Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  “ኦሮማይን ካነበቡ ድምዳሜው ሻዕቢያ መጥፋት አለበት የሚል ብቻ ነው” በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲራባና ተደጋጋሞ እንዲተረክ ተጠየቀ
News

“ኦሮማይን ካነበቡ ድምዳሜው ሻዕቢያ መጥፋት አለበት የሚል ብቻ ነው” በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲራባና ተደጋጋሞ እንዲተረክ ተጠየቀ

Ethioreview newsEthioreview news—January 11, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሻዕቢያን የማይቀየር ማንነት ቁልጭ አድርጎ በታሪክና ትንቢት ለትውልድ ያስቀመጠው ኦሮማይ የተሰኘው የጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ መጽሃፍ በተደጋጋሚ እንዲተረክና በተለያዩ የአገር ውስጥና የዓለም ታላላቅ ቋንቋዎች ሊተረጎም እንደሚገባ ተጠየቀ። “ኦሮሚያን አንብቦ ወይም አድምጦ የተረዱ ሁሉ መጨረሻ ላይ የሚደርሱበት ድምዳሜ ሻዕቢያ መጥፋት አለበት የሚል ብቻ ነው” ሲሉም ጥቆማውን ጥያቄውን ያቀረቡት አመልክተዋል።

ጥያቄውን ያነሱት ኦሮማይ በእንግሊዝኛ መተርጎሙን በዜና የሰሙ ወገኖች ናቸው። በዓሉ ግርማ በረቂቅ ብዕሩ ሻዕቢያ ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ፣ በእባብ የሚመሰሉ መርዘኞች ስብስብ እንደሆነ፣ ይህ ዕባባዊ ባህሪው እንደማይለቀው፣ ኢትዮጵያዊያን በየዋህነት የሚያደርጉትን በመርዘኛ ተግባራቸው እየገለበጡ ለጥቃት የሚጠቀሙ፣ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራቸውና ውጥናቸው ሳያሳካ እንደማይተኙ ያስረዳበት መጽሃፍ እንደሆነ ያስረዳሉ።

“አሁን ላይ ሻዕቢያን አስመልክቶ የተወሰኑ መንሸዋረሮች ያሉት ኦሮማይን በቅጡ ካለመረዳት የተነሳ ነው። ሻዕቢያ መፍትሄ እንዳለው አድርገው እየሰሩና እግሩ ስር የሚንከባለሉት ኦሮሚይን በቅጡ ባለማንበባቸው ወይም ባለመረዳታቸው ሳቢያ ነው። ይህ ምንም ዓይነት ጥናት አያስፈልግም” በማለት ትውልድ ሁሉ የሻዕቢያን ማንነት፣ ኢትዮጵያ ላይ ያለውን አቋም፣ እንዴት በሴራ የተካነና የዋህነትን በክፋት መርዝ ለውሶ የሚናደፍ፣ እስከመቼውም ሊቀየር የማይችል የእፉኚቶች ስብሰብ መሆኑን እንዲያውቅ በተለያዩ ቋንቋዎች በተደጋጋሚ ሊተርክ እንደሚገባው ይገልጻሉ።

ጥያቄውን ካነሱት መካከል አንዱ የሆኑት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያው አቶ ይርጋለም አሰፋ ” ሻዕቢያ መርዙን ምላሱ ስር ደብቆ በጠራራ ጸሐይ እንደሚንከላውስ ተናዳፊ እባብ ዓይነት ነው” ይላሉ። ለዚህም ማስረጃው ሻዕቢያን እንደ ፊልም ቁልጭ አድርጎ የሳለው ኦሮማይ መሆኑን አመልክተው ተደጋጋሞ ሊተርከና ትውልድ ሻዕቢያን በወጉ እንዲረዳው መደረግ እንዳለበት ያምናሉ። ይህ ቢሆን “ሻዕቢያ እግር ስር የሚንደባለሉት ትውልዱን አያሳስቱትም። እነሱም የዚያን ያህል ድፍረት አይኖራቸውም”

