Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ENTERTAINMENT  በህግ አምላክ – ጥርሷን ጨርሳ በድዷ ሳንቲም በምትበላ ‘’ታክሲ ‘’
ENTERTAINMENT

በህግ አምላክ – ጥርሷን ጨርሳ በድዷ ሳንቲም በምትበላ ‘’ታክሲ ‘’

Ethioreview newsEthioreview news—October 3, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ታዋቂ የግል ሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ የሚታከም የስራ ባልደረባዬን ለመጠየቅ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቸ ጋር ጎራ ብዬ ነበር፡፡በዚህ ታዋቂ የግል ሆስፒታል ዋና በር ላይ ተደርድረው ለህሙማንና ቤተሰቦቻቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ከተዘጋጁት ታክሲዎች መካከል ይህች ምስሏን የምትመለከቷት  ‘’የጃጀች ታክሲ ‘’ከፊት ቀድማ ተሳፋሪዎችን ትጠባበቃለች፡፡በታክሲዋ እርጅናና መልከጥፉነት ተገርሜ በሞባይሌ ምስሏን ለመውሰድ መዘገጋጀቴን ልብ ያለ አንድ ሌላ ባለታክሲ  ሳቅና ቀልድ በተቀላቀለበት አነጋገር ‘’ ፎቶ ማንሳት ክልክል ነው፣ካሁን በፊት በሰይፉ ፋንታሁን ፕሮግራም የቀረበችው ይበቃታል‘’አለኝ፡፡አብረውኝ የነበሩት የስራ ባልደረቦች በኔና በባለታክሲው ቀልድ የተቀላቀለበት ንግግር ተገርመው ሲስቁ ጓደኞቸም በታክሲዋ ሁኔታ እንደኔው ተገርመው እንደነበር ልብ አልኩ፡፡
እኔን የበለጠ የገረመኝና ያሳሰበኝ እንኳንስ ሊጓዙባት ቀርቶ ለእይታም የምትደብርና‘’ከአርጅናም አልፋ ያረጠች ታክሲ ‘’ለትራንስፖርት አገልግሎት ያቀረበው ‘’የታክሲ ባለንብረት ‘’ድፍረትና ማንአለብኝነት ብቻ ሳይሆን በህይወታቸው ወስነውና ምቾታቸውን አጥተው ያውም ገንዘብ ከፍለው በዚች ጥርሷን ጨርሳ በድዷ ሳንቲም በምትበላ ‘’ታክሲ ‘’
የሚሳፈሩት  ሰዎች ናቸው፡፡
እርግጥ ነው የከተማችን አንዱና በኔ እምነትም እጅግ  አሳሳቢውና አስመራሪው ችግር የትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት መሆኑን አውቃለሁ፡፡በዚህ ምክንያትም በሌሎች አገሮች በተለይም በኢኮኖሚ ባደጉ አገሮች ‘’እስከመፈጠራቸው የተረሱ ‘’ እና ሞዴላቸው ወደ ሙዚየም ከገባ ዓመታት ያስቆጠሩ ተሸከርካሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ያለማንም ከልካይ በጎዳናዎቻችን ላይ ሲንተፋተፉና እንደ ኤሊ በደረታቸው እየተሳቡ የትራፊክ መጨናነቅ ሲፈጥሩ እንመለከታለን፡፡


የኢትዮጵያ መንግስት የራሱን ተሸከርከሪዎችም ሆነ ሌሎች ንብረቶች የሚያስተዳድርበትና አስፈላጊም ሲሆን የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱ አሮጌና ጊዜ ያለፈባቸውን ንብረቶች/ተሸከርካሪዎች የሚያስወግድበት ወይም ቅርጽና ይዘታቸውን ቀይሮ ለሌላ አገልግሎት የሚያውልበት መመሪያ እንዳለው አውቃለሁ፡፡ጥያቄው መመሪያው በሁሉም ዘንድ በትክክል ይፈጸማል ወይ የሚለው ነው፡፡
በነገራችን ላይ በሌሎች ያደጉ አገሮች ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች የሚገለገሉባቸውን ማናቸውም ንብረቶች በእርጅና ምክንያት ከመሰቀቃዬታቸው በፊት ቀድሞ ማስወገድና በአዲስ መተካት የተለመደ ነው፡፡የታወቁ የአሮጌ ንብረቶችና ቁሳቁሶች መሸጫና ማስወገጃ ‘’መጋዝኖች ‘’እንዳሏውም እኔ ራሴ ምስክር ነኝ፡፡በአንድ ወቅት በነበርኩበት አገር አንድ ‘’ ምርጥ ጃኬት‘’ገዝቸ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ለብዙ ጊዜ መዘነጤንና  በኋ

ላም ለአንድ ዘመዴ በስጦታ ማበርከቴን አስታውሳለሁ፡፡
በዚህም ምክንያት ነው በሌሎች አገሮች የአገልግሎት ዘመናቸውን ጨርሰው የተወገዱ  ተሸከርካሪዎች፣ ኮምፒውተሮች፣ አልባሳት …በልዩ ልዩ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው በመግባት ችግር ሲፈጥሩና አደጋም ሲያስከትሉ የምንመለከተው፡፡
ሌለው አስገራሚ ነገር የተሸከርካሪ ቁጥጥርና የትራፊክ ፖሊስ አካላት እንዲህ ዓይነት በእርጅና ምክንያት ቆዳቸውን የቀየሩ ተሸከርካሪዎችን እየተመለከቱ ምንም ዓይነት እርምጃ ሲወስዱ አለመታየታቸው ነው፡፡ጭራሹንም በየዓመቱ የተሸከርካሪ ደህንነትና ቴክኒካዊ ብቃት  ማረጋገጫ ማስረጃ እየሰጡ በየቀኑ ግን የተሸከርካሪ አደጋና የሰው ሞት ወሬ ያቀርቡልናል፡፡
መንግስት ሆይ ! በህግ አምላክ! ለአይን የሚያስቀይሙ ብቻ ሳይሆን አደጋ የሚያስከትሉና መህበራዊ ችግር በመፍጠር ከተመሳ ጭምር የሚያቆሽሹ ያረጡ ተሸከርካሪዎችን  እንዲሁም ሌሎች ያረጁ ንብረቶች ማስወገድ የሚችል ሌላ‘’የኮሪደር ልማት  ‘’እንድትጀምርልን በዚች ታክሲ ስም እንጠይቃለን፡፡

Vua Al Abebe fb

entertainment
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በአማራ ክልል የሰላም ዋጋ ስለምን ተራከሰ? የንጹሐንና ሕጻናት … እምባ
ገንዘብ ሚኒስቴር የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝር በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ያደርጋል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ENTERTAINMENT

ራስ – በኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች IA መጠቀም የሚያስችለው መተግበሪያ

August 21, 2025
ENTERTAINMENT

በግብፅ የቀብር ስፍራዎች 3ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ማር ተገኘ

August 3, 2025
ENTERTAINMENT

ፍቅረ ማርቆስ ደስታ – ኢትኖግራፈሩ ደራሲ

July 24, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2