Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  TIPS 1  ትህነግና ያወዛገበው ጉባኤ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት? መቀዳደም!
TIPS 1

ትህነግና ያወዛገበው ጉባኤ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት? መቀዳደም!

Ethioreview newsEthioreview news—August 9, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

መቀዳደም ሊኖር እንደሚችል ምልክት አለ። ቀድሞ መበላላት እንዳይፈጸም ስጋታቸውን የሚገልጹ በርክተዋል። ሰክነው ምክር የሚሰጡና የሚያስጠነቅቁ ጥቂት አይደሉም። የትግራይ ህዝብ ዳግም ጦርነትና ችግር የሚሸከምበት ትከሻ እንደሌለው የሚገልጹ ችግር ተፈጥሯል የሚሉት ወገኖች በንግግር ችግራቸውን እንዲፈቱ ወትውተዋል። ሰሚ የለም። የስልጣን ሽኩቻው ወደ እርስ በርስ ግጭት እንዳያመራ ፍርሃቱ ባየለበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ወገኖች ግፋ በለው እያሉ ነው።

«በውስጣችንም ቢሆን በተካሄደ ውይይት ጉባኤ አይካሄድ ያለ የለም። ሐሳብ የሚንሸራሸርበት ጉባኤ ይሁን፤ የተደረገውን ዝግጅት ደግሞ ምን ይመስላል ብለን እንየው። እንዲህ ዓይነት ጉባኤ ሰው የማይድንበት፤ ወደ ቀውስ ያስገባን ሃይል ተመልሶ ወደ ሥልጣን እርካብ የሚቆናጠጥበት፤ ሌላውን የሚቀጠቅጥበት መድረክ ለመፍጠር ነው።“ አቶ ጌታቸው ረዳ

“ሊካሄድ በታቀደው ጉባኤ አልሳተፍም ” ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ዓርብ ነሀሴ 3/2016 ዓ.ም ለህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ተኽለብርሃን ኣርኣያ በፃፉት ደብዳቤ በጉባኤው እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል። አቶ ጌታቸው በደብዳቤያቸው ” ህወሓት መዳን የሚችለው አባላቱና አመራሩ በሚያካሂዱት ጤናማ እንቅሰቃሴ ነው ” ብለዋል።

የጀርመን ድምጽ በትጅነግ ጉያ ውስጥ የተፈጠረውን ይህን አሳሳቢ ችግር ጦርነት ያማዝዝ ይሆን ሲል ሰፊ ዘገባ አርቧል። ከስር ቀርቧል።

More stories

ዘመነ ካሤ ቀድሞ ወደ ድርድር ?  ሰባት የፋኖ ቡድኖች ያሉበት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ

July 22, 2024

በኦሮሚያ የሰላም ውይይት ፍንጭ ተሰማ፤ “ጃል መሮ እጅ ካልሰጡ ከጃል ሰኚና ከመንግስት አያመልጡም”

October 11, 2024

ኢምሬት ከፈረንሳይ ጋር ያሰረችውን የ 20 ቢሊዮን ጦር መሳሪያ ግዢ አቋረጠች

August 31, 2024

ኢትዮጵያ እንዲህ ተዘርፋለች፤ ” አሁንም ሌቦች አሉ የመንግስት ሌብነት ማለት ግን ይህ ነው”

