በወለጋ የተለያዩ ግንባሮች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መሪ ናቸው የተባሉትን ጨምሮ ለጊዜው ቁጥራቸው ይፋ ያልሆነ ታጣቂዎች መማረካቸው ተሰማ። በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መመለሳቸውን ተቤኒሻንጉል ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ምስልና ቪዲዮ አስደግፎ አስታወቀ።
በዳሬ ሰላም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራሮች ጋር ንግግር እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ኦፕሬሽኑ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያስታወቁት ክፍሎሽ እንዳሉት በሰሙሉ ወጊያ በተለይም ከትናንት በስቲያ የኦነግ ሸኔ አዋጊዎች ናቸው የተባሉ መማረካቸውን ተናግረዋል።
በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል በሚያደርጉት የተለያዩ ስያሜ ያላቸው ላይ ታቂዎች ላይ በተመሳሳይ ሙሉ ማጥቃትና ማጽዳት መጀመሩ ይፋ በተነገረበት ወቅት፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሰፊ ይዞታቸውን እያጡና እየተማረኩ መሆናቸው መንግስት በይፋ ባይገልጽም በአካባቢው ያሉ ምስክሮች አረጋግጠዋል።
“በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጠቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም ተመልሰዋል” ሲል ነው ቢሮው ይፋ ያደረገው።
በመኩሪያው ዚፋሃ እና በመኮነን ፋኖ በሚባሉ ግለሰቦች ሲመራ የነበረው የጉህዴን ታጣቂዎች ቡድን በውይይት የሰላም ስምምነት መቀበሉ ታውቋል። ውይይቱ ሰፊና ከፍተኛ ጥረት የተደረገበት እንደሆነ ተመልክቷል።
በማንዱራ ወረዳ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው ሲገቡ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች በገነተ ማሪያም ከተማ በመገኝት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋውያ፣ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭ በመቀበል ወደ ህብረተሰቡ መመለሳቸው የቀጠናውን ሰላም በዘላቂነት የተረጋጋ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል።
ተመላሾችን በተማሩበትና ፍላጎታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ለማሰማራት እንደሚሠራም ተናግረዋል።
በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ጫካ ውስጥ መቀመጫቸውን አድርገው በአዋሳኝ አካባቢዎች ስጋት ሲፈጥሩ የነበሩ ታጣቂዎች በውይይት መምጣቸው ለህብረተሰቡ ሰላም ዘላቂ መፍትሄ እንደሚሰጥም ነው የተገለጸው።
የሰላም ስምምነቱን ተግባረዊ ለማድረግና ወደ ሰላምና ልማት ለመግባት የሀገር ሽማግሌዎችና አመራሮች በተገኙበት ከሰላም ተመላሾች ጋር በጉሙዝ ብሄረሰብ ባህል መሠረት የእርቅ ስነ ስርዓት መካሄዱን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ ያመለክታል።
- የታሪካዊው ምክክር ፈተና እና ዕድል፤ አገራዊ ውህደት ወይስ የተራራቁ መስመሮች ስምምነት?VOE OPINION | ADDIS ABABA | July 31, 2026 – በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ በይፋ የተጀመረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ የሚገኘው አገር አቀፍ የውይይት መድረክ፣ በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ወሳኝና አዲስ ምዕራፍ ከፋች ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል። ለአገራቸው ቀና የሚያስቡ “ዳግማዊ አደዋ” እያሉትም ነው። ለዘመናት… Read more: የታሪካዊው ምክክር ፈተና እና ዕድል፤ አገራዊ ውህደት ወይስ የተራራቁ መስመሮች ስምምነት?
- የትግራይ የሰላም ኃይሎች አዛዥ የእነ ሞኖጆሪኖን ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስታወቁቪኦኢ ዜና | Addis Ababa | July 30, 2026 ራሱን የትግራይ የሰላም ኃይሎች ብሎ የሚጠራው ቡድን ትህነግን ከመቀሌ በማስወጣት ከተማዋን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን አጠቃላይ ዝግጅት ማጠናቀቁን የቡድኑ ወታደራዊ አዛዥ ለአዲስ ሪፖርተር ገለጹ። ይህ የተሰማው ከትህነግ መውደቅ በኋላ በትግራይ ስለሚከናወነው የመንግስት አወቃቀር ቅድም ዝግጅት መደረጉ ይፋ ከሆነ አንድ ቀን በኋላ ነው። በቀድሞ የትሕነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በወዲ… Read more: የትግራይ የሰላም ኃይሎች አዛዥ የእነ ሞኖጆሪኖን ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አስታወቁ
- Ethiopian Minister Says Egypt Should Pay for Nile Water UseVOE | Addis Ababa | July 30, 2026 – Ethiopia’s Minister of Water and Energy, Habtamu Itefa, has argued that Egypt should compensate Ethiopia for using the Nile’s waters, saying downstream countries have benefited for decades from Ethiopia’s natural resources without providing any financial return. Speaking in an interview with Fana Broadcasting Corporate (FBC), the… Read more: Ethiopian Minister Says Egypt Should Pay for Nile Water Use
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘBy VOE News ADDIS ABABA – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 የሥራ ዘመን ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ (9.1 ቢሊዮን ዶላር) ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ። ገቢው ከቀደሙት ዓመታት የላቀ መሆኑ ተመልክቷል። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱን የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ ዘንድሮ የተመዘገበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ… Read more: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ
- Egypt’s Losing Game over the GERD Has Never Been About Hydro-Technical EngineeringVOE NEWS | ADDIS ABABA | July 29, 2026 Egyptian politicians have repeated the same familiar refrain for years that Ethiopia is acting unilaterally over the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) and threatening the water security of downstream countries. The language has changed little. From official statements and diplomatic forums to state-aligned media campaigns, the accusation… Read more: Egypt’s Losing Game over the GERD Has Never Been About Hydro-Technical Engineering






