Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  law  የአቶ ቢረሳው ገዳዮች ተብለው የተጠረጠሩ ማንነታቸውን ቀይረው ተያዙ፤ አንደኛው ጥበቃቸው ነበር
lawNews2

የአቶ ቢረሳው ገዳዮች ተብለው የተጠረጠሩ ማንነታቸውን ቀይረው ተያዙ፤ አንደኛው ጥበቃቸው ነበር

Ethioreview newsEthioreview news—January 20, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በግድያው ከተጠረጠሩትና በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሶስት ተጠርጣሪዎች መካከል አንደኛው የቀድም የባለሃብቱ የጥበቃ ሰራተኛ ነው። ግድያውም የተፈጸመው ተቀነባብሮና ዝግጅት ተደርጎበት ሲሆን፣ የተያዙት ራሳቸውንና ማንነታቸውን ቀይረው በደቡብ ክልል ነው። ፖሊስ በምስል፣ በስምና በአድራሻ ይፋ ያደረገው ዜና ግድያውን የፖለቲካ አጀንዳ ላደረጉት ክፍሎች የሚያስደስት አይሆንም

በድንገት ደጃቸው በር ላይ የተገደሉትን የአክሰስ ኮም ኩባንያ ባለቤት እና የሸበል በረንታ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢረሳው ህይወታቸው ካለፈ ቅጽበት ጀመሮ በተደረገ የተቀናጀ ክትትል ባለሃብቱን ገድለዋል የተባሉ ሁለት ተጠረጣሪዎች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በስም የሚታወቁ ሚዲያዎች ግድያውን ለተቋቋሙበት ዓላማ አውለውት እንደነበር አይዘነጋም።

አቶ ቢረሳው ምናለ ታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም 1ሰዓት ከ30 ላይ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተመትተው እንደተገደሉ ምንጮቹን ጠቅሶ የዘገበው መሰረት ሚዲያ፣ ግድያው ሲፈጸም፣ ባለሀብቱ በሚኖሩበት ለሚ ኩራ፣ ወረዳ ዘጠኝ አትሌቶች መንደር ምንም ዓይነት የጥበቃ ኃይል እንዳልነበረና ሟች የብቸና ሰው መሆናቸውንም አመላክቶ ነበር።

ይህንኑ ዜና ተከትሎ ሟች የጎጃም ሰው በመሆናቸው የተጠቁ ተደርጎ ዜናው የፖለቲካ መገበያያ መሆኑም አይዘነጋም። በርካታ አስተያየት እየታከለበት ” አትነሳም ወይ” በሚል ቅስቀሳ የማህበራዊ ሚዲያ መቀሰቀሻ ግብዓት ሆኖ ነበር።

More stories

«የትግራይ ሕዝብ ያተረፈው መከራና ስቃይ ነው»

May 5, 2022

ቴድሮስ አድሃኖም “የአማራ ክልል አሳሰበኝ” አሉ

August 7, 2023

ኢሉ አባቦራ ውስጥ ነብይ ነኝ ያለው የሃይማኖት ሰባኪ በመድፈርና ጽንስ በማቋረጥ ተፈረደበት

January 13, 2023

ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም በማዋል

July 3, 2025

ፖሊስ እንዳለው አቶ ቢረሳው ምናለ ፈንታ ታሕሳስ 21 ቀን 2017 ዓም በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው እንዳለፈ ገዳዮችን ማደን ጀምሯል።

ፖሊስ የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ በወንጀሉ ስፍራ ፈጥኖ በመድረስ የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት ለማወቅና በቁጥጥር ስር ለማዋል ቀን ከሌት ያልተቋረጠ እና እልህ አስጨራሽ ክትትል ሲያደርግ ማድረጉን ገልጾ መረጃ ቢሰጥም፣ የባለሃብቱን ግድያ ያሰራጩት ክፍሎች ግን ፖሊስን ጠቅሰው ይህ እስከተጻፈ ድረስ ምንም አላሉም።ከወንጀሉ ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ማንነትና ምንነት ለመለየትም ከአዲስ አበባ ሐዋሳ እስከ ሞያሌ ጫፍ የደረሰ መረጃና ማስረጃዎችን የማሰባሰብ ተግባር መከናወኑን ፖሊስ ዘርዝሯል።

በፖሊሳዊ ጥበብ እና ስልት በተሰራው በዚህ ስራ ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠረውን መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለውን ግለሰብ እና አብዩ አይተነው ፈንታ ጨምሮ ለወንጀሉ መፈፀም አካባቢውን በመቆጣጠር ተሳትፎ የነበረውን አቶ ወርቁ መለሰ ካሴ የተባሉትን ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጌዴዎን ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ላይ በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሪፖርት ያስረዳል።

ተጠርጣሪዎቹ ከወንጀሉ መፈፀም በፊት በተቀነባባረ ሴራ በቂ ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን የግድያ ወንጀሉን የፈፀመው መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለው ግለሰብ  በህገ-ወጥ መንገድ በታጠቀው ማካሮቭ ሽጉጥ  የአቶ አብዩ አይተነው ፈንታ የግል ጠባቂ ሆኖ ሲያገለግል እንደቆየ ተጠቁሟል።

ሁለቱ ግለሰቦች ከአቶ አብዩ አይተነው ፈንታ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት አንዱ የአካባቢውን እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ለወንጀል ፈፃሚው ሁኔታውን ሲያመቻች መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለው ደግሞ የግድያ ወንጀሉን መፈፀሙን ለፖሊስና  ለፍርድ ቤት ከሰጡት የእምነት ቃል የተረጋገጠ ከመሆኑም ባሻገር በወንጀሉ ስፍራ የመርማሪዎችንና አቃቤ ህግ ቡድን እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት የወንጀሉን አፈፃፀም መልሶ ማቋቋም (Re-construct) በተግባር አሳይተዋል፡፡

በዕለቱም የወንጀሉ ፍሬ የሆነው ንብረትነቱ የአቶ አብዪ አይተነው ፈንታ የውግ ቁጥር  የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ እና ለማምለጥ የሞከሩበት እንዲሁም ሽጉጡን የደበቁበት ላንድክሩዘር ተሽከርካሪ በኤግዚቢትነት ተይዟል ፡፡ ምንም እንኳን ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመቀየር ከወንጀሉ ተጠያቂነት ለማምለጥ በሐሰተኛ ስም ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ለመጥፋት ቢያስቡም በተሰራው እረፍት አልባ ፖሊሳዊ ጥበብ በታከለበት የክትትልና የምርመራ ስራ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በቅንጅት ሰርተዋል፡፡ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ የክትትል ስራ ውስጥ የጎላ ተሳትፎ እና ትብብር ማድረጉም ተጠቅሷል፡፡

የተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር መዋል ወንጀል ፈፅሞ ከህግ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይቻል የሚያረጋግጥ ተግባር መሆኑን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ የህብረተሰቡን አቅም በመጠቀም ውጤት መገኘቱን አመላክቷል፡፡ በቀጣይም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚደረጉ የፍትህ ሂደቶች ውሳኔውን ተከታትሎ ለህዝብ እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

homelaw
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያ የሥልጣን ቀናቸው በርካታ ትዕዛዞችን እንደሚያስተላልፉ ገለፁ
የጀዋር መሐመድ “አልፀፀትም” “እንደ መውጫ” ምዕራፍ  የእስታንፎርዱ የፖለቲካ ምሩቁ ጀዋር ተመራጩ የአገዛዝ ሥርዓት 
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2