July 7, 2024

ህወሓት በተለያዩ ወቅቶች ያጋጠሙት ቀውሶች

በ1969 ሕወሐት ገና በለጋ ዕድሜው እንዳለ በውስጥ ቀውስ መታመሱ ትግሉን መሄድ በሚገባው አቅጣጫና ፍጥነት እንዳይሄድ እግር ከወርች ያሰረውን ገመድ ለመበጠስና በተሻለ ፖለቲካዊ ቁመና ለመሄድ እንደ አንድ መፍትሄ የወሰደው ሰፊውን የድርጅቱን አባላት በማወያየትና ሐሳብን በሐሳብ በማሸነፍ እንደነበር ነባር የድርጅቱ አባላት በተለያዩ ጊዜያት የከተቧቸው ድርሳናት ያመላክታሉ። 
በ1977ም ድርጅቱ አጋጠሙት ከሚባሉ ቀውሶች ሌላኛው የሚጠቀስበት ዓመት ነበር። በወቅቱ የሚመራበት ርዕዮተዓለም እና ወታደራዊ እንቅስቃሴው አቅጣጭ ጠፍቶበት የዕውር ድንብሩን የተጓዘበት ሁኔታ መፈጠሩንም እንዲሁ ነባር የድርጅቱ አባላት ይገልጻሉ። በወቅቱ እነ ዶክተር አረጋዊ በርኸ እና ኢንጅነር ግደይ ዘርአጽዮን የተባሉ ከፍተኛ የድርጅቱ አባላት ከድርጅቱ እንዲሰናበቱበት ያደረገ ጉባኤ ተካሂዶ ድርጅቱ አሁንም ወደ ተሻለ መስመርና አቅጣጫ እንደገባ የድርጅቱ ድርሳናትና ነባር የድርጅቱ አባላት ይናገራሉ። 
ሌላው ህወሓት ያጋጠመው ትልቅ ተብለው ከሚጠቀሱ ቀውሶች ደግሞ ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ በ1993 ዓም የተከሰተው ነው። በዚህ ጊዜም የነበሩ ችግሮቼ ያላቸውን ገምግሞ እነ አቶ ገብሩ አስራት፣ አቶ ስዬ አብርሃን ጨምሮ በርካታ የድርጅቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር አባላትንና ተራ አባላትን በማግለል ድርጅቱ እየተንገዳገደ አሁን ያለበት ደረጃ ደርሷል። 

የሕወሓት ምርጫና መዘዙ
2012 በዓለማችን በነበረው የኮረና ተሐዋሲ ስርጭት ምክንያት የፌደራል መንግሥት ምርጫ ሲያራዝም በአንድ ሀገርና ሰንደቅ አላማ ሥር የሚገኘው ህወሓት ግን በክልሉ ምርጫ አካሂዳለሁ በማለት የራሱን ምርጫ ቦርድ አቋቁሞ ምርጫ በመካሄዱ የሚልዮኖችን ሕይወት የፈጀ፣ ያፈናቀለ፤ በቢልዮን ብር የሚገመት ንብረትን ያወደመ ጦርነት እንዲካሄድ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።

የጉባኤ ዝግጅትና ውዝግቡ
ጦርነቱ የሚበላውን በልቶ የተረፉ መሪዎችን በማጨባበጥ ለጊዜው ቢቆምም አሁንም ህወሐት በምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ዕውቅና ሳያገኝ ጉባኤውን አካሂዳለሁ ማለቱን እና በምርጫ ቦርድ እንደ አዲስ ፓርቲ እንዲመሰረት የቀረበለትን ጥያቄ ባለመቀበሉ በፓርቲው ውስጥና ከፌደራል መንግሥት ጋር ድሮውንም በቋፍ ላይ የነበረው ግኑኝነት ወደ ለየለት ጦርነት እንዳያመራ ብዙዎችን አስግቷል። 


ሕወሓት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ በ50 ዓመት ታሪኩ አጋጥሞት የማያውቅ ቀውስእንዳጋጠመው ገልጿል። የድርጅቱ የሕዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ ለDW በሰጡት አስተያየት ፓርቲው ወራት በፈጀ ስብሰባ የውስጥ ችግሩን ፈትሾ፤ ሂስና ግለሂስ በማካሄድ አጠቃላይ ችግሩን ለመፍታት ጉባኤ ለማካሄድ መወሰኑን ገልጸዋል። ለዚህም ሦስት የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ያሉበት አዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ የስብሰባው መሰናዶም ዴሞክራሲያዊና ትክክለኛነቱ ተገምግሞ የጉባኤ ዝግጅት መካሄዱን አክለዋል። ብቸኛ የድርጅቱ ችግሮች የመፍቻ ቁልፍ ጉባኤ ማካሄድ መሆኑን በማከል። 

በዚህ ዝግጅት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሕዝብ ግኑኝነት ሃላፊን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ባይሳካም የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርና የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ግን ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ተከታዩን ብለዋል። 

