Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  መሬት ለምን ይንቀጠቀጣል? ሰርቫይቫል 101 
SOCIETY

መሬት ለምን ይንቀጠቀጣል? ሰርቫይቫል 101 

Ethioreview newsEthioreview news—January 4, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ሁኔታው በኢትዮጵያ ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ሊፈጠር ይችላል፤ በተለይ የስምጥ ሸለቆን ታከው የሚገኙ ከተሞች፤ ይህ መረጃ አስፈላጊ በመሆኑ ለሌሎችም ያካፍሉ፤ ያዳርሱ፡፡

       ==የመሬት ውስጣዊ አወቃቀር==


መሬት ሙሉ በሙሉ በጠጣር ቁስ የተሞላች አይደለችም፡፡ መሬት የተዋቀረችው ከሦሥት ዋና ዋና ንብርብር ንጣፎች ነው፡፡ እነርሱም፡- ቅርፊተ አካል(Crust)፣ የምድር ማዕከል ንጣፍ(Mantle)  እና ውስጠ እምብርት(Core) ናቸው፡፡ (አወቃቀሩ በስዕላቂ መግለጫ ውስጥ ይገኛል ተመልከቱት፡፡)

•  ቅርፊተ አካል(Crust)፡- ይህ ስስ የሆነ የመሬት የላይኛው  ንጣፍ ነው፡፡ እኛ የምንንቀሳቀስበትን የመሬት ወለል ይወክላል፡፡

•  የቀለጠ አለት(Mantle)፡- ይህ በመሬት ቅርፊተ አካል እና በመሬት ውስጠ እምብረት መከካከል ቀልጦ የሚዋልል የቀለጠ አለት ነው፡፡

•  ውስጠ እምብርት(Core)፡- ይህ የመሬት ውስጠ እምብርት ክፍል ሲሆን ስሪቱም ብረት ነው፡፡

==የመሬት ውስጠ እምብርት ምን ያክል ሞቃት ነው?==


የዚህን ጥያቄ መልስ ማንኛውም ተመራማሪ በእርግጠኝነት  ይህን ያክል ነው ብሎ አይናገርም፤ ነገር ግን የውስጡ ክፍሎች በጣም ሞቃት እንደሆኑ የሚመሰክሩ ማስረጃዎች በመሬት ገፅታዎች ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ሁኔታም በእሳተ ገሞራዎች ፍንዳታ እና ቀልጠው በሚፈሱ አለቶች መልክ ማየት ይቻላል፡፡  
                      
==መሬት መንቀጥቀጥ==


የመሬት ዉጫዊው ክፍል በተለያዩ ቅርፊት መሰል አካላት(plates) የተሸፈነ ነዉ፡፡ የነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት ዉፍረት በአማካይ ከ(20-60) ኪ.ሜትር ወደ መሬት ስር ይዘልቃል፡፡ እነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት በመካከላቸዉ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የኃይል መጠራቀም ይፈጥራል፡፡ የኃይል መጠራቀሙም እየጨመረ ይሄድና የአለቱ አካል ሊሸከመዉ ከሚችለዉ አቅም በላይ ሲሆን ይደረመሳል፡፡ ይህ በከፍተኛ ጫና ታፍኖ የነበረ ኃይል በድንገት ሲያፈነግጥ የሚወጣዉ ከፍተኛ ኃይል በመሬት የላይኛዉ ቅርፊት አካል ላይ በሞገድ መልክ በፍጥነት ይሰራጫል፡፡ የዚህን ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጠረ ወይም ተከሰተ እንላለን፡፡ የነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት እንቅስቃሴ ሁኔታ እና መጠን እንደየአካባቢዉ ይለያያል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ጥናት ሴስሞሎጂ (Seismology) ይባላል፡፡ ቃሉም የግሪክ (Seismos) ሲሆን ትርጉሙም መንቀጥቀጥ ማለት ነዉ፡፡

እነዚህ ቅርፊት አካሎች(Plates) አንዱ ከሌላዉ የሚለይበት እጅግ በጣም ረዥም የሆነ ስንጥቅ ይገኛል፡፡ ይህ ስንጥቅ የተለያዩ መዛነፎችን ይፈጥራል፡፡ ይህ አጠቃላይ ስንጥቅም የዝንፈት መስመር(fault line) ይባላል፡፡ በዝንፈት መስመር የሚለያዩ ቅርፊተ አካሎች(Plates) እጅግ ግዙፍ እንደመሆናቸዉ መጠን አንደኛዉ በሌላኛዉ ላይ ተፅዕኖ ማድረሳቸው የማይቀር ነዉ፡፡ በመሆኑም እነኚህ የተለያዩ ቅርፊተ አካሎች እርስ በርሳቸዉ በተቃራኒ አቅጣጫ አንዱ ከሌላኛዉ ሊሸሽ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ቅርፊተ አካሎቹ እርስ በርሳቸዉ ተደጋግፈዉ የሚኖሩበትን መንገድ ስለሚያመክን በከፍተኛ ጫና ምክንያት አለቶቹ ተያይዘዉ እንዲደረመሱ ሲያደረግ ታምቆ የቆየዉ ኃይል በማፈንገጥ የሚለቀዉ ኃይል ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ይፈጥራል፡፡ ከዚህ ማዕከላዊ ቦታ የሚነሳዉ ከፍተኛ ሞገድ በሁሉም አቅጣጫ በመሰራጨት እረጃጅም ስንጥቅ መስመሮችን እየሠራ በመቀጠል የላይኛዉን የመሬት ንጣፍ ገፅታ ያመሰቃቅላል፡፡

ከተፈጥሮአዊ ምክንያቶች በተለየ ሁኔታ የሰዉ ልጅ አንዳንድ እቅስቃሴዎችም የመሬት መንቀጥቀጥ ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- የተለያዩ መርዛማ ዝቃጮችን ለማስወገድ ተብለዉ የሚቆፈሩ ጥልቅ ጉድጓዶች፣ ዉሃ ለማከማቸት ተብለዉ የሚቆፈሩ ጥልቅ ጉድጓዶች፣ በመሬት ዉስጥ ለዉስጥ ለኒዩክለር ጦር መሳሪያ ሙከራዎች የሚቆፈሩ መተላለፊያዎች፤ ሰዉ ሰራሽ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ የእነዚህ ድርጊቶች መስፋፋት ከተፈጥሮአዊዉ የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ተፅእኖ በመፍጠር የመሬት መንቀጥቀጥ ሊያስከትል ይችላል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያስከትለዉ ዉድመት አደጋዉ የደረሰበት አካባቢ ያለዉ የመሬት አቀማመጥ፣ መንቀጥቀጡ የሚቆይበት ጊዜ እና መንቀጥቀጡ የሸፈነዉ ክልል ይወስነዋል፡፡ ህንፃዎች የተሠሩበት የንድፍ ዓይነት እና ለግንባታ ጥቅም ላይ የዋለዉ የቁስ ዓይነትም የአደጋዉን አስከፊነት ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ ማስተዋል ከምንችለዉ በጣም ዝቅተኛ የንዝረት መጠን አንስቶ እስከ ብዙ ሺህ ኪ.ሜትሮች የሚደርስ የሞገድ ነዉጥ ሊፈጥር የሚችል ነዉ፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ላይኛዉ ቅርፊተ አካል ላይ የሚገኙትን ህንፃዎች ፣ድልድዮች እና ግድቦች እንዲፈርሱ በማድረግ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከባህር ወይም ከዉቂያኖስ ከፍተኛ የሆነ የዉሃ ሞገድ ሱናሚ(Tsunami) በማስነሳት እና ወደ የብስ በማምጣት ለመገመት የሚያዳግት ጥፋትን ያደርሳል፡፡ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተተክለዉ የሚገኙ መሳሪያዎችም የመሬት መንቀጥቀጦችን ከተለያዩ ቦታዎች ላይ በየቀኑ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ በእርግጥ ከእነዚህ ዉስጥ አደጋ የመፍጠር አቅም ያላቸዉ በጣም ጥቂቶች ናቸዉ፡፡

ባለፉት 500 ዓመታት በዓለማችን ላይ ብዙ ሚሊዮን ሰዎች ሕይወታቸዉን በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት አጥተዋል፡፡ የብዙ አገራት የመሠረተ ልማት አዉታሮች እና ንብረቶች እንዳልነበር ሆነዉ አልፈዋል፡፡  የመሬት መንቀጥቀጥን ቀድሞ መተንበይ በጣም አዳጋች ቢሆንም በቂ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን  በማድረግ፡-ለምሳሌ ስለ አደጋዉ ትምህርት በመስጠት፣ የአደጋ ጊዜ እቅዶችን በማዉጣት እና በማሰልጠን ፣ጠንካራ እና ተጣጣፊ(ከሁኔታዉ ጋር የሚስማማ) ንድፍ ለህንፃዎችም ሆነ ለሌሎች መሠረተ ልማቶች በመጠቀም ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል፡፡

