Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?!
NewsOPINION

አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?!

Ethioreview newsEthioreview news—February 19, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በሰሜን ኢትዮጵያ ከትህነግ (የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር) ጋር በተደረገው ጦርነት በተወሰነ መልኩ በጦር መሣሪያ በተለይ ግን በሰው ኃይል አብላጫውን ይዞ የነበረው ትህነግ ቢሆንም ጦርነቱ ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት እንደገና መጠናከር ብዙ ትምህርት ጥሎ ያለፈ ነበር። ከጦርነቱ በኋላ መከላከያ በሰው ኃይልም ሆነ በመሣሪያ በፍጥነት የሄደበት መንገድ ተጠቃሽ ነው።  

ከዚህ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ስንገዛቸው የነበሩ የጦር መሣሪዎችን ማምረት ጀምረናል ማለታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ለዚህ ማስረጃ የሚሆነውም በየጊዜው በመከላከያ ሚኒስቴር ሥር በተለያዩ ክፍሎች ከተተኳሽ ጀምሮ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችና ተሸከርካሪዎች በአገር ውስጥ በልዩ ሁኔታ እየተመረቱ እንደሆነ የሚወጡ መረጃዎች በመጠቆማቸው ነው። ይህ በአየር ኃይል በኩል እየተደረገ ያለውን ፈጣን ለውጥ ሳይጨምር ነው።

አሁን ባለው አካሄድ ኢትዮጵያ በቅርቡ የሚሊታሪ ድሮኖችን እንደምታመርት ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። በተለይ አገር በቀል ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ድሮን በማምረት ረገድ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካና ኬኒያ ዋንኞቹ እንደሆኑ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ምንጮች ይናገራሉ። የምስራቅ አፍሪካ ቁንጮዎቹ ኢትዮጵያና ኬኒያ እንደሆኑ የጠቆመው መረጃው የሁለቱም አገራት ኢንጂኔሮች ከቱርክ ኢንጂኔሮች ጋር በመሆን ድሮኖቹን በአገር በቀል ቴክኖሎጂ እየቀየሩ እንደሆነ ጠቅሷል። ይህም በቅርቡ ኢትዮጵያም ሆነች ኬኒያ የቴክኖሎጂው ባለቤት እንደሚሆኑ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ ምርት የአፍሪካን ገበያ መቆጣጠር በሚለው ስትራቴጂ ደግሞ ቴክኖሎጂው ሰፊውን የአፍሪካ ገበያ በራዳሩ ውስጥ የሚያስገባ እንደሚሆን ይገመታል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ በተለይም አየር ኃይል ከስድስት ዓመት በፊት እንኳን በዚህ ደረጃ በቴክኖሎጂ የረቀቀ ምጥቀት ላይ ሊደርስ ይቅርና “ለኢትዮጵያ አየር ኃይል አያስፈልጋትም” በሚለው የትግነጉ መሪ መለስ ዜናዊ አገር አውዳሚ እሳቤ ግቢው ሳር በቅሎበትና የከብቶች ግጦሽ ቦታ ሆኖ ነበር። አየር ኃይሉ በተለይ ከግብፅና ግብፅ ከምትልካቸው የቀጣናው ጠብ ጫሪዎች የሚመጣውን ትንኮሳ በፍጥነት የመመከትና ድባቅ የመምታት ብቃቱን አስተማማኝ ደረጃ ላይ ከማድረስ አኳያ ከአፍሪካ ቀንድ ባለፈ የመካከለኛው ምስራቅና ካውኬዢያ (ምስራቅ አውሮጳና ምዕራብ ኤዢያን) የሚያካትተውን ጂኦፖለቲካ የቃኘ እንደሆነ ይስተዋላል። በዚህ የጂኦፖለቲካ ማዕቀፍ ውስጥ ዋነኛ ተጠቃሽ አገር ደግሞ አዘርባጃን ነች። 

More stories

በትግራይ አምስት ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት ጀመሩ፣ አንዱ ኤክስፖርት ጀምሯል

