Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  የደም ግፊት – ድምጽ አልባው ነብሰ ገዳይ
SOCIETY

የደም ግፊት – ድምጽ አልባው ነብሰ ገዳይ

Ethioreview newsEthioreview news—November 2, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ስለ ደም ግፊት የሚወጡ መረጃዎች አስደንጋጭ እየሆኑ ነው። ደም ግፊት እጅግ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች እየጨረሰ ነው። ደም ግፊት “ድምጽ አልባው ገዳይ” የተባለውም ለዚህ ነው። አሁን አለሁ ሲሉ ድንገት ጭጭ የሚያደርግ የዘመናችን መርዝ ነው።

በመላው ዓለም 1,28 ቢሊየን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 79 ዓመት የሆነ ሰዎች ለከፍተኛ የደም ግፊት የጤና ችግር መጋለጣቸውን የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል። እንደመረጃው ከተጠቀሰው ቁጥር 46 በመቶ የሚሆኑት ችግሩ እንዳ4ለባቸው እንኳን አያውቁም።

ድምጽ አልባው ገዳይ የደም ግፊት፤ አስቀድሞ መደረግ የሚገባው ጥንቃቄ የህክምና የባለሙያ ምክር

High blood pressure (hypertension) - Diagnosis & treatment - Mayo Clinic
አማካኝ የደም ግፊት 120 በ80 መሆኑን የህክምና ባለሙያዎችም ሆኖ የህክምና መረጃዎች ያመለክታሉ። ሰዎች አዘውትረው የደም ግፊታቸውን ጠን በመለካት እንዲከታተሉ ይመከራል።ፎቶ ከማኅደር፤ የደም ግፊት ሲለካምስል Getty Images/AFP/R. Gacad

ከፍተኛ የደም ግፊት ወይም በህክምናው ሃይፐርቴንሽን በደም ቧንቧ ውስጥ የሚኖረው የደም ግፊት 140 በ90 ወይም ከዚያ በላይ ሲደርስ እንደሆነ የህክምና መረጃዎች ያመለክታሉ። እንዲህ ያለው የደም ግፊት መጠን የተለመደ ሲሆን ተገቢው የህክምና ክትትልና ጥንቃቄ ካልተደረገ ግን አደገኛ መሆኑንም ያሳስባሉ።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰዎች ድንገት ከከፍተኛ የደምግፊት ጋር በተያያዘ በልብ ህመም ወይም ለደም ዝውውር መታወክ ወይም ስትሮክ መጋለጣቸው እየተደጋገመ ነው። እንደ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ በመላው ዓለም 1,28 ቢሊየን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 79 ዓመት የሆነ ሰዎች ለደም ግፊት የተጋለጡ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 46 በመቶ የሚሆኑት ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳላቸው አያውቁም።  ሳይታወቅ ለተለያየ የጤና ችግር ከመዳረጉም በላይ እስከ ሕልፈተ ሕይወት ያደርሳልና የህክምና ባለሙያዎች ከፍተኛ የደም ግፊትን ድምጽ አልባው ገዳይ ይሉታል። የደም ግፊትን በየጊዜው መከታተል በመዘናጋት ሊያስከትለው ከሚችለው ውስብስብ የጤና ችግር አስቀድሞ ለመከላከል እንደሚረዳም ይመክራሉ። በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ በግል ክኒሊካቸው የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት የአጠቃላይ እና የውስጥ ደዌ ሀኪም ዶክተር ሊበን በሽር ስለደም ግፊትን የደም ማነስና ደም መብዛት በሚል ያልተገባ ስያሜ መስጠት እንዳለ ያመልክታሉ።