«በውስጣችንም ቢሆን በተካሄደ ውይይት ጉባኤ አይካሄድ ያለ የለም። ሐሳብ የሚንሸራሸርበት ጉባኤ ይሁን፤ የተደረገውን ዝግጅት ደግሞ ምን ይመስላል ብለን እንየው።  አንድ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ጉባኤ ሰው የማይድንበት፤ ወደ ቀውስ ያስገባን ሃይል ተመልሶ ወደ ሥልጣን እርካብ የሚቆናጠጥበት፤ ሌላውን የሚቀጠቅጥበት መድረክ ለመፍጠር ነው።“ 

የቀድሞው የድርጅቱ ነባር ከፍተኛ የአመራር አባልና የቀድሞው የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ተከታዩን ብለው ነበር። 
«የችግሩ መንስኤ ውስጣዊ እንጂ ውጫዊ አደለም። የቆየ ችግር አለ፤ ይህም የሥርዓት ችግር ነው። አመራሩ ማዕከሉን ጥቅምና ሥልጣን አድርጓል። በድርጅቱ ውስጥ በጉልህ የሚታይ ሁለት የድር መተሳሰር ተፈጥሯል። ይህ ነው ሁሉንም ነገር ያበላሸው።» ይላሉ አቶ ገብሩ አስራት። 
በሕወሓት ውስጥ በድርጅቱ ጽሕፈት ቤት እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ቡድን ተቧድነው በድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መካከል በማሕበራዊ መገናኛ ብዙኀን ሠራዊቶቻቸው ጭምር ከፍተኛ የሆነ የስም መጠፋፋትና ጥልልፍ እየተስተዋለ ይገኛል። ይህም የርዕዮተ ዓለም ልዩነት፣ የፖሊሲና የስትራተጂ ልዩነት ያመጣው ጤናማ የውስጥ ፖለቲካዊ ትግል ሳይሆን ለወንበር የሚደረግ የዝሆኖች ፍትግያ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ይገልጻሉ። የሕወሓት ጽሕፈትቤት ሃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ ግን ይህን አይቀበሉም። 

የህወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን ተቃውሞ
አቶ አማኑኤል የድርጅቱ ማዕከላይ ኮሚቴና ሰፊው አባላቱ የተሳተፉበት ዴሞክራሲያዊ የጉባኤ ዝግጅት መካሄዱን ቢገልጹም የድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽን ግን አካሄዱ ዴሞክራሲያዊ አይደለም በማለት ሦስት አባላቱን ከዝግጅት ኮሚቴው እንደሳበ ገልጿል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አቶ ተክለብርሃን አርአያ በቅርቡ ለክልሉ የመገናኛ ብዙሃን ከተናግሩት ይህ ይገኝበታል። 
«ግልጽ የሆነ መርሐግብር ይቀመጥ ተብሎ ነበር። እስከ አሁን ግልጽ የሆነ መርሐ ግብር አልተቀመጠም። በጉባኤው ዝግጅት የወከልናቸው አባሎቻችን እየተቃጠሉም ቢሆን ሲታገሉ ቆይተዋል። እኛ የቁጥጥር ኮሚሽንም ይህ ነው የሚባል የዝግጅት መርሐ ግብር የለንም። መርሐ ግብሩን አምጡ እንላቸዋለን ነገ ከነገ ወድያ እያሉ ይጨቃጨቃሉ።» 

ሕወሓትና የምርጫቦርድ ፍጥጫና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ
ሕወሓት ከምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ዕውቅና ሳያገኝ ጉባኤ አካሂዳለሁ፤ እንደ አዲስ ተመዝገቡ የሚል የምርጫ ቦርድን ሀሳብ አልቀበልም ማለቱ በውስጥ ሽኩቻ ብቻ የሚያበቃ ቢሆን በቀላሉ የሚታለፋ ሊሆን ይችል ነበር የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች ወደፊት ከሚካሄደው ምርጫና መንግሥት የመሆን አካሄድ ጋር ተያይዞ ግን ከፌደራል መንግሥት ጋር የሚያጋጭ ሊሆን እንደሚችል ያክላሉ። የተሰጋውም አልቀረ፤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በቅርቡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው የምክክር መድረክ ጉዳዩ ተነስቶ ተከታዩን ብለዋል።  
 