March 9, 2021

ብሔራዊ ባንክ በዱባይ ያሉ ድርጅቶን ተጠንቀቁ አለ

August 6, 2025

ኤርትራዊያን ስደተኞችን ከትግራይ ክልል ለማስወጣት የአደጋ ጊዜ እቅዶች መሰናዳቸውን የመንግስታቱ ድርጅት ገለጸ

August 5, 2021

የኢትዮጵያና የሶማሊያ መሪዎች የፊት ለፊት ንግግር ለማካሄድ ቱርክ አንካራ ገቡ፤ ኤርዶጋን የሁለቱን አገራት ውዝግብ ለመቋጨት አቅደዋል

December 11, 2024

የቀድሞ ሶቪየት ኅብረት አካል የነበረችው አዘርባጃን አነስተኛና ብዙም ትኩረት የማይሰጣት አገር ብትሆንም አሁን ላይ ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ አፍሪካ ቀንድ ባሉት አገራት ዘንድ የጂኦፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪ በመሆን እየታየች ነው። ከአዘርባጃን ደቡብ የምትገኘው ወሳኝ አጎራባች አገር ኢራን የዚህ መልከዓምድር “በጥባጭ” ተብላ የምትወነጀል ሲሆን በአካባቢው የኃይል አሰላለፍ የአዘርባጃን አስፈላጊነትም ከኢራን ጋር ካላት ጉርብትና የሚታይ ነው።

በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉ ቡድኖች በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በየመን፣ በሊባኖስ፣ በሶሪያ፣ በፍልስጤምና በኢራቅ የውክልና (proxy) ጥቃትና ውድመት ሲያደርሱ ከኢራን በስተሰሜን የምትገኘው አዘርባጃን በዚህ ልክ ሳትደፈር ከመቆየት ባለፈ እየበለፀገች ለመሆኗ ምክንያት ከእስራኤል ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመመሥረቷ ነው። ይህ ወዳጅነት ሠላሳ ዓመታት ያስቆጠረና እስራኤልንም በብዙ መልኩ የጠቀመ ነው።

አዘርባጃን ከእስራኤል ጋር ያላት ግንኙነት ከኢራን በኩል በርካታ ቀጥተኛ ዛቻዎችና አንዳንዴም የውክልና ጥቃቶች እንዲደርስባት ያደረገ ነው። ከዚህም ሌላ፤ እስራኤልን ከማጥቃት አዘርባጃንን በቀጥታ ማጥቃት የተሻለ ነው የሚል ንግግር ከኢራን በኩል የተሰማበትም ሁኔታ አለ። ለምሳሌ የሐማስ መሪ የነበሩት ኢስማኤል ሐኒያ በተገደሉበት ጊዜ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ እስራኤልን በቀጥታ ከማጥቃት አዘርባጃንን ዒላማ ማድረግ ይገባል ብለው ነበር።

በሌላ በኩል አዘርባጃንን በስተደቡብ ምዕራብ የምታዋስናትን አርሜኒያን በመጠቀም ኢራን አዘርባጃንን አጥቅታለች። ለምሳሌ አርሜኒያና አዘርባጃን ደም በተቃቡበት የናጎሮ ካራባህ የድንበር ጦርነት ኢራን ለአርሜኒያ ቀጥተኛ ድጋፍ በማድረግ አዘርባጃንን ያቆሰለ ተግባር ፈጽማለች። በዚህ ጦርነት አዘርባጃን በአሸናፊነት እንድትወጣ በማድረግ በኩል እስራኤል ከፍተኛውን ሚና ተጫውታለች።

አዘርባጃን ከሶቪየት ኅብረት ከወጣች በኋላ ነጻ አገር ሆና ስትቋቋም ወዲያው ዕውቅና ከሰጧት አገራት መካከል አንደኛዋ እስራኤል ነች። አዘርባጃን ከኢራን ጋር ለዘመናት ለቆየው የድንበር ግጭት መሢሕ ትሆነኛለች ብላ የተማመነችው በእስራኤል ሲሆን በዚያን ጊዜ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት የዚያን ጊዜውን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይትዛቅ ራቢንን ከኢራን ታደጉን ብለው ላቀረቡት ጥያቄ ራቢን ቃል ገብተው ነበር፤ እስካሁንም ድረስ አዘርባጃን ከእስራኤልን የጸጥታና የደኅንነት ብቃትና ልምድ ተጠቃሚ ስትሆን ቆይታለች።