የደም ግፊት እና የደም ማነስ

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022

የደም ማነስ ወይም በእንግሊዝኛው የኒሚያ የሚባለው የቀይ የደም ሴሎች በቁጥርም ሆነ በአይነት ሲያንሱ እና ብረት ወይም አይረን የሚባለው ንጥረነገር (የቀይ የደም ሴልን ኦክስጅን የሚያመላልሰው) በደም ውስጥ የእሱ ማነስ ሲከሰት የሚታይ የጤና ችግር ነው። የደም ግፊት በምሳሌ ሲያስረዱ ዶክተር ሊበን በቧምቧ ከሚወርድ የውኃ ኃይል ጋር ያነጻጽሩታል፤ ግፊት የሚባለው ልብ በሚመታበት ጊዜ በደም ቧምቧ ውስጥ የደም አወራረድ ያለውን ኃይል ያመላክታል ነው ያሉት። ይኽ ደግሞ ክንድ ላይ ተደርጎ በመለኪያ አማካኝነት ሊለካ እና ሊታወቅ እንደሚችልም አመልክተዋል።

የደም ግፊት አመጣጥ

ከፍተኛ የደም ግፊት መንስኤው የማይታወቅ እና የሚታወቅ ተብሎ ይለያል። ከቤተሰብ የሚወረስ እንዳለ ሁሉ በአኗኗር ዘይቤ ማለትም አመጋገብ እና እንቅስቃሴ ካለማድረግ፤ እንዲሁም ውፍረት፣ አልክሆል መጠጥ፤ ማጨስ እና ተያያዥ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ልማዶችን ማዘውተር በመንስኤነት ይጠቀሳሉ። ከፍተኛ የደም ግፊት ከሌላ ህመም ጋር በምክንያትም በውጤትም እንደሚያያዝ የሚናገሩት ዶክተር ሊበን፤ የስኳር ህመም፤ የደም ውስጥ ቅባት ወይም ስብ መጨመር ኮሌስትሮል የሚባለው ማለት ነው፤ የደም ስርን በማጥበብ ለደም ግፊት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት።

ሊደረግ የሚገባ ጥንቃቄ

የተለያዩ የደም ግፊት መለኪያዎች እየመጡ ነው። አጋጣሚውም ሆነ ዕድሉ ካለ በቀላሉ በእጅ ላይ እንደ ሰዓት በማሰር የራስን የደም ግፊት መለካት ይቻላል። ፎቶ ከማኅደር፤ የደም ግፊት መለኪያ

የደም ግፊትን በተለይ ደጋግሞ መለካት እንደሚኖርበት፤ ከምንም በላይ ደግሞ የጤና እክሉ እንዳለበት የተነገረው ሰው በተረጋጋ ሁኔታ እቤቱ ሆኖ የደም ግፊቱ መለካት እንዳለበትም ዶክተር ሊበን ያመለከቱት። እርግጥ ነው በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ሰዎች በቤታቸው የግላቸው የደም ግፊት መለኪያ ላይኖራቸው እንደሚችል ይታወቃል እና ሀኪም ጋር ተመላልሶ በመሄድ ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት። እንዲህ ያለው የጤና እክል ከመከሰቱ አስቀድሞ ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ በተመለከተም ለህመም ከመጋለጥ በፊት ሰዎች አቅም በፈቀደ ሳያሰልሱ የጤናቸውን ይዞታ ወደ ሀኪም እየሄዱ መታየት፤ ቢያንስ በእግር በመጓዝ በቂ እንቅስቃሴ በየቀኑ ማድረግ፤ አመጋገብን በተመለከተም ጨው እና ቅባት አለማብዛትን መክረዋል።  

ምንም እንኳን ከፍተኛ የደም ግፍት በአብዛኛው የሚያሳየው የተለመደ የህመም ምልክት ባይኖርም የራስ ምታት፤ በእይታ ላይ የሚከሰት ብዥታ፤ የደረት ላይ ህመም እና የመሳሰሉን ሊያስከትል እንደሚችል ነው የሚገለጸው። ያልታከመ ከፍተኛ የደም ግፊት የኩላሊትን ጤናማ ተግባር የማሰናከል፤ የልብ ህመም እና የደም ዝውውር በማዛባት የተለያዩ የጤና እክሎችን እንደሚያስከትልም የህክምና ባለሙያው አመልክተዋል።

source Dw


SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ሰውን “ሰው” የሚያደርገው ምንድነው? ከእኛ ይልቅ የጥንቶቹ ዘመናዊ ነበሩ
Bihi: Somaliland Sea Access MoU with Ethiopia stands, nothing has changed
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2