«ከዚህ ቀደም ምርጫ ቦርድ ምርጫ አራዝማለሁ ሲል ብዙዎቻችን ስንስማማ TPLF አልስማም ብሎ የገባንበት ቀውስ ይታወሳል። ምን ያክል ሰው እንደወደመ ምን ያክል ሐብት እንደወደመ መገመት ትችላላችሁ።  ያ የወደመ ሐብትና የወደመ የሰው ሕይወት በትክክል ሳይገመገም እንዴት ጠፋ ሳይባል ሌላ ጥፋት ማምጣት ጥሩ አደለም። ሕዝብ ይጎዳል። እኔ ብፈልግም ባልፈልግም ዋጋ የለውም። ምርጫ ቦርድ ካልተቀበለው TPLFን፤ ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ምርጫ ሊሳተፍ አይችልም፤ መንግሥት ሊሆን አይችልም። ምን ማለት ነው? ተመልሰን ደግሞ ጦርነት እንገባለን ማለት ነው።» 
ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አባባል ብዙ ትችቶችን አስተናግዷል። አንድ ህወሐት የምርጫ ቦርድን ሕግ አላከበረም ተብሎ ወደ ጦርነት እንገባለን ማለት «አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ» እንዲሉ በፓርቲው ጥፋት የትግራይ ሕዝብ ዳግም በጦርነት የሚጎዳበት ምክንያት አይኖርም በሚልም ብዙ ተቃዎሞ ደርሶታል። የሕወሐት የሕዝብ ግኑኝነት ሐላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋም ይህን ይጋራሉ። 
 
«አንድ ፓርቲ ችግሮቹን ለመፍታት አንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ስብሰባ ስላደረገ ጦርነት ሊታወጅበት አይችልም። ማለት ያደረገው እኮ ስብሰባ ነው።  ዓመቱን ሙሉ ወራትን የወሰዱ ስብሰባዎችን እናደርግ ነበር። ምንም የተፈጠረ ነገር የለም። ጉባኤ ከዛ በላይ የሆነ ስብሰባ አይደለም። ከፍተኛ ሥልጣን ስላለው በድርጅቱ ላይ ድርጅቱ የሠራቸውን ሥራዎች የገመገማቸውን ውጤቶች የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ስብሰባ ከመሆኑ በስተቀር ምንም ነገር የለውም ። 
ሕጋዊ አይደለም ዕውቅና አንሰጠውም ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ ከምርጫ ቦርድ ጋር የሚያልቅ ነው። በጣም ቴክኒካልና ሕጋዊ የሆነ የአድሚኒስትሬሽን ጉዳይ ነው የሚሆነው። በዚህ ደረጃ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ፓርቲ ስብሰባ ስላደረገ ወደ ጦርነት ይገባል የሚል ጭራሽ ሊታሰብ አይችልም።» 

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስጋት
ሕወሓት በውስጡ እየተካሄደ ያለው ሽኩቻና ከፌደራል መንግሥት ጋር የፈጠረው አታካሮ ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይደርስ ብዙዎች የክልሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ይህ ያሰጋቸው ሦስት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ይህንኑ በመግለጽ ከሰጡት መግለጫ ተከታዩን ይገኝበታል። 

«ይህ ሃይል የትግራይ ሚድያ፣ ፖለቲካ፣ የጸጥታ መዋቅር፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ ኑሮ ሳይቀር የተቆጣጠረአፋኝ ሃይል ነው። ይህ ጸረ ሕዝብ ሃይል የራሱን ውስጣዊ መናጨት ወደ ሕዝቡ ለማስረግና በሕዝባችን አንድነት ስንጥቅ ለመፍጠር የሚሄደውን አካሄድ እንዳይበቃው በውስጥና በውጭ ያሉ ተጋጣሚዎቹ ላይ የሃይል ሚዛንን ለማግኘት ሲል ሕዝባችንን ጭዳ የሚያደርጉ የተለያዩ አደገኛ አካሄዶችን እየታዘብን ነው። ስለሆነም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖር ትግራዋይ በአንድነት ወግድ ሊለው ይገባል።» 

