Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  OPINION  በዲጂታል ዓለም ወረቀት ለምን ተወደደ?
OPINION

በዲጂታል ዓለም ወረቀት ለምን ተወደደ?

Ethioreview newsEthioreview news—October 9, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ብዙ ጋዜጦችና መጽሔቶች በወረቀት ዋጋ ውድነት ምክንያት ከገበያ ውጭ ሆነዋል። ፀሐፊዎች በወረቀት ዋጋ ውድነት ምክንያት መጽሐፍ ማሳተም እየቻሉ አይደለም። የጋዜጣና መጽሔት መሸጫ ዋጋ ሲጨመር አንባቢው ለመግዛት ይቸገራል። መጽሐፍ አሳትሞ ለመሸጥ ከመሸጫ ዋጋው ይልቅ የማሳተሚያ ዋጋው ሊበልጥ ይችላል።

ስለዚህ መጽሐፍ ማሳተም የሚችለው ባለሀብትና ባለሥልጣን ብቻ ነው ማለት ነው። ባለሀብት ደግሞ መጽሐፍ የሚጽፍበት ጊዜ የለውም። መጽሐፍ ለመጻፍ የሚያስችል ማህበራዊና ተፈጥሯዊ ዕይታ የለውም። ባለሥልጣንም ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ነክ ነገሮችን ካልሆነ በስተቀር ማህበራዊና ተፈጥሯዊ የሆኑ ዕይታዎችን የማየት ዕድሉ የተገደበ ነው።

የአብዛኛውን ሕዝብ ስሜት ሊገልጽ የሚችል የማህበረሰቡን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የሚያዩት፣ ተፈጥሮን በእግር እየተንቀሳቀሱ የሚመሰጡባት፣ ከአረቄ ቤት እስከ ባለኮከብ ሆቴል ያሉ ገጠመኞችን… የማየትና የመስማት ዕድል ያላቸው የድርሰት ተሰጥዖ ያላቸው ጥበበኞች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ገንዘብ የላቸውም። ስለዚህ አገሪቱ ሀሳብ አልባ ልትሆን ነው ማለት ነው። ሀሳብ ማለት የግድ ሳይንሳዊና ፖለቲካዊ ጽንሰ ሀሳብ ብቻ አይደለም። የሰዎች አዳዲስ ዕይታዎች፣ ፍልስፍናዎች፣ የሕይወት ውጣ ውረድ ገጠመኞች፣ የዘመን ትውስታዎች… የአንዱ ለአንዱ መዳረስና መተዋወቅ አለባቸው። እነዚህ ሰዎች ግን ድሃዎች ናቸውና ጽፈው ማሳተም አይችሉም። ማሳተም እንደማይችሉ ስለሚያውቁ የመጻፍ ወኔያቸውም ይቀዘቅዛል።

የጋዜጦችና መጽሔቶች አማራጭ አለመኖር ነገሮችን ሁሉ በግለሰቦች ስሜት ላይ ብቻ ለተመሰረተው ማህበራዊ ሚዲያ ያስረክባል። የተቋማዊ አሰራር ባህል ይበላሻል። ተጠያቂነትና ተቋማዊ ኃላፊነት ስለማይኖር አሉቧልታና ሀሰተኛ መረጃ ይበዛል። የንባብ ባህል ይጠፋል። ወጣቱ ትውልድ የማህበራዊ ገጾች ሰለባ ይሆናል። ማህበራዊ ገጾች ደግሞ በባህሪያቸው ጥድፊያ የሚበዛባቸው ናቸው። ረጃጅም ነገር ለማንበብ አያስችሉም። የገጽ መጠናቸው ውስን ስላልሆነ በስስት እየሮጡ ለማየት ያስገድዳሉ። በወጣትነት ዕድሜ ደግሞ ሁሉን ነገር ለማየት መጓጓት ያለ ነው። ስለዚህ ነገሮችን በጥልቀት የሚያይ ትውልድ አይፈጠርም ማለት ነው። በጥልቀት ማሰብ የሚቻለው ጠለቅ ያሉ ነገሮችን ማንበብ ሲቻል ነው። በጥልቅ የሚያስብና የሚያሰላስል ትውልድ አልተፈጠረም ማለት የተማረ አልባ አገር እናስረክባለን ማለት ነው።

More stories

“በነዉጥና በኃይል የበለፀገ ሀገር የለም”

May 2, 2023

ወያኔያዊ አማራነትን አማራ “አማራ ነኝ”

December 6, 2022

ሰውን “ሰው” የሚያደርገው ምንድነው? ከእኛ ይልቅ የጥንቶቹ ዘመናዊ ነበሩ

November 1, 2024

ወግ አጥባቂው የኦክላሆማ ሴናትር ማ’ናቸው?

