Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  Reaction  የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው?
Reaction

የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው?

Ethioreview newsEthioreview news—May 24, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ብዙዎቻችን ውሀን የመጠጣት ባህላችን በጣም ዝቅ ያለ ነው። ይህ ልምድ ደሞ ብዙ መዘዝን ይዞብን ምጣቱ አይቀሬ ነው።

አንድ ወንድማችን “ኩላሊቴ በጠጠር ምክንያት ፈሳሽን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ አልቻለም እና ሀኪሞቹ አሁን መውጣት አይችልም ፣ ገና ነው የሚል መልስ ነው የሰጡኝ ፣ እና ለምንድን ነው” የሚል ጥያቄ አንስቶልኝ ነበር።

የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው ጊዜ 80% በውስጡ ካልሺየም ኦግዛሌት (calcium oxalete) የተቀሩት ደግሞ ከካልሺየም ፍስፌት (calcium phosphate) ፣ ዩሪክ አሲድ (uric acid) ፣ ሲስቲን (cystine) ሊሰሩ ይችላሉ።

የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው በአንድ ኩላሊት በኩል ይታያል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሁለቱም ኩላሊት ሊኖር ይችላል።

More stories

የአፍ ምሬት ከምን ይመጣል?

May 20, 2025

የጨጓራ ካንሰር | Gastric cancer

June 23, 2024

የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው?

May 24, 2024

ለሳይንቲስቶችን ግራ የሆነው በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት

November 3, 2024

ለኩላሊት ጠጠር የሚያጋልጡን ነገሮችስ?

ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ እድላችን የሚወሰነው ሽንት በተሰራበት (composition) ለምሳሌ በካልሼየም ኦግዛሌት የተሰራ ጠጠር ከሆነ በሽንት ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛ መጠን ካልሺየም እና ኦግዛሌት ሲኖር እንዲሁም ዝቅተኛ ካልሽየም እና ፖታሺየም መውሰድ እና ፈሳሽ ነገር ያላቸው ምግቦች አለማዘውተር እንዲሁም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከስኳር የተሰሩ ጣፋጭ መጠጦች ተጋላጭነተን ይጨምረዋል ተብሎ ይታሰባል።

ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች ለምሳሌ አንድ ሰው ከዚህ በፊት የኩላሊት ጠጠር ከነበረበት ድጋሚ የመመለስ እድል ሊኖረው ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ በዘር (በቤተሰብ) ወስጥ ጠጠር ያለበት ካለ ፣ በተደጋጋሚ የላይኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ተጠቂ መሆን ፣ መድሀኒቶች ለምሳሌ Idinavir, Acyclovir, Sulfadiazine፣ መድሀኒቶችን ከሚገባው መጠን በላይ መውሰድ፣ ከመጠን በላይ ውፍረት፣ ከመጠን በላይ በፕሮቲን እና Vitamin C የበለፀጉ ምግቦች መመገብ ፣ ከከመጠን በላይ የሰውነት እንቅስቃሴ ለምሳሌ የማራቶን ሯጮች ፣ ደም ግፊት ፣ ስኳር ፣ ሪህ ችግር ያለባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምልክቶቹስ?

– በአብዛኛው ከ20-60 ደቂቃ ሄድ መጣ የሚል ህመም በጎናችን አካባቢ ሊሰማን ይችላል። ህመሙ በጣም ሀይለኛ ውጋት ፣ ቁርጠት ስለሆነ ህመምተኛው የመንቆራጠጥ ነገር ሊያሳይ ይችላል።

አንዳንዴም ህመሙ እስከ ሽንት ፌኛ አካባቢ ሊደርስ ይችላል። ይህም አንደ ጠጠሩ ያለበት ቦታ ይወሰናል። ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም ወደቀይነት (ደም) መቀላቀል ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ሽንት ማጥ ፣ ሽንት ማጣደፍ ሊኖር ይችላል።

ምርምራዎቹስ?

– ከላይ የጠቀስኳቸውን ምልክቶች በምናይበት ግዜ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብናል። የጤና ባለሙያውም እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ ምርመራዎችን ለምሳሌ የሽንት ምርመራ ፣ የሆድ አልትራሳውንድ ፣ የሆድ x ray ፣ የሆድ ሲቲ ስካን ፣ ሊያዝልን ይችላል

ነፍሰ ጡር እናት ላይ ምርመራዎችን ስናዝ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ከx-ray ፣ እና ሲቲ ስካን የሚወጣው ጨረር በተለይ ፅንሱን ሊጎዳው ስለሚችል ነው። ስለዚህ በዚህ ጊዜ አልትራሳውንድ ተመራጭ ይሆናል።

የሚያመጣውስ ችግር?

-የኩላሊት ጠጠር ካልታከመ ለኢንፌክሽን ፣ ደጋሚ ተመልሶ የመምጣት ችግር (recurrence) ፣ የሽንት ቱቦ መዘጋት ፣ ኩላሊትን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እስከማድረስ ሊደርስ ይችላል።

ህክምናውስ?

– አመጋገባችንን ማስተካከል

– ጠጠሩን ያመጣብን ችግር ከታወቀ ማከም

– የህመም ስሜት ላላቸው ታካሚዎች እንደ አስፈላጊነቱ የህመም ማስታገሻ ሊሰጥ ይችላል።

– ማንኛውም የኩላሊት ጠጠር በቀዶ ጥገና ይወጣል ማለት አይደለም። ይህም የሚወሰነው እነደ ጠጠሩ መጠን ሲሆን የጠጠሩ መጠን እስከ 10 ሚሊ ሜትር ከሆነ በሽንት እንዲወጣ ነው የሚመከረው። በዚህ ጊዜ ታካሚው ዉሀ በብዛት እንዲጠጣ ይመከራል መጠናቸው ከ10 ሚሊሜትር በላይ ከሆነ የመውጣት እድላቸው ጠባብ ስለሆነ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ሊጠበቅን ይችላል። ለምሳሌ በድምፅ እና በጨረር በመታገዝ ጠጠሩ እንዲሰባበር በማድረግ ከዛም ውሀ በመጠጠት በሽንት እንዲወጣ ይደረጋል አንዳንድ ጊዜም በቀዶ ጥገና መውጣት ሊያስፈልግ ይችላል።

የህክምና አማራጮቹ የሚወሰኑት በባለሙያው ስለሆነ ከባለሙያ የሚሰጡንን ምክሮች ማክበር ተገቢ ነው።

NB. ንፁህ ውሀ በብዛት መጠጣት ተነገሮ ከማያልቁት ጥቅሞች አነዱ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ባሉበት ተቀምጠው ጉዳት እንዳያስከትሉ እና ለማስወገድ እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ ውሀ የመጠጣት ልምዳችንን ብናዳብር መልካም ነው።

ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ via አዲስ አድማስ

reaction
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በራያ አዘቦ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት ሰባት ሰዎች ተገደሉ፤ የትግራይ ሃይሎች አጻፋ ጥቃት ከፍተዋል
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ – ብድርና ዋስትና
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ENTERTAINMENT

“ኢትዮጵያን ትልቅ አገር ናት፤ ኃላፊነቱም ከባድ ነው ” የቁንጅና ንግስት ሀሴት ደረጄ

June 3, 2025
Reaction

ልብ ሊሉት የሚገባ በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት? ኪንታሮት ካልታከመ ጣጣው?

May 28, 2025
Reaction

በተለይ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች

May 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2