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ስለሺ አበበ የተባሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ የሻዕቢያን ሴራና ዕባብነት ለመረዳት ሻዕቢያን “ክጃለሁ” ብሎ አዲስ አበባ የገባውንና በመጽሃፉ የተገለጸውን “ስዕላይ በራኺ” ማየት በቂ ነው። የስዕላይ ባህሪ ያነበበ የሻዕቢያ ሰዎችን መሰሪነት፣ በምንም መልኩ ሊታመኑ እንደማይችሉ፣ ይህ ባህሪያቸው ከቶውንም እንደማይቀየር ማሳያም እንደሆነ ይገልጻሉ። አሁን ሻዕቢያ ዙሪያ የተኮለኮሉት ሁሉ ይህን ቢረዱ የኢትዮጵያ መከራ የሚያበቃበትን ጊዜ እንደሚያሳጥረው ይናገራሉ።

ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ በ1975 ዓ.ም ለኅትመት የበቃው ኦሮማይ መጽሃፍ ይህ ትውልድ ሻዕቢያን እንደፊልም በግላጭ እንዲያየው ከማድረግም በላይ ብሄራው ቁጭትን እንደሚያነሳሳ ጥያቄውን ያቀረቡት ወገኖች ይገልጻሉ። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ኦሮማይን ለታሪካ ለትውልድ በተለያዩ ቋንቋዎች ማሳተም ብቻ ሳይሆን በፊልምና በዘጋቢ መልክም ሊሰራ እንደሚገባ ይጠቁማሉ። ከዛም አልፎ በቤተ መዘክር አንድ ተራኪ ምስል ተበጅቶለት ትውልድ ሁሉ ሊማርበት እንደሚገባ ምክር ይሰጣሉ። “ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ የጥበብ ሰዎችም ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባ ነበር። ስራቸው ነው። ይመለከታቸዋል” ሲሉ ወቀሳና ጥቆማ ያቀርባሉ።

ሲያስረዱም ” የኢትዮጵያ ዕዳ የሆነው ሻዕቢያ በሁሉም ኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ በነበረው በቤተሰብ አደረጃጀት ልጆቻቸውን ከዕባብነቱ በሚመነጨው መርዘኛ የሃሰት ትርክት መንደፉን ይጠቅሳሉ። ስለዚህም ሻዕቢያ ለነደፋቸው ከተቀበሉት ማስተካከያ፣ ለኢትዮጵያዊያን ግን ሻዕቢያ በትክክልም መርዘኛ እባብ መሆኑ በማሳየት እሱ ካልጠፋ ሰላም ሊገኝ እንደማይቻል አቋም የሚይዙበት ይሆናቸዋል” ብለዋል።

ሃሳቡን ያነሱት ክፍሎች “የበዓሉ ግርማ ታላቅ ድርሰት የሆነው ኦሮማይ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ መተርጎሙ ተሰማ” በሚል ፋና የዘገበውን ዜና ተመልክተው አድንቀዋል። ቢዘገይም ይህን ላደረጉ ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል። ዓለምም ሆነ አፍሪካዊያን ሻዕቢያን ጠንቅቀው እንዲያውቁት እንደሚረዳቸው ገልሰዋል። ይሁን እንጂ በቂ እንዳልሆነ አመልክተዋል።

በተለይ በአረብኛ ባስቸኳይ ተተርጉሞ ሊሰራጭ እንደሚገባ አሳስበዋል። አረብ አገራት ሻዕቢያ ታማኝ ወዳጅ ሊሆን እንደማይችልና በዚሁ ባህሪው ተገልሎ ” በኤርትራ ሰዓት ቆሟል” እስኪባል የተገለለ፣ አምራች ዜጎች በቅርቡ የሚነጥፉባት አገር የተሸከመ የሽፍታ ስብሰብ መሆኑ ለመረዳት እንደሚያግዛቸው አመልክተዋል። ቢቻል በፈርንሳይኛ፣ በጀርመንኛና በቻይንኛ ቢተረጎም ጥቅሙ የጎላ መሆኑ አስረድተዋል።

ሻዕቢያ እንዲፈጠር ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በውክልናና በተላላኪነት ኢትዮጵያ ላይ የሚዘምቱ ታጣቂዎችን ሲያሰለጥን፣ ሲያደራጅና፣ ሲያዘምት መኖሩ ይታወሳል። አሁንም ይህንኑ ተግባሩ እንደገፋበትና መረጃዎች እየወጡበት ነው። ከለውጡ በሁዋላ የተፈጠረውን ሰላም ተንተርሶ አማራ ክልል ውስጥ ሴል መስርቶ ቀውስ ማስነሳቱንም በመረጅ አስደግፈው እያጋለጡት ነው። ይህ ሳያስቆጫቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት የሻዕቢያ ተቃዋሚዎችን እያሰለጠነ ነው ሲሉ ከመሳይ ጋር በመሂን እየተቀባበሉ ክስ አሰምተዋል። አስተየቱን የሰጡት እነዚህን ወገኖች “ሻዕቢያ እግር ስር የሚንደባለሉ”ሲሉ ከሚገልጿቸው መካከል ናቸው።

በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በውጭ አገር ስለሚኖሩ፣ ሻዕቢያን እንዲያውቁት ይህ ሊደረግ እንደሚገባው አጥብቀው ያሳሰቡት እነዚሁ ክፍሎች፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ይህን መሰሉን ስራ ህግና ደንብ አክብሮ ቢሰራ እንደሚበጀው አመልክተዋል። ህብዝ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ስለ ሻዕቢያ በቂ መረጃ ቢያገኝ በዚህ ደረጃ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነፍጥ አንጋች እየፈለፈለ ችግር ሊፈጥር እንደማይችል አክለው ያስረዳሉ።

የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በቀናነት በሚፈጽሙት ነገር ሁሉ ግብረ መልሱ በተለያየ መልኩ ጥቃት እንደሆነ በደፈናው ያስረዱት ወገኖች፣ ይህ ትውልድ እንደቀደመው የሚታለል እንዳልሆነ ማሳየትና በብሄራዊ ቁጭት ነቅቶ አገሩን እንዲታደግ ኦሮማይ በተደጋጋሚ በብዛት ህዝብ በሚያዳምጣቸው መገናኛዎች ትክክለኛው ሰዓት ተመርጦ ሊተረክ ይገባል። የብሄራዊ ጥቅም ጉዳይ የታጨቀበት በመሆኑ መጽሃፉ በትምህርት ቤቶች የክርክር መድረክ፣ በተለያዩ የውይይት አውዶች ላይ መጋገሪያ እንዲሆን አገር ወዳድ የሆኑ ሁሉ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባም ጠይቀዋል።

ፋና እንዳለው ኦሮማይ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተረጎሙት ዴቪድ ደ ጉስታ እና መስፍን ፈለቀ ይርጉ ናቸቅ። በ1970ዎቹ የታተመውው ኦሮማይ በስነ-ፅሁፍ ስልቱና በይዘቱ የተዋጣለት ድርሰት መሆኑን በርካታ ደራሲያንና ሃያሲያን መስክረውለታል። በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው ኦሮማይ 400 ገፅ ያለው ሲሆን በእንግሊዝ ሀገር መታተሙን ይፋ ያደረገው ጋርዲያን ነው።

የተረጎመውን መጽሃፍ መነሻ በማድረግ ሻዕቢያን የሚዲያ አጀንዳ በማድረግ ረገድ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ብዕራቸውን ሊያነሱ እንደሚገባም መክረዋል። በራሳቸው ጥምረት ውስጥ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉም አመልክተዋል። በእነሱ መረዳት ሻዕቢያ እስካለ ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም። ኦሮማይን አንብበው የተረዱ ሁሉ ድምዳሜያቸው ተመሳሳይ እንደሆነም አመልክተዋል።


ተስፋዬ ገ/አብ እንደ “ካቡጋ”

“ሰውን ውደደው እንጅ አትመነው” የሚል የጥንት የአበው አባባል አለ። ግራ የሚገባኝ አባባል ነው ለእኔ። ከወደድኩት እንዴት አላምነውም የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ እያመላለሰብኝ። መቼም እየጠሉ ማመን የሚባል ነገር ከቶም ይኖራል ብሎ ማሰብ መኖሩን እጠራጠራለሁ። በዚያው መጠን ደግሞ በመካከላቸው አንዳች ነገር እስካልተከሰተ ድረስ፣ እየወደዱ ያለማመን ነገር እንዴት እንደሚኖር ማሰብም ያስቸግረኛል። ምናልባትም ያልጠረጠረ ተመነጠረ ዓይነት ለማለት ከሆነ ያስኬድ ….

በቴሌግራም ይከተሉን https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Addis Ababa Attracts over 5 Million Domestic, International Tourists in six Months 
ተስፋዬ ገ/አብ እንደ “ካቡጋ”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2