October 6, 2022

የንባብ ባህልን ለማዳበር እንደ አብርሆት ቤተ መጽሐፍ አይነት ግዙፍና ማራኪ ቤተ መጽሐፍ ተገንብቷል። ቤተ መጽሐፉ ግን በቀደመው ዘመን የተጻፉ ብቻ የሚነበቡበት መሆን የለበትም። አዳዲስ መጻሕፍት፣ ጋዜጦችና መጽሔቶችም የሚገኙበት መሆን አለበት። የቀድሞዎችን ብቻ ለማንበብ ከሆነ ቤተ መጽሐፍ ሳይሆን ቤተ መዘክር ሆነ ማለት ነው። የኢንተርኔት መጠቀሚያ ብቻ መሆን የለበትም። እንደዚያ ያማረ፣ የሚመስጥ እና ፀጥ ያለ ግርማ ሞገስ ያለው ቤተ መጽሐፍ የኢንተርኔት መጠቀሚያ ብቻ ሊሆን አይገባም። ኢንተርኔት የትም ሆኖ መጠቀም ይቻላል።

አዳዲስ መጽሐፎች በብዛት ይታተሙ ዘንድ፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች አማራጭ የሚዲያ አይነቶች ይሆኑ ዘንድ፣ በአጠቃላይ የንባብ አብዮት ይፈጠር ዘንድ መንግሥት በወረቀትና የማተሚያ ግብዓቶች ላይ ያለውን ቀረጥ መላ ሊለው ይገባል። የንባብ ባህል ባልዳበረበት ማህበረሰብ ውስጥ ወረቀትና የማተሚያ ግብዓት እንደ ቅንጦት መታየት የለበትም፤ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

ብዙ ሰዎች ‹‹ዘመኑ የዲጂታል ነው›› ሲሉ ይሰማል። በተደጋጋሚ ስንለው እንደቆየነው የዲጂታሉ ዓለም እንኳን እንደ ኢትዮጵያ አይነት ታዳጊ አገር የሥልጣኔ ጫፍ ላይ ናቸው በሚባሉት አገራትም ብዙ የቴክኒክ ችግር ያጋጥመዋል። መረጃን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ የዲጂታሉ ዓለም ላይ ብቻ መንጠልጠል አስተማማኝ አይደለም። የሆነ ጊዜ፣ የሆነ ቀን ውድመት ሊያጋጥመው ይችላል። ቀላል፣ ምቹ እና ቀልጣፋነቱ አከራካሪ አይደለም። እሱ ላይ ብቻ መተማመን ግን አስተማማኝ አይሆንም፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ስናየው ደግሞ በአዲስ አበባ ደረጃ እና በወጣቶች ብቻ አይደለም መለካት ያለብን፤ በቦታም ሆነ በዕድሜ ምክንያት ኢንተርኔት የማይጠቀሙ አሉ። 600 ገጽ መጽሐፍ በኮምፒውተር ማንበብ ለወጣትም ቢሆን ለጤናም ተስማሚ አይደለም። የበይነ መረቡ ዓለም በባህሪው ለአጫጭር ነገሮች ነው። ለመዝናኛ ነገሮች ነው።

የሚገርመው እኮ ‹‹ከመምህሩ ደቀ መዘምሩ›› መሆናችን ነው። የበይነ መረቡን አማራጭ በፈጠሩት አገራት ወረቀት አልቀረም። መጻሕፍት፣ ጋዜጣና መጽሔቶች ይታተማሉ። በሠለጠኑት አገራት ወረቀት አልቀረም፤ ታዲያ እኛ ምን ስለሆነ ነው የወረቀትን ነገር እንዲህ እንደ ቀላል ያየነው? እውነት ይህን ያህል የዲጂታል ተጠቃሚ ሆነን ነው? አይመስለኝም፤ ሰነፎች ስለሆንን ነው።

