ትናንት ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል። በ power politics ፓርቲውና መሪው አቢይ አህመድ የደረሱበት ደረጃ power consolidation ልንለው እንችላለን። የዛሬ ሁለት አመት ” እየመጡ ነው ” ነጠላ ዜማ የለቀቁልን ሰዎች የከፋ ተስፋ ሙቁረጥ despair ውስጥ ያሉ ይመስላል።
የዛሬ ሁለት አመት ተቃዋሚው ጎራ አራት ኪሎን በሳምንታት ዕድሜ ውስጥ እጁ እንደሚያስገባ እርግጠኛ ነበር ። የድል ዜና ፣ ጎሮ ወሸባዬ የዩቱይብ ገጹን አጠለቅልቆት ነበር ። ሁሌም እንደማደርገው ወላጅ እናቴን ለመጠየቅ ወርሀ February ወደ ሸገር አቀናለሁ ። የዛሬ ሁለት አመት ከራይድ ሹፌሮች አንስቶ እስከ እነ Radison Blue እና እማሆይ አሰገደች እልፌ ሆቴሎች ንጽህና ክፍሎች ሳይቀሩ ” እየመጡ ነው ! ” ጮክ ተብሎ ይነገር ይጻፍባቸው ነበር።
ያኔም ዛሬም ለአቢይ አህመድ ተቃዋሚዎች ያቀረብንላቸው ጥያቄ አንድ ብቻ ነበር ። ” ከሰበር ዜና ሜጋፎኖቻችሁ ባሻገር ሰውየውን ጥላችሁ ሀገር የምትመሩበት ድርጅት አላችሁን ? ” የሚል ነበር ። ዕድሜ ብዙ ስላስተማረን ዩዩቱይብ ጎሮ ወሸባዬና መሬት የረገጠ ድርጅታዊ ንቅናቄን መለየት ወትሮም ዛሬም ብዙ አይቸግረንም።
ትናንት ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል። በ power politics ፓርቲውና መሪው አቢይ አህመድ የደረሱበት ደረጃ power consolidation ልንለው እንችላለን። የዛሬ ሁለት አመት ” እየመጡ ነው ” ነጠላ ዜማ የለቀቁልን ሰዎች የከፋ ተስፋ ሙቁረጥ despair ውስጥ ያሉ ይመስላል። ትግላችን የሚሉትን እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ ጨከን ብለው ለመመርመር ፣ የአራት ኪሎው ፕሮጄክት ለምን የዳግም ትንሳኤ ንግርትን ያህል ራቀ ሲሉ መጠየቅን ፈርተዋል። ይልቅ ቀላሉ መንገድ መርጠው የአቢይ አህመድን ጃኬት ንጣት ፣ የአደም ፋራህን ቁመት ርዝመት በኢትዮ ፎረምኛ ልብወለዳዊ ትርክት መንገድ ይተርኩት ፣ ይበልቱት ይዘዋል።
ፖለቲካ በሆነ መላ የመንግስት ስልጣን መንበርን ጨብጠህ ህሳቤዎችህን እውን ለማድረግ የምትጥርበት ሂደት ነው። ፖለቲካ በራስህ ህልም/ተረክ የምትዳክርበት ፣ እንደ ትግርኛ ጭፈራ ዝንተአለም በአንድ እሽክርክሪት የምትዞርበት ሂደት አይደለም። ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ቅንጦት በሆነባት ኢትዮጵያ አየሩን በአንተ ትርክት ብትሞላው ምድሩ ላይ ድርጅት ከሌለህ ጉንጭ አልፋ ድካም ነው። የማህበራዊ ሚዲያውን ጉርምርምታም ከብሶት አደባባይነት አልያም እንደ ለንደኑ Hyde Park speakers corner ያለፈ ከዲስኩር መወራወሪያ መድረክነት ያለፈ ፋይዳ የለውም ።
እአሁንም ምክራችን አንድ ነው። ከ despair ውጡ ፣ ራሳችሁን ፣ ትግላችን የምትሉትን ንቅናቄ መነሻ መንስኤን ሀቀኝነት ፣ ትልሙን ፣ አደረጃጀቱን ደፈር ብላችሁ መርምሩ ። ያን ማድረግ ተስኗችሁ የራሳችሁ ሰበር ዜና ምርኮኛ መሆንን ከመረጣችሁ ፣ ” እየመጡ ነውን ” መሬት ላይ ካለው እውነታው ውጪ በ remix መገረብ ካሻችሁ ፣ መጨረሻችሁ ትