Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  በካዛንችሱ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በሚቀጥሉት 18 ወራት 20 ሺ ቤቶች
SOCIETY

በካዛንችሱ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በሚቀጥሉት 18 ወራት 20 ሺ ቤቶች

Ethioreview newsEthioreview news—January 25, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪውን የቤት ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ አማራጮችን ታሳቢ በማድረግ እየሰራ ይገኛል፡- ዘሪሁን አምደማሪያም (ኢ/ር)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪውን የቤት ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ አማራጮችን ታሳቢ በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት እና የግል አጋርነት ጽ/ቤት ኃላፊ ዘሪሁን አምደማሪያም (ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ኃላፊው ዘሪሁን አምደማሪያም (ኢ/ር)  ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪውን የቤት ጥያቄ ለመመለስ 4 የተለያዩ አማራጮችን አስቀምጦ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

እነዚህ የቤት ልማት አማራጮች  በመንግስት በጀት ፤ በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ አጋርነት፤ የ20/80 እና 40/60 እንዲሁም በግሉ ዘርፉ የሚገነቡ የቤት ግንባታ ፕሮግራሞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በካዛንችስ የመልሶ ማልማት ፕሮግራም የሚለማው የመኖሪያ ቤት በመንግስት እና በግል አጋርነት የሚለማ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በመልሶ ማልማት ፕሮግራሙ መንግስት በራሱ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለኦቪድ ኮንትራት ተሰጥተው የሚያሰራቸው 1 ሺ ቤቶች  መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም በግል አልሚዎች የሚሰሩ ቤቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ኃላፊው  በሚቀጥሉት 18 ወራት በካዛንችስ መልሶ ማልማት በጥቅሉ ወደ 20 ሺ ቤቶች እንደሚገነቡ  ተናግረዋል፡፡

በካዛንችሱ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የመንግስት ድርሻ ማደጉን ገልጸው 65 በመቶ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም 35 በመቶ የመንግሰት ድርሻ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም ለህብረተሰቡ የሚቀርበው የቤት ቁጥርም ከፍ ያለ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ሁሉም የቤት ፕሮግራሞች ታሳቢ የሚያደርጉት የቤት አቅርቦቱን ማስፋት ነው ያሉት ኃላፊው መንግስት ባለው ድርሻ የመግዛት እና የመከራየት አቅምን ከግምት በማስገባት መዝግቦ የያዛቸውን የቤት ፈላጊዎች ተደራሽ የሚያደርግበት ሁኔታ እንደሚፈጥር አብራርተዋል፡፡

በአጠቃላይ መንግስት በተለያዩ  የቤት ልማት ፕሮግራሞቹ  የቤት አማራጮችን ማስፋት ላይ እንደሚያተኩር ያብራሩት ኃላፊው አቅርቦቱ ከሰፋ በሁሉም አቅርቦቶች ቤት የማግኘት እድሎች እንደሚኖሩ አውስተዋል፡፡

በዚህም  እየቆጠቡ ያሉ ነዋሪዎች የተለያዩ የቤት አማራጮች እንደሚከፈቱላቸው አስረድተዋል፡፡

መንግሰት ከራሱ ድርሻ ላይ በተለያየ ሁኔታ እየቆጠቡ ያሉ ነዋሪዎችን የፕሮግራሞቹ እና የአቅርቦቶቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ብለዋል፡፡

በዚህም በኪራይ ለሚሳተፉ በኪራይ የመግዛት አቅም ላላቸው ደግሞ በግዢ ያቀርባልም ብለዋል፡፡

በመሆኑም የቤት አቅርቦት ፕሮግራሞቹ  የቤት ተመዝጋቢዎችን ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡

በ፣ሆኑም ተመዝጋዎችም የአሁኑን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ እና  ወቅቱን የሚመጥን ቁጠባ ማድረግ እዳለባቸውና ቁጠባቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚኖርባቸው አስረድተዋል፡፡

AMN

SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
freezes foreign aid for almost all countries, including Ukraine, Israel, and Turkey
ባለቤቱ ላይ ለመስማት የሚከብድ እጅግ ዘግናኝ የወንጀል ድርጊት የፈጸመው ግለሰብ በሞት ተቀጣ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2