ነዳጅ አዘርባጃን ለእስራኤል በዋነኛነት የምታቀርበው የውለታ ማስጠበቂያ ሸቀጥ ሲሆን እስራኤል ደግሞ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሣሪያና የሚሊታሪ ቴክኖሎጂ ለአዘርባጃን ታቀርባለች። እስራኤል ወደ አገሯ ከምታስገባው ነዳጅ 55 በመቶው ከአዘርባጃን የሚመጣ ነው፤ አዘርባጃን ወደ አገሯ ከምታስገባው የጦር መሣሪያ 69 በመቶው ከእስራኤል የሚመጣ ነው። በናጎሮ ካራባህ ጦርነት አዘርባጃንን አሸናፊ እንድትሆን ያደረጋትን ድጋፍ ያደረገችው እስራኤል ሲሆን የቱርክ ድጋፍም በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በዚያኛው ወገን አርሜኒያንን በጦር መሣሪያ ስትደግፍ የነበረችው ራሺያ ነበረች።

አርባጃን ካላት የጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታና ኃያላኑ የሚፋጠጡባት የፖለቲካ ዐውድማ ከመሆኗ አንጻር አሜሪካ ከአዘርባጃን ጋር ጠንካራ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እንድትመሠርት በአሜሪካ የሚገኙ ይሁዲዎች ግፊት እያደረጉ ነው። በተለይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የእስራኤል ወዳጅ እንደመሆናቸው አሜሪካ ከአዘርባጃን ጋር በምትመሠርተው ግንኙነት ኢራንን ቀለበት ውስጥ ማስገባት ትችላለች፤ በአዘርባጃን በኩል በማዕከላዊ ኤዢያ አገራት ጠንካራ መልሕቅ መጣል የሚያስችል ይሆናል፤ በተለይ የማዕከላዊ ኤዢያ አገራት በማዕድናት የበለጸጉ በመሆናቸው አሜሪካንን በእጅጉ ተጠቃሚ ያደርጋታል የሚል ማሳመኛ የአሜሪካ ይሁዲዎች በማቅረብ እስራኤልን ለመጥቀም እየወተወቱ ይገኛሉ።

ኢራን በቀጥታ የማታገኛትን አዘርባጃንን በውክልና በኤርትራ በኩል ለማግኘት እየጣረች እንደሆነ በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ኤርትራም ይህ ግንኙነቷ ዋጋ የሚያስከፍላት ከሆነ ለዘመናት የኢራን ወዳጅ በመሆኗ የምትከፍለው መስዋዕትነት እንደሆነ አድርጋ የወሰደችው ይመስላል።

ባለፈው ዓመት የኢራን ፕሬዚዳንት በመሆን ማሱድ ፔዜሽኪያን ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ መሐመድ ተገኝተው ነበር። በኤርትራ መገኘት የተደሰቱት አዲሱ የኢራን ፕሬዚዳንት ማሱድ “የኢራን እስላማዊ ሪፑብሊክ ያላትን ልምድ ለኤርትራ ለማስተላለፍና ብቃቷንም ለማጋራት ዝግጁ ነች” በማለት ነበር የገለጹት።

በአንጻሩ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ከመቼውም የበለጠ ግንኙነት እያደረገች ትገኛለች። የሁለቱ አገራት ግንኙነት የተጀመረው እኤአ በ1992 ዓም ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሁለቱ አገራት እጅግ የጠበቀ ወዳጅነት እንደመሠረቱ የተለያዩ ኩነቶች ያስረዳሉ።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን አስከትለው በአዘርባጃን ኢፊሴላዊ ጉብኝት አድርገዋል። በዋንኛነት የተጠቀሰው የዲጂታል ሥርዓትን ከአዘርባጃኑ ASAN፡ Azerbaijan Service and Assessment Network ለመማርና በኢትዮጵያ ለመተግበር ነው።