‹‹አሜሪካን ፔፐር አሶሴሽን›› ባለፈው ዓመት ባወጣው ዝርዝር ሐተታ፤ ወረቀት በዚህ በዲጂታል ዘመን ተፈላጊነቱ እንደቀጠለ ነው። በተለይም ድምጽ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች እና ለዓይነ ሥውራን አሁንም አማራጩ ወረቀት ነው። ደረሰኝ የመሳሰሉት ሰነዶች ዛሬም በወረቀት ናቸው። በዲጂታል ያሉ አማራጮች ድንገተኛ ስረዛ (delete) እያጋጠማቸው ነው። ይህን የሚለው የዓለም ልዕለ ኃያሏ አሜሪካ ውስጥ ያለው ማህበር ነው። ውሎች ዛሬም እየተደረጉ ያሉት በወረቀት ነው። ከምንም በላይ ደግሞ ዓይነ ሥውራን እየተማሩ ያሉት ለመንካት በሚመቸው ወረቀት ነው። የዲጂታሉ ዓለም ለጊዜው ለእነርሱ ምቹ አይደለም።

የማህበሩ ሰነድ፤ 25 በመቶ የሚሆነው የአሜሪካ ገጠራማ ክፍል የብሮድ ባንድ ተጠቃሚ አይደለም ይላል። በዚህም ምክንያት ወረቀት በብዛት መመረትና መሰራጨት አለበት ብሎ ይመክራል። የጉግል ፈጣሪው ላውረንስ ኤድዋርድ ፔጅ አገር የሆነችው አሜሪካ እንዲህ ካለች፤ ታዲያ እኛ ማን ስለሆንን ነው ወረቀትን እንዲህ የናቅነው? 25 በመቶ የሚሆን ኢንተርኔት የማይጠቀም ሕዝብ አለኝ የምትለው አሜሪካ ወረቀት በብዛት ይሰራጭ ስትል፤ 80 ምናምን በመቶ አርሶና አርብቶ አደር ይዘን ወረቀትን እንደ ዋዛ ማየት ነበረብን?

በዲጂታል ዘመን ወረቀት መወደዱ ሊገርም ይችላል። አማራጭ ሲኖር፣ በብዙ መገልገያዎች ወረቀት ሲቀር፣ መርከስ እንጂ መወደድ አልነበረበትም። ምናልባት ግን ማምረቱ ላይ ትኩረት ስላልተሰጠ ይሆናል። መወደዱ ግን የሚያሳየው ተፈላጊነቱን ነው። ባደጉት አገራት ሳይቀር አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ነው።

ወደ አገራችን ዓውድ ስናመጣው ደግሞ ወረቀት አሁንም በጣም የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ነው። አባቶች በካፌዎች አካባቢ ሲቀመጡ በአጠገባቸው የሚያልፈው ሎተሪ የያዘ ወጣት ብቻ ይሆናል ማለት ነው። ጋዜጣና መጽሔት እያቀያየሩና እያማረጡ አያነቡም ማለት ነው። ወረቀት ለውል እና ለደረሰኝ ብቻ መሆን የለበትም። በተለይም ለንባብ ባህላችን መዳበር የግድ ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ለጊዜው የተሻለው መፍትሔ የወረቀትና የማተሚያ ግብዓቶች ላይ ማሻሻያ ማድረግ ነውና ይታሰብበት!

ዋለልኝ አየለ

 አዲስ ዘመን መስከረም 25/2017 ዓ.ም

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኔታንያሁ ሊባኖስ እንደ ጋዛ ልትፈራርስ እንደምትችል አስጠነቀቁ
በመስከረም ወር ብቻ ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና ከ90 ሚሊዮን ዶር በላይ ገቢ ተገኘ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
OPINION

እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

April 8, 2026
OPINION

ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

April 8, 2026
OPINION

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – የሃሰት ትርክ ዘመቻ በደቦ

March 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2