Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  ማሻሻያው ግልፅ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው ፓርቲዎችን ወደፖለቲካ ምህዳሩ ለማምጣት ያለመ ነው – ምርጫ ቦርድ
POLITICS

ማሻሻያው ግልፅ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው ፓርቲዎችን ወደፖለቲካ ምህዳሩ ለማምጣት ያለመ ነው – ምርጫ ቦርድ

Ethioreview newsEthioreview news—October 27, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ቦርዱ ባደረገው ማጣራት የጋምቤላ ህዝቦች  ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ አገው ለፍትህና ለዴሞክራሲ  ፓርቲ፣ አዲስ  ትውልድ ፓርቲ፣  የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ የሌላቸውን ሴት አባላት ቁጥር አለን በማለት የሃሰት ሪፖርት በማቅረብ  ገንዘብ  በመቀበል ህገ-ወጥ ተግባር በመፈጸማቸው የዕግድ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው አብራርተዋል።

የተሻሻለው የፓርቲዎች የምዝገባና ሰነድ ማሻሻያ ክፍያ ግልፅ ዓላማ ያላቸውን ፓርቲዎች ወደ ፖለቲካ ምህዳሩ ለማምጣት ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 67/4/ሀ-ለ/ መሰረት የምዝገባ ጥያቄ ያቀረበ ፖለቲካ ፓርቲ ወይም የመሰረታዊ ሰነዶች ማሻሻያ ያደረገ ፓርቲ ክፍያ እንደሚፈጽም ተቀምጧል።

በአንቀጽ 67/6/ ደግሞ የክፍያ መጠኑም በቦርዱ እንደሚወሰንም ተደንግጓል፡፡

በዚሁ መሰረት ሀገር አቀፍና ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት ለማግኘት 100 ብር እና ሙሉ እውቅና ለማግኘት 200 ብር ሲከፍሉ መቆየታቸውን የቦርዱ መረጃ ያሳያል።

የተመዘገቡ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን በጉባኤ አሻሽለው ሲያቀርቡ 30 ብር የአገልግሎት ክፍያ ይከፍሉ እንደነበርም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብእሸት አየለ በሰጡት ማብራሪያም ፥ ቦርዱ ፓርቲዎች የሚከፍሉት የገንዘብ መጠን ላይ ከጥቅምት 11/2017 ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆን ማሻሻያ ማድረጉን ገልጸዋል።

ቦርዱ ፖለቲካ ፓርቲዎች መከተል በሚገባቸው ሕግጋት፣ የፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ሌሎችም ሙያዊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

በዚሁ መሰረት የጊዜያዊ እውቅና ክፍያ ወደ 15 ሺህ ብር፣ የሙሉ እውቅና ክፍያ 30 ሺህ ብር እንዲሁም የሰነድ ማሻሻያ ክፍያው ወደ 5 ሺህ ብር ከፍ ማለቱንም ነው ያነሱት።

“አንድ አንድ ፓርቲዎች በፓርቲነት የሚመዘገቡት በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አሻራ ለማኖር ሳይሆን ተያያዥ ጥቅሞችን በማሰብ መሆኑን ተገንዝበናል” ሲሉም ገልጸዋል።

“በአግባቡ የሚታገሉ፣ ከድጎማ ፖለቲካ የተላቀቁ ፓርቲዎችን ማበረታታት ይገባል” ያሉት አቶ ውብእሸት ፥ ቦርዱ የክፍያ ማሻሻያ ያደረገው የፖለቲካ ምህዳሩን ለማጥበብ ሳይሆን ግልፅ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸውን ፓርቲዎች ወደ ፖለቲካ ምህዳሩ ለማምጣት እንደሆነም አብራርተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሴቶችን ተሳትፎ ለማበረታት በማሰብ ከቦርዱ የሚመደበውን ገንዘብ አላግባብ በወሰዱ ፓርቲዎች ላይ የእግድ እርምጃ መወሰዱንም አስረድተዋል።

ቦርዱ  በፓርቲዎች  ውስጥ የሚሳተፉ  ሴቶችን  እንዲሁም  አካል  ጉዳተኞችን ለማበረታታት  ለፓርቲዎች  ገንዘብ  የሚሰጥበት አሰራር መዘርጋቱን መግለጻቸው የዘገበው ኢዜአ ነው።  

ይሁን እንጂ  ለማበረታቻ  ከቦርዱ  የሚበጀተውን ገንዘብ አላግባብ ለመጠቀም የሌላቸውን አባላት ቁጥር አለን በማለት የሚያቀርቡ ፓርቲዎች መኖራቸው ተረጋግጧል ነው ያሉት።

ቦርዱ ባደረገው ማጣራት የጋምቤላ ህዝቦች  ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ አገው ለፍትህና ለዴሞክራሲ  ፓርቲ፣ አዲስ  ትውልድ ፓርቲ፣  የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ የሌላቸውን ሴት አባላት ቁጥር አለን በማለት የሃሰት ሪፖርት በማቅረብ  ገንዘብ  በመቀበል ህገ-ወጥ ተግባር በመፈጸማቸው የዕግድ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው አብራርተዋል።

እንደ ምክትል ሰብሳቢው ገለጻ ፥ ቦርዱ ፓርቲዎቹ ላይ እርምጃውን የወሰደው በህጉ መሰረት ፓርቲዎች  አሉ ስለተባሉት ሴት አባላት ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው ነውvua FBC

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ብልጽግና አባላቱን የሚቃኝበት የምዘና ነጥቦች አዘጋጀ፤ ለምርጫ መንደረደሪያ የሚሆኑትን 27 ቁልፍ ጉዳዮች ነቅሶ ትምህርትና ስልጠና ጀመረ
በሼክ መሐመድ ክስ በስጦታ የተሰጠ ሃብትን አስመልክቶ ለጊዜው የቀረበ ክስ የለም፤ “አብነት የተፈረደባቸው የወሰዱትን የከሳሽ የአክሲዮን ትርፍ እንዲመለሱ ነው”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2