ባለፈው ኅዳር 5 (Nov 14, 2024) የኮፕ29 (COP29 የአካባቢ ጥበቃ ዓለምአቀፋዊ ስብሰባ) በአዘርባጃን ሲካሄድ በሥፍራው የተገኙት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከአዘርባጃኑ ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደው ነበር። በውይይቱ የASAN አሠራር ወደ ኢትዮጵያ ስለማምጣት እንዲሁም በዓለምአቀፍ ድርጅቶች፣ በታዳሽ ኃይል፣ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ የተገለጸ ነበር። ከዚህ ውጪ ግን ውይይቱን ለየት ያደረገው ጉዳይ ወደ አቡ ዳቢ ይጓዙ የነበሩ ሦስት የአዘርባጃን መርከቦችን ኤርትራ ካገተች ከሰባት ቀን በኋላ መሆኑ ነው።

ከአንድ ወር በፊት የአዘርባጃኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊዬቭ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ሲሆን የጉብኝታቸውም ዋና ዓላማ የኢትዮ-አዘርባጃንን ሦስተኛውን የፖለቲካ ምክክር ከሚኒስትር ደኤታ ምስጋኑ አረጋ ጋር በመሆን ለመምራት ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ራፊዬቭ ከሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ ከካቢኔ ሚኒስትሮች ጽ/ቤት ኃላፊዋ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ፣ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት አካሂደዋል። እስካሁን በተደረጉት ውይይቶች ከአዘርባጃን በኩል የሚሰማው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን የጎላ የበላይነት ተጠቃሚ የመሆን ነው።

በያዝነው ዓመት (2017) ጥቅምት 28 (November 7, 2024) የካስፒያን የባሕር አገልግሎት የሚያሠራቸው ሦስት የአዘርባጃን መርከቦች (CMS Pehlеvan, CMS Igid, and CMS-3 vessels) የስዊዝ ካናልን አልፈው የአዘርባጃንን ሠንደቅ እያውለበለቡ ወደ አቡ ዳቢ (የተባበሩት አረብ ኤምሬት) ሊሄዱ ሲሉ ቀይ ባሕር ላይ በኤርትራ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። መርከቦቹ ባጋጠማቸው የአየር መበላሸት ምክንያት ነበር ወደ ኤርትራ የባሕር ወሰን የገቡት ተብሎ ነው የተነገረው።     

ከአዘርባጃን በኩል የወጣው ኦፊሴሊያዊ ሰነድ እንደሚያመለክተው መርከቦቹ የሚያልፉበት መንገድ አደገኛ የባሕር ዘራፊዎች (ፓይሬትስ) ያሉበት በመሆኑና መስመሩ ለደኅንነታቸው አደገኛ እንደሆነ ስለተነገራቸው ደኅንነታቸው የሚጠበቅበትን መስመር መምረጥ ግድ ሆኖባቸዋል። በዚህ ወቅት በኤርትራ የባሕር መስመር ሲያልፉ በተፈጠረ የአየር መዛባት መስመሩን ጥሰው እንዲገቡ ወደ መገደድ ሲደርሱ VHF-16 channel የተባለውን ዓለምአቀፍ የግንኙነት መንገድ በመጠቀም ወደ ኤርትራ ጥሪ ቢያስተላልፉም ምንም ምላሽ አላገኙም።

ከአሰብ በቅርብ ርቀት መርከቦቹ በኤርትራ የታገቱበት ቦታ

ይፋ የሆነው ሰነድ እንደሚያመለክተው ወደ ኤርትራ ወሰን መግባት የተገደዱት መርከቦች “ሐሙስ ጥቅምት 28 ወደ 10፡06 አካባቢ የኤርትራ ባሕር ኃይል 13°23′ North Latitude and 042°39′ East Longitude መገናኛ ላይ (ወደ አሰብ አካባቢ) ሦስቱንም መርከቦች በቁጥጥር ሥር አውሏቸዋል። ከኤርትራ የተሰጠው ምክንያት መርከቦቹ አቅጣጫቸውን ቀይረው በኤርትራ ባሕር ኃይል የተሰመረውን መስመር በማለፋቸው ነው” የሚል ነው። ባሕር ኃይል የተባለው ከመርከቦቹ ለቀረበለት ጥሪ ለምን ምላሽ እንዳልሰጠ ምንም ያለው ነገር የለም። በመርከቦቹ ውስጥ 18 የመርከቡ ሠራተኛ የአዘርባጃን ተወላጆች፣ 6 ደግሞ የሌላ አገራት ተወላጆች በድምሩ 24 ሰዎች እንዳሉ ሰነዱ ያብራራል።

