Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News2  ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው
News2

ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው

Ethioreview newsEthioreview news—July 3, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ከተማዋ ድንዛዜ የሰፈነባት፣ ጎስት ታውን (ghost town) ትመስል ነበር፤ ባጃጆች አንድ ሰው ሲያዩ ሥጋ እንዳየ አሞራ ነው ሰው የሚከብ ቡት፤ ወደ ዘጌ ደሴቶች ለሚደረገው ጣናን አቋርጦ የመሄድ ጉዞ ቢዚ ሆነው ይውሉ የነበሩት ጀልባዎች አሁን ላይ የውሃውን ዳርቻ በሙሉ ሸፍነውት የሥራ ማቆም ዓድማ የመቱ ነው የሚመስለው፤ ወደ አዲስ አበባ ስመለስ አውሮጵላኑ ሞልቶ የነበረ ቢሆንም ከተሳፋሪ ውስጥ የነበሩት የውጭ ዜጎች ሁለት ብቻ ነበሩ”

  • እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርም ከዘርፉ ይገኝ ነበር

የአማራ ክልል ቱሪዝም በግጭቱ ምክንያት ሥራ ለማቆም መቃረቡን የክልሉ የባህልና የቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ’

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዐማራ ክልልን ይጎበኛሉ ተብለው ከታቀዱት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር የመጡት 20 በመቶ ብቻ መኾናቸውን የገለጸው የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የክልሉ ቱሪዝም በእጅጉ በመዳከሙ ሥራ ለማቆም መቃረቡን አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ ትናንት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልሉ ተለዋዋጭ ገጽታ እያሳየ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት፣ “ዘርፉን ጨርሶ ለማስቆም እየተቃረበ ነው፤” ብለዋል፡፡

More stories

ጓደኛቸውን ገድለው  ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው የተሰወሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

May 21, 2024

የብሪክስ ፕላስ የመረጃና እና የባህል ሚዲያ ማዕከል ተመሰረተ

October 15, 2024

” የሎንግ ኦነግ ሸኔን መክዳት ከዜና በላይ ነው” – የሸኔ የሎጂስቲክ መረጃ መንግስት እጅ ገባ

February 18, 2024

“የቴህራን የአየር ክልል በኛ ቁጥጥር ስር ሆኗል” እስራኤል

June 16, 2025

በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችም፣ በግጭቱ ሳቢያ ከሥራ ገበታ ውጭ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡ (VOA)

ጥር 7 2016 የታተመው የጀርመን ድምጽ ዘገባ ችግሩ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ዶ/ር አየለ አናውጤ ጠቅሶ ዘግቦ መዘገቡ ይታወሳል። በአማራ ክልል በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ ክስተቶች የክልሉ የቱሪዝም እንቅስቃሴ በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ነዋሪዎችና በክልሉ ተደጋጋሚ ጦርነት ከመከሰቱ ቀደም ብሎ በ2010 ዓ.ም 210 ሺህ የወጪ ቱሪስች አማራ ክልልን የጎበኙት መሆኑ ተጠቅሷል ።

በክልሉ በነበሩና ባሉ ችግሮች ምክንያት በ2016 ዓ.ም ግማሽ ዓመት ክልሉን የጎበኙ የውጪ ጎብኝዎች ቁጥር ከ3ሺህ 500 ብዙም እንደማይበልጡ ጽ/ቤቱ አመልክቷል። ከዘርፉ የተገኘው ገቢም በእጅጉ ቀንሷል ተብሏል።

በዓለም ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ በሽታ ምክንት ተጎድቶ የነበረው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያገግማል ተብሎ ሲጠበቅ እንደገና በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ቱሪዝሙን ከድጥ ወደ ማጡ ከትቶት ቆይቷል፣ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአማራ ክልል የተፈጠረው የሰላም እጦት የባሰ ቱሪዝሙንና በአስጎብኝነት የተሰማሩ ወጣቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደጎዳ አንድ በጎንደር ከተማ በአስጎብኝነት የተሰማሩ ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

