Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ባለሀብቶች ብድር ከመስጠት አንስቶ ሌሎችም ድጋፎች እንደሚሰጥ ተገለፀ፡፡

    February 9, 20220

    ሹፌሮችን በመግደል ተሽከርካሪ ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች የሞት ቅጣት ተወሰነባቸው

    October 21, 20240

    የአማራ ክልል ከትግራይ ጋር ሁሉንም ጉዳይ በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመጨረስ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

    March 31, 20230

    Sudan official: ‘Mediation between Khartoum and Addis Ababa faces obstacles’

    February 14, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    መላው አማራ ከነገ ጀምሮ ለህልውና ዘመቻ እንዲነሳ ክተት ተጠራ

    July 25, 20210

    የጆ.ባይደን አስተዳደር የሰላም አማራጭ ንግግሩን ቀድሞ የትህነግን ፍላጎት አቋም አድርጎ አቀረበ

    November 1, 20220

    በሽረ አዲስ ተስፋ፤ ሕዝብ በነጻነት ስለቀጣዩ ዕጣው አየመከረ ነው

    December 26, 20220

    እውነትን ለሥልጣን መናገር ፣ ሳማንታ ፖወር ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

    March 1, 20210

    በአዲስ አበባ ከ27ሺህ በላይ ወጣቶች ተደራጅተው ከተማዋን እየጠበቁ ነው

    November 11, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል
News

ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል

Ethioreview newsEthioreview news—April 17, 20240
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም ጠቅሶ ለአራተኛ ጊዜ ወረር የተፈጸመባቸውን ስፍራዎች አስታወቀ። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የፌደራል መንግስትና ዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ የህወሃትን የዳግም የጦርነት አዋጅ እንዲያወግዙና እንዲያስታግሱ ጠይቋል።

ትህነግ ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ እንደሆኑ ያስታወቀው መግለጫው የክልሉ ሕዝብ፣ የፌደራል መንግሥቱ እና ዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ድርጊቱን እንዲያውቁትና እንዲያስቆሙ ጠይቋል።

“የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ” ሲል ማሳሰቢያ ያቀረበው የአማራ ክልል “ይህ የማይኾን ከኾነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመኾን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መኾኑን ለማሳወቅ እንወዳለን” ብሏል።

“ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈጸም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈጸመባቸው አካባቢዎች ናቸው” ያለው የአማራ ክልል ያወጣው መግለጫ ትህነግ ከጦርነት ውጭ መኖር እንደማይችል ለማስታወስ የማንነት ጥያቄ የቆየ ጥያቄ መሆኑን አመልክቷል።

More stories

ለመንግስት ሁሉ አቀፍ የሰላም አሳብ ቀረበለት፤ የእርቅ ኮሚሽን በመጪው ዓመት ህገ መንግስት እስከመቀየር የሚያደርሰውን ስራ ይጀምራል

September 6, 2023

አንድ መቶ አስራ አንድ አገሪቱን በብሄርና በሃይማኖት የሚንጡ ህገወጥ ድረ ገጾች ተለዩ፤ አስሩ ተያዙ

June 1, 2022

ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን ሊተካ የሚችል የማህበራዊ ትስስር ገጽ ስራ ላይ ልታውል ነው

August 21, 2021

ኢትዮጵያ አንደ አገር ገናና በነበረችበት ዘመን አሜሪካ አትታወቅም ነበር

October 17, 2022

በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩና ፍትህ የተዛባባቸው የአማራ ተወላጆች ስቃይ በተሞላበት ችግር ውስጥም ኾነው በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መኾኑ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች የተረጋገጥ ጉዳይ እንደሆነ መግለጫው አስታውሶ ነው ወረራ መፈጸሙን ያወገዘው። ሙሉ መግለጫውን ከስር ያንብቡ

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናብቦና ተቀናጅቶ በርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ ካቢኔ አማካኝነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ይህን የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት የሆነውን የህወሓት ቡድን ባለፉት ሦስት ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈጸም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈጸመባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች ስቃይ በተሞላበት ችግር ውስጥም ኾነው በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መኾኑ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች የተረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡

ተቸንካሪነት ዋና መለያ የኾነው የህወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን አሰቃቂና ታሪክ ምንጊዜም የማይዘነጋው የባንዳነት ተግባር ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያዊያን እና በጀግኖች የፀጥታ ኀይሎች አማካኝነት የሽንፈት ፅዋን ከመጎንጨቱ ባሻገር የማንነትና የራስ አሥተዳደር ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት ችለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ኹኔታ ያልተመቸው ተቸንካሪው የህወሓት ቡድን በሦስት ዙሮች ከተደረገው ጦርነት ማግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡አሁንም እየፈጸመ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የአማራ ክልል መንግሥት ይህን መሰሉን የህወሓትና የግብረ አበሮቹን ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ እየጠየቅን ይህ የማይኾን ከኾነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመኾን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መኾኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የተከበራችሁ በክልላችን በየደረጃው ያላችሁ የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር አባላት፡- ከሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ ትህነግ በቀሰቀሰው ጦርነት ሕዝባችን ቀጥተኛ ተጠቂ በመኾኑ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ተዳርጎ የነበረ መኾኑ ይታወቃል፡፡ ኾኖም ግን በየደረጃው የሚገኙ የመዋቅር አባላት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ጥምር የጸጥታ ኃይሎችና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመኾን ሀገር አፍራሽ የጥፋት ኀይሉ ላይ የተቀዳጀው ድል ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ በፅናትና በቁርጠኝነት ሕዝቡን በማደራጀት አካባቢያችሁን በመጠበቅ ታሪካዊ ኀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የተከበርከው የክልላችን ሕዝብ፡- በተደጋጋሚ ጥቃት የፈጸመብህ የጥፋት ኀይል ዛሬም እንደ ትናንቱ ወረራ ፈጽሟል፡፡ በመኾኑም መላ የክልላችን ሕዝብ ከሐሰት ፕሮፓጋንዳ እና ሠርጎ ገቦች ራስህን በመጠበቅ ከክልል መንግሥትና በየአካባቢው ከሚገኙ አሥተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቻችን የከፈቱብንን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የድርሻህን እንድትወጣ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት፡- የፌደራል መንግሥት ህወሓት የቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ ማድረጉን ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተደረገውን ጥረት በሙሉ ልብ በመደገፍ ለውጤታማነቱ የድርሻችንን ስንወጣ ቆይተናል፡፡ ኾኖም ግን ህወሓት በተደጋጋሚ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሲያፈርስ ቆይቷል፡፡ አሁንም በሙሉ አቅሙ ወደ ጦርነት ገብቷል፡፡ ይህን እኩይ ድርጊቱን የአፍሪካ ኅብረትና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል፡፡በመኾኑም ይህን እብሪተኛ ቡድን በአጭር ጊዜ ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ሕዝባችንን ከጥፋት መታደግና የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ይገባል፡፡

ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ

ህወሓት ከምስረታዉ ጀምሮ ለአማራ ሕዝብ ባለው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት በአማራ ሕዝብና በመላ ሀገሪቱ ሕዝብ ላይ የማያባራ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ሲቀሰቅስ ኖሯል፡፡ ለዚህም ነው ህወሓት የኢትዮጵያም ኾነ የአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋት ምንጭ ነው የምንለው፡፡

ኾኖም በአሳሳች የፕሮፖጋንዳ ሥራዎቹ ምክንያት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ በህወሓት ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም ሲይዝ ተስተውሏል፡፡ ዛሬ ግን ለዚህ አሳሳች ፕሮፖጋንዳው ያልተመቼ ኹኔታ ተፈጥሯል፡፡ በጠራራ ጸሐይ የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ወቅት ወረራ መፈጸሙ በገሃድ ታይቷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀደም እንዳደረገው በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ማወናበድ አይችልም፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ህወሓት የፈጸመብንን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝና ከጎናችን እንዲቆም የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

ሚያዚያ 08 /2016 ዓ‹ም

ባሕር ዳር

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?
የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ART and CULTURE

አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ

May 17, 20260
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
ART and CULTURE

አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ

May 17, 20260
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • አጭር ዳሰሳ ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ May 17, 2026
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news