የዛሬ 25 ዓመት ገደማ አዘርባጃን የናጎሮ ካራባህን ግዛት በተመለከተ ከአርሜኒያ ጋር ጦርነት በገጠመችበት ወቅት በስድስት ሳምንት (44 ቀናት) ጦርነቱ በአዘርባጃን ድል አድራጊነት እንዲጠናቀቅ ያደረገው ዋነኛው ነገር የወታደራዊ ድሮን ቴክኖሎጂ እንደሆነ ይነገራል። በወቅቱ አርሜኒያ ሩሲያ ሠራሽ ድሮኖች የተጠቀመች ሲሆን አዘርባጃን ግን ከእስራኤልና ከቱርክ ያገኘቻቸውን ድሮኖች በማጣመር ተጠቅማ የአየር የበላይነት ሊኖራት ችሏል። የአዘርባጃን ድሮኖች ዒላማ በመለየትና በማጥቃት፣ በመከታተል፣ በመግደል ወዘተ ልዩ ብቃት እንደነበራቸው የስትራቴጂክና የዓለምአቀፍ ጥናት ማዕከል ሰነድ ያብራራል።

ከእስራኤል በቢሊዮን የሚቆጠር የጦር መሣሪያና የሚሊታሪ ቴክኖሎጂ ድጋፍ የምታገኘው አዘርባጃን ባለፈው ዓመት አንድ ትልቅ የድሮን ማሠልጠኛና መጠገኛ ተቋም ከፍታለች። ቱርክ ሠራሽ Akinci drone ድሮኖ ጋር በተያያዘ የተሠራው ተቋም የአዘርባጃን ወታደራዊ ዓቅም እጅግ ከፍ የሚያደርግና ከድሮን ጋር በተያያዘ ከውጭ የምታስመጣውን በአገር ውስጥ ቴክኖሎጂ ለመለወጥ ታስቦ የተደረገ መሆኑ የወጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ እኤአ በ2028 የአዘርባጃን የመከላከያ በጀት 4 ቢሊዮን ዶላር (ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ) ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።  

  • Akinci drone
  • የአዘርባጃን የድሮን ማሠልጠኛና መጠገኛ ተቋም
  • Akinci drone

የአዘርባጃን የድሮን ማሠልጠኛና መጠገኛ ተቋም

በአሜሪካ የሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ይሁዲዎች ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ምክንያት በማድረግ አሜሪካ ከአዘርባጃን ጋር ግንኙነት ብትፈጥር በእጅጉ ትጠቀማለች እያሉ መወትወት ከጀመሩ ቆይተዋል። በተለይ አዘርባጃን ከእስራኤል ጋር የመሠረተችው የጠበቀ ግንኙነትና የእስራኤል “ምርጥ ወዳጆች” ከሚባሉ ሙስሊም አገራት መካከል አንዷ መሆኑ ለአሜሪካ መደላድሉ የተሠራ ነው ይላሉ። ስለዚህ ጥሩ ግንኙነት መጀመሪያ “በአብርሃም ስምምነት” አዘርባጃንም እንድትካተት በማድረግ እንደሆነ ይጠቁማሉ።

“የአብርሃም ስምምነት” (Abraham Accords) የሚባለው በአሜሪካ አደራዳሪነት እስራኤል ከአረብ አገራት ጋር ነገሮችን የማርገብና መሬት የማውረድ ስምምነት ነው። ይህም እኤአ በ2020 ዓም በኋይት ሐውስ እስራኤል ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ከባሕሬይን ጋር የተስማማችው ነው። በቀጣይ ሞሮኮና ሱዳን ሌሎች ፈራሚ አገራት ሆነዋል።

