ባልደረቦች ለቢቢሲ ሲናገሩ ራሳቸውን አካል ጉዳተኛ መስለው እንዲተውኑ የሚዘጋጁ ሰዎች ጉቦ ይሰጣቸዋል።

ለምሳሌ አዲስ አገር ለፈውስ አግልግሎት ሲኬድ በቅድሚያ ምልመላ ይደረጋል። ምንዱባን የሚኖሩባቸው ሰፈሮች መልማዮች ይላኩና ጠቀም ያለ ገንዘብ ተሰጥቷቸው የሚተውኑ ሰዎች ይዘጋጃሉ።

ከዚያ የመድረክ ተውኔቱ ከመጀመሩ በፊት ለጆሽዋ እነዚህ ምልምል ተዋንያን የለበሱት ልብስና የቱ ጋ እንዳሉ ይነገረዋል። ከዚያ የእውነት ታማሚ ከሆኑ ሰዎች መሀል ይደረደራሉ።

ጆሽዋ እነሱ ጋ ሲደርስ ያጠኑትን ይተውናሉ። ‘ተፈወስን’ ብለው ይዘላሉ። ለዚህ ጠቀም ያለ ጉቦ ይሰጣቸዋል።

5- ሐሰተኛ የሕክምና ሰርተፍኬት

ለሚሊዮኖች በጥንቃቄ ተሰናድቶ የሚሰራጨው የፈውስ አገልግሎት ብዙውን ጊዜ ኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎችን የመፈወስና ካንሰር የነበረባቸውን የማዳን ተግባር ያካትታል።

ዶክተሮች እነዚህ በሽተኞች መዳናቸውን በምስክርነት እንዲናገሩ ይደረጋል።

በ2000 ዓ/ም አንድ ሶይንካ የተባለ የናይጄሪያ ጋዜጠኛ እነዚህ የሕክምና ሰርተፍኬቶች ሐሰተኛ እንደሆኑ ደርሶባቸው ለማጋለጥ ሞክሮ ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ የትም ሳይደርስ ተድበስብሶ ቀረ።

እስከዛሬም ግን ተፈውሰናል ብለው የሚያምኑ ሰዎች በርካታ ናቸው።

“እውነታው ግን ሁሉም ነገር የተጠና ተውኔት ነው። የተውኔቱ ደራሲውና አዘጋጁ ደግሞ ፓስተር ጆሽዋ ነው” ይላል ፖል።

6- ቪዲዮ ቅንብር

ተአምራት የሚባሉ ፈውሶች በሙሉ ይቀረጻሉ። ከዚያ ቪዲዮዎቹ በከፍተኛ ጥንቃቄ ይቀናበራሉ። ፈውሱ ከጆሽዋ ጸሎት በኋላ በቅጽበት የሆነ እንዲመስል ይደረጋል። ይሁንና ታማሚው ምናልባት ጤናው መሻሻል ያሳየው ከዓመት በኋላ ሊሆን ይችላል።

ነገር ግን ታማሚ ሳለና ከዚያ መሻሻል ሲያሳይ የሚቀረጹት ፊልሞች ይቀናበሩና ጆሽዋ ልክ ሲጸልይ ግለሰቡ የዳነ እንዲመስል ይደረጋል። ከዚያ ለሚሊዮኖች ይሰራጫል።

ይህን ለቢቢሲ ያጋለጠችው ደግሞ በጆሽዋ ኢማኑኤል ስቱዲዮ ለ5 ዓመታት በአቀናባሪነት ያገለገለችው ቢሶላ ናት።

“እውነተኛውን የቪዲዮ ክፍል ሰዎች እንዳያዩት ቆርጠን እናወጣለን፤ ሚሊዮኖች ያዩት ሁሉ ቅንብር ነው፤ ይህን የምለው ደግሞ እኔም አንዱ አቀናባሪ ስለነበርኩ ነው” ትላለች ቢሶላ።

ቢቢሲ በዚህ ጉዳይ ላይ አሁንም አገልግሎት ላይ ከሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን ምላሽ አላገኘም።ከዚህ ቀደም ቤተ ክርስቲያኑ ባወጣው መግለጫ “በጆሽዋ ላይ የሚሰነዘሩት ትችቶች መሠረተ ቢስ ናቸው ብሎ ነበር።

ሙሉ ዘገባው የቢቢሲ ነው

SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ቴዲ አፍሮ ለጥምቀት የተዘቀዘቀ መስቀል ያለበት ጥበብ መልበሱ እያነጋገረ ነው
ግብጽ ሶማሊያ በምትፈገው ሁሉ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች፤ ኤርትራም ተመሳሳይ አቋም አላት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
FEATURED

የጸረ – ቤተሰቡ የአንዳርጋቸው ጽጌ የፖለቲካ ውርዴ ውርስ፣ ባንዳነትና ክህደት

November 7, 2025
FEATURED

የአስገድዶ መድፈርና የግፍ ወንጀል – ከትግራይ የወጣው አዲስ ሪፖርት ገለልተኛነት?

October 23, 2025
ECONOMY

“የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማየት ሁላችንንም ያብቃን፤ እኔ እንደማይ አምናለሁ፤ ያመነ ከእኔ ጋር ይጓዝ” አብይ

October 8, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2