==ዝርግ ንጣፎች  እንዴት ይንቀሳቀሳሉ?==

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022


ዝርግ ንጣፎች የጎንዮሽ በተቃራኒ አቅጣጫ ሊፋጩ ወይም በተቃራኒ አቅጣጫ ተቀራርበው ሊገፋፉ ወይም በተቃራኒ አቅጣጫ ሊራራቁ ወይም በተቃራኒ አቅጣጫ በቁመታቸው ሊፋጩ  ይችላሉ፡፡  ይህ ማለት ደግሞ እነኝህ ንጣፎች የሚገናኙበት ቦታ መረጋጋት የተሳነው እና ብዙ ክንውኖች ያሉበት ቦታ ነው፡፡ ለምሳሌ በስዕል እንደምትመለከቱት ሁለት የተለያዩ ዝርግ ንጣፎች በተቃራኒ አቅጣጫ ቢራራቁ በሁለቱ ዝርግ ንጣፎች ታፍኖ የነበረው የቀለጠ አለት በከፍተኛ ኃይል መገንፈሉ የማይቀር ነው፡፡ ያም ካልሆነ ደግሞ በሁለቱ ዝርግ ንጣፎች በተቃራኒ አቅጣጫ መራራቅ ምክንያት(የአብዛኞቹ ስምጥ ሸለቆዎች የተፈጠሩበት መንገድ) የሚፈጠረው የአለቶች መናድ ከፍተኛ ንዝረቶች በመፍጠር መሬትን ማንቀጥቀጡ የማይቀር ነው፡፡(ስዕላዊ መግለጫዎችን ይመልከቱ)

በዝንፈት መስመር(የቅርፊተ አካሎች መዋሰኛ) ላይ በእንቅስቃሴዎቹ ምክንያት የሚፈጠረው ከፍተኛ ጫና የሚፈጥረው የኃይል መጠራቀም አለቱ መሸከም ከሚችለው አቅም በላይ ሲሆን የሚከሰተው የአለቶች መሰባበር እና መደርመስ በሁሉም አቅጣጫ ሞገዱ በመሰራጨት እና ከፍተኛ ንዝረት በመፍጠር የመሬት መንቀጥቀጥን ያስከትላል፣ የመሬት ገፅታም ምስቅልቅሉ ይወጣል፡፡

==የመሬት መንቀጥቀጥ ልኬት==


የመሬት መንቀጥቀጥ ልኬት የሬክተር ስኬልን(Recter scale) በመጠቀም ይከናወናል፡፡ ዘዴው የሚጠቀመው የሂሳብ ቀመሮችን በመሆኑ በጣም ልከኛ ነው፡፡ ትልቅ ቁጥር ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያመለክተው ትልቅ ጥፋትን ነው፡፡ በስዕል ውስጥ ያለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ፡፡

አንድ የሬክተር ስኬል ቁጥር ከቀዳሚው ቁጥር በአስር እጥፍ ኃያል ነው፡፡ ይህንን የመሬት መንቀጥቀጥ የሚለካው መሳሪያ ሳይስሞግራፍ(Seismograph) ይባላል፡፡  ከተለያዩ ቦታዎች የሚወሰዱትን የሬክተር ስኬል(Recter scale) መረጃዎች በንፅፅር በማየት የመሬት መንቀጥቀጡ ከየት አካባቢ እንደጀመረ ለመለየት ይረዳል፡፡

በክፍል ሁለት የመሬት መንቀጥቀጥ በምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ ምን ይመስላል? ሁኔታው ያሰጋናል ወይ? የሚለውን እንመለከታለን፡፡ ወደፊት በክፍል ሦሥት ደግሞ ሁኔታው ሲፈጠር ምን አይነት ፈጣን እንርምጃ እንውሰድ የሚለውን እናያለን፡፡

     (ክፍል አንድ – እ እ አ 2016 ላይ የተፖሰተ ነው)

By Muluken Asrat FB

SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Ethiopia Backs New Peacekeeping Force in Somalia
መሬት ለምን ይንቀጠቀጣል?  ሰርቫይቫል 101
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2