የተጠያቂነት ጉዳይ
በትግራይ የደረሱት የሰው ሕይወትና ንብረት ውድመት እንዲሁም አሁን ያሉት ሥር የሰደደ ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፈታት ያልቻሉት ተጠያቂነት ባለመስፈኑ እንደሆነ የክልሉ ነዋሪዎች በተለያዩ መድረኮች በምሬት ሲገልጹ ተደምጠዋል። የሕወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ በሰጡት መግለጫም የተጠያቂነት ጉዳይ ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ የድርጅቱ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ሲባል ኮሚቴ ተዋቅሮ ዋና ዋና አጥፊዎች የተባሉ መለየታቸውን በድርጅቱም ሆነ በጊዜያዊ አስተዳደሩ በኩል ቢገለጽም እስካሁን ተጠያቂነት አለመስፈኑ ግን ብዙዎችን አስቆጥቷል። ይህን አስመልክተን ላነሳንላቸው ጥያቄ አቶ አማኑኤል አሰፋ «ለሁሉም ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ችግሮቻችን መፍቻው ጉባኤ መካሄድ አለበት የምንለው ለዚሁ ነው» የሚል ምላሽ ሰጥተውናል። ጉባኤ ካልተካሄደ ተጠያቂነት አይሰፍንም እያሉ ነው? ለሚል ተከታይ ጥያቄያችንም፤ «የለም በድርጅቱ ውስጥ የጉድለቶቹ አተያይ የተለያየ መልክ ስላለው ጉባኤው ይዳኘን እያል ነው» ብለዋል። 
 
 «በጣም ጉባኤው አስፈላጊ የሆነው ችግሮቻችንን ለመፍታት እኛ አንድ አይደለንም ነው። ችግሮቻችንን የምናይበት መነጸር አንድ አይደለም። በአንድ ድርጅት ውስጥ ታቅፈን ይሄ ነው ችግሩ ለማለት ተቸግረናል። ስለዚህ ዝም ብለን እየተሳሳብን መኖር አለብን? እንዴት ይሆናል ? አይሆንም እኮ። የሚያስታርቀን አንድ አካል አለ፤ ሁላችንም ተጠሪ የሆንበት ጉባኤ የሚባል አካል አለ። ስለዚህ ማን እንደተሳሳተና ማን ትክክል እንደሆነ ይነግረናል።» 
በትግራይ ለተፈጸሙ ችግሮችና ላስከተሉት ጉዳት ተጠያቂነትን በተመለከተ በድርጅቱም ሆነ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ልዩነት ያለ አይመስልም። እስካሁን ባለው ሂደት ግን አንዱ ሌላኛውን ከመውቀስና ችግሮችን ከመዘርዘር የዘለለ ጠብ የሚል ተጠያቂነት አልሰፈነም። በቅርቡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የሣልሳይ ወያነ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉ፤ አሉ የተባሉ ችግሮችን የሚዘረዝሩት ባለሥልጣናቱ መሆናቸውን በማመልከት፤ ሥልጣን የያዙ ሰዎች ሐላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።  

«እኔን በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር አለ። በትግራይ ችግሮች ተዘርዝረው እየተነገሩ ያሉት ችግሮቹን እንዲፈቱ ሥልጣን በያዙ ሰዎች ነው። ሐላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል “ 
ሕወሓት በውስጡና ከፌደራል መንግሥት ጋር የገባውን እሰጥ አገባ እንደተባለው ተጠያቂነትን በሚያስከትል መልኩ ጉባኤ በማካሄድ ይፈታ ይሁን? ወይስ በተቃራኒ ይጓዝ ይሆን? ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። 

DW Amharic

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኢሳያስን ለማስወገድ የኤርትራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት መሠረቱ
AliExpress is set to enter Ethiopia
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2