ትራምፕ በኋይት ሐውስ እስራኤል ጠ/ሚ/ር ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ከባሕሬይን ው/ጉ/ሚኒስትሮች ጋር

ይህንን እንደ መነሻ የሚጠቅሱት አሜሪካዊ ይሁዲዎች ይኸው የአብርሃም ስምምነት ለአዘርባጃን፣ ለካዛክስታን እና ለዑዝቤክስታን በተለይ ግን የእስራኤል ምርጥ ወዳጆች ለተባሉት ለሁለቱ አገራት መዘርጋት አለበት፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ተመልሰው ወደ መሪነት የመጡበትን ዕድል መጠቀም አለባቸው፤ ይህም ዞሮ ዞሮ የእስራኤል ወዳጅ አገራትን በመጠቀም አሜሪካንን በአካባቢው የበላይነት እንዲኖራት፣ ኢራንን በቅርብ ርቀት እንድትከታተል፣ አሜሪካንን በነዳጅና በሌሎች የኢኮኖሚ ጉዳዮች በብዙ እንድትጠቀም የሚያስችላት ነው የሚል መሟገቻ ሀሳብ ከሚያቀርቡት ቀዳሚው የመካከለኛው ምስራቅ ኤክስፐርት የሆኑት ጆሴፍ ኤፕስቲን ናቸው።

እንግዲህ ኤርትራ መርከብ አግታ እሰጥ አገባ ውስጥ የገባችው ከዚህች አገር አዘርባጃን ጋር ነው። ከኢትዮጵያ ጋር እጅግ የጠነከረ ወዳጅነት የመሠረተችው አዘርባጃን በእስራኤል በጥብቅ ከመደገፏ አንጻር የኢራን ወዳጅ የሆነችው ኤርትራ የያዘችው ዓቋም ዋጋ የሚያስከፍላት ሊሆን ይችላል።

በቅርቡ የእስራኤል ታዋቂ ጋዜጣ (ሐሬትዝ) ላይ ኤርትራ ከኢራን ጋር ገጥማ በእስራኤልና በአሜሪካ ጥቅም ላይ ያነጣጠረ ተግባር ላይ መሰማራቷን የሚገልጽ ትንታኔ ማተሙ አይዘነጋም። ከዚህም ባሻገር ኤርትራን ከሰላሳ ዓመት በላይ የተቆጣጠረው የኢሳያስ አፈወርቅ አገዛዝ የሽብር ቡድኖችን በውክልና በማሰለጥንና በማስታጠቅ ከነበረው የቀደሞ ታሪክ አንጻር አሁን የአዘርባጃንን መርከቦችና መርከበኞች ከነጭነታቸው ማገቱ ሸምቀቆውን እንደሚያጠብቅ ይገመታል።

ይህ አጋጣሚ በተደጋጋሚ በኢሳያስ አፈወርቅ ሤራና የውክልና ደባ ሰለባ ለሆነችው፣ ለዚህም ብዙ ዋጋ ስትከፍል ለኖረችውና ሕጋዊ ወደቧን ለተዘረፈችው ኢትዮጵያ እንደ ልዩ አጋጣሚ እየታየ ነው። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ “በአፍሪካ ቀንድ ሌላ ግጭት እንዳይከሰት ለማድረግ አሁን እርምጃ መውሰድ ይገባል” (To avoid another conflict in the Horn of Africa, now is the time to act) በሚል ርዕስ በአልጀዚራ ላይ በታተመው ሰፊ ጽሑፍ በኤርትራ ላይ እርምጃ የመውሰጃው ጊዜ አሁን ነው ሲሉ ለዓለም የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ፣ ለአሜሪካ፣ ለቻይናና ለአውሮጳ ኅብረት ያቀረቡት ጥሪ ከላይ የተባለውን የሚያጎላ ይሆናል።

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ “ጦርነት ለኤርትራ የገቢ ምንጭ ነው” ባሉበት ሰፊ ማብራሪያቸው “ግጭት እዚህና እዚያ መፍጠር፣ አማጺያንን እና ገንጣዮችን መርዳት ወይም መንግሥታት ወደ ጦርነት እንዲገቡ፣ በቀጣናው መከፋፈል እንዲፈጠር ማድረግ የኤርትራ መንግሥት ለኅልውናው ሲል የሚፈጽመው ተግባር ሆኗል። … የምስራቅ አፍሪቃ ቀንድ ከታወከ መካከለኛው ምስራቅና መላው አውሮጳ የትርምሱ ዋንኛ ሰላባ ይሆናሉ። ስለዚህ ጫና ለማሳረፍ ጊዜው አሁን ነው” የሚል የዲፕሎማሲ ጫና ጥያቄ አቅርበዋል። እንደቀድሞ የኢሳያስን አገዛዝ ወደ ማዕቀብ ከርቸሌ እንዲመለስ የጠየቁበት አግባብ ዝም ብሎ የቀረበ ጥሪ እንዳልሆነም ጉዳዩን የሚከታተሉ ይገልጻሉ።

የታገቱት መርከቦች የአዘርባጃን ጉዳይ ብቻ ሳይሆኑ የእስራኤልም ናቸው። ኤርትራ ከኢራን ጋር ካላት የቀረበ ግንኙነት አንጻር በመርከቦቹ የተጫነውም ሆነ የኤርትራ ድርጊት እስራኤልን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የሚነካ ነው። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ካላት የሻከረ ግንኙንትም ይሁን ከኢራን ጋር ካላት ፍቅር በእነዚህ መርከቦች ላይ የምትወስደው ውሳኔ ግን ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል ይገመታል። መርከቦቹን ከመልቀቅ መዘግየቷም አንዱ ተጠቃሽ ይህ ይሆናል። መርከቦቹን በሰላም እንኳን ብትለቀቅ የፈጸመችው የባሕር ላይ ውንብድና ለአካባቢው የበለጠ የስጋት ምክንያት ያደርጋታል።

የቀጣናውንና ጂኦፖለቲካውን በጥሞና የቃኘ አካሄድ መከተል ይህ ክስተት ለኢትዮጵያ በርካታ በረከቶችን ይዞ እንዲመጣ የሚያስችል ነው። በአንድ በኩል ኤርትራ ወሳኝ የሆነውን የባብኤል መንደብ ሰርጥን በመቆጣጠር መቀጠል በቀጣናው የጦር ቤዝ ለመሠረቱ አገራት ሰላም የሚነሳ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጥበት ኃያላኑን የማሳሰብና ወደ ውሳኔ የማድረስ ሥራ ነው። ሌላው ኤርትራ ከኢራን ጋር ያላት ግንኙነት ከባሕር መንገዱ አልፎ ኢራን ጠላት የምትላቸውን አገራት በእጅ አዙር የምታጠቃበት መንገድ ከፋች መሆኑን በማሳወቅ፤ ሌላና ወሳኙ ደግሞ ሰርጡን እንደ ኤርትራ ዓይነት ግጭት ቀለቡ የሆነ አገር እንዲቆጣጠረው ከመፍቀድ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ኖሯት የሰርጡ ሚዛን አስተካካይ እንድትሆን ድጋፍ ለማሰባሰቢያ መጠቀም ነው። ከሁሉ የሚልቀውና ዘላቂ የሆነው ግን ከበረሃ ውንብድና ያለ ሕዝብ ይሁንታ ከሠላሳ ዓመት በላይ በሥልጣን የቆየውን የኢሳያስ አገዛዝ ዕረፍት እንዲወስድ በአገር ውስጥ ኢሳያስ ሲወገድ የሚከሰተውን ክፍተት ሊተካ የሚችል ኃይል ከማዘጋጀት ጀምሮ በሁሉም መስክ የማሳመን ዘመቻ ለማድረግ በር ከፋች በመሆኑ ነው። 

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

NEWSOPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ትልቅ ጦርነት በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ ይችላል”
የ17 አመት ታዳጊ አዶናይት ይሄይስ ላይ የአስገድዶ መድፈርና የግድያ ወንጀል የፈፀመው የሞት ቅጣት ተወሰነበት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2