ድምፃቸው እንዲቀየር የፈለጉ የላሊበላ ከተማ ነዋሪና አስጎብኝም በክልሉ የተከሰቱ ተደጋጋሚ ችግሮች በቱሪዝም እንዳስትሪው ላይ የፈጠሩትን ጫና አስረድተዋል፡፡ ለውጪ ጎብኝዎችን በተለያየ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አስጎብኝዎች ያለሥራ መቀመጣቸውን ደግሞ አንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ነግሮናል፡፡

“… አሁን ቱሪስት የለም፣ ላሊበላ ሲከበር ቱሪስቶቹ ከላሊበላ ወደ ባህር ዳር፣ ከላሊበላ ወደ ጎንደር ይመጡ ነበር። መንገዱ፣ የሰላሙ ሁኔታ ያን አላደረገም፣ አሁን ጥምቀት እየመጣ ነው፣ ግን እንቅስቃሴ የለም፣ ቤት ቁጭ ብለን ነው ያለነው፣ ያለው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የሞተ ነው፣ የምንሰጠው አገልግሎት ቱሪስቱን ወደ ገዳማት መውሰድና መመለስ፣ እንግዶቹን ከአየር ማረፊያ መቀበል፣ ወደ ቱሪስት መዳራሻ መውስድ፣ ባለው ሁኔታ ግን አሁን ቱሪስትም አይመጣም ስራችንም ቆሟል፡፡ ቱሪስቶችን ወደ ጣና ገዳማት የሚወስዱ ወደ 150 ጀልባዎች ነበሩ፣ ወደ 80 ለቱሪዝም አገልግሎት የተዘጋጁ ተሸከርካሪዎች ነበሩ ሌሎችም፣ ይህ ሁሉ ሥራ አሁን አቁመዋል” ብለዋል።

“ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመግባታችን በፊት የነበረው የቱሪስት ቁጥር ካለው እምቅ ሀብት አኳያ ዝቅተኛ ነው ቢባልም ጥሩ የሚባል ነበር፣ ከጦርነቱ በኋላ ባሉት ጊዜዎች ግን ቁጥሩ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ ነው የመጣው፣ ከጦርነቱ በፊት በዓመት እስከ 270ሺህ የውጪ ቱሪስት አማራ ክልልን  ይጎበኝ ነበር፣ እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርም ከዘርፉ ይገኝ ነበር፣ ወደ 2016 ዓ ም ስንመጣ በ2016 ዓም ግማሽ ዓመት  84ሺህ የዉጪ ጎብኚ ወደ ክልሉ ይመጣል ተብሎ ታቅዶ ነበር፣ ግን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ባለፉት 6 ወራት 10ሺህ 500 ያህል ብቻ ናቸው ወደ ክልሉ የመጡ የውጪ አገር ቱሪስቶች፡፡ በገቢ ደረጃ 238 ሚሊዮን ብር ነበር በግማሽ ዓመቱ የታቀደው፣ በግማሽ ዓመቱ ከውጪ አገር ጎብኝዎች የተገኘው ገቢ ግን ከ40 ሚሊዮን ብር  የበለጠ አይደለም” ብለዋል፡፡  

እንደ ዶ/ር አየለ ባለፉት 6 ወራት 11 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ጎብኝዎች የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ታቅዶ የነበረ ሲሆን 4 ሚሊዮን ያህል የአገር ውስጥ ጎብኝዎች ወደ ቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች መድረሳቸውን አመልክተዋል፡፡ ከአገር ውስጥ ጎብኝዎች በ6 ወሩ ወደ 8 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆን አፈፃፀሙ ግን 1.6 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ከጦርነቱ በፊት ከአገር ውስጥ ጎብኝዎች ብቻ በዓመት እስከ 5 ቢሊዮን ብር ይሰበሰብ እንደነበርም ኃላፊው በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

በርካታ ወጣቶች በአስጎብኝነትና ተያያዥ ሥራዎች ተሰማርተው እንደነበር ኃላፊው አመልክተው መልሶ ለማደራጀት እንቅስቃሴ እየተደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ ተፈጠረው የሰላም እጦት ስራዎችን እንዳናከናውን አድርጎናል ብለዋል፡፡

“በማህበር ተደራጅተው፣ አንዳንዶቹ የማህበረሰብ ኢኮ ቱሪዝም አቋቁመው፣ ሎጂዎችንም ገንብተው፣ እየሰሩ የነበሩ ነበሩ በብዙ ቦታዎች በጎብኝ እጦት ምክንያት ተበትነው ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ አንዳንዶቹ የሚሰሩባቸው ኢኮ-ሎጂዎች በጦርነት ምክንያት ፈርሶባቸው ሥራ ያቆሙ ናቸው፣ አንዳንዶቹ እስከ ስደት ደረጃ የደረሱ እንዳሉ መረጃዎች አሉን፡፡”

ከወራት በፊት ከአውሮጳ ዘመዶቿን ለመጠየቅ በባሕር ዳር አካባቢ ጉብኝት አድርጋ የነበረ አንዲት የክልሉ ነዋሪን በመጥቀስ የጎልጉል መረጃ አቀባይ እንዳለው ግለሰቧ ባሕር ዳር ስትሔድ ያየችው ሁሉ አስደንግጧታል። ከቦሌ አውሮጵላን ተሳፍራ ስትሄድ ለወትሮው ባንድ በረራ ውስጥ እስከ ግማሽ ያህል የውጭ አገር ሰዎች ይሳፈሩ ነበር፤ እሷ በሄደችበት ጊዜ ግን አንድም የውጪ ዜጋ ተሳፋሪ አላየችም።

እዚያ በቆየችበት ጊዜም የተመለከተችውን ስትናገር፤ “ከተማዋ ድንዛዜ የሰፈነባት፣ ጎስት ታውን (ghost town) ትመስል ነበር፤ ባጃጆች አንድ ሰው ሲያዩ ሥጋ እንዳየ አሞራ ነው ሰው የሚከብ ቡት፤ ወደ ዘጌ ደሴቶች ለሚደረገው ጣናን አቋርጦ የመሄድ ጉዞ ቢዚ ሆነው ይውሉ የነበሩት ጀልባዎች አሁን ላይ የውሃውን ዳርቻ በሙሉ ሸፍነውት የሥራ ማቆም ዓድማ የመቱ ነው የሚመስለው፤ ወደ አዲስ አበባ ስመለስ አውሮጵላኑ ሞልቶ የነበረ ቢሆንም ከተሳፋሪ ውስጥ የነበሩት የውጭ ዜጎች ሁለት ብቻ ነበሩ” በማለት ትዝብቷን አጋርታለች። ስትቀጥልም “ይህንን ያየሁት ኅዳር እና ታኅሣሥ አካባቢ ነበር፤ ያኔ ለጓደኞቼ የነገርኳቸው አማራ ክልል ቱሪዝም ይቆማል ብዬ ነበር፤ ዛሬ ይህንን እንደ ትንቢት ተፈጽሞ ስሰማ ምንም አልደነቀኝም” ብላለች።  

ራሱን ፋኖ ብሎ በሚጠራው ብረት ባነሳ ኃይልና በመንግሥት መካከል የተከሰተው ግጭት በጦርነትና በትህነግ ወረራ ወድሞ የነበረውን ክልል ሳያገግም አከርካሪውን ብሎ ያሽመደመደው ሆኗል። የትህነግ ዘረፋ ክልሉን 14 ዓመት ወደኋላ የወሰደው ሲሆን እስካሁን ቀጥሎ ያለው መሪና ዓላማ ዓልባ ግጭት እጅግ ብዙ ዓመታት ክልሉን ወደኋላ እየወሰደው መሆኑ በገሃድ የሚታይ ሆኗል። ጉዳዩ በቶሎ ካልተቋጨ በአማራና በሌሎች ክልሎች መካከል የሚኖረው ሁሉን ዓቀፍ ልዩነት “ተበደልን” በሚል ሰበብ እንደገና ክልሉን ለማያባራ መከራ ውስጥ እንዳያስገባው አስተያየት ሰጪዎች ሥጋታቸውን ይናገራሉ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

home
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ልክ እንደ ኬንያ ጀግኖች አዲሶቹን መናፈሻዎች አቃጥሉ፣ ፓርላማውን አውድሙ” ጥሪ ለኢትዮጵያዊያን
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ – ከ3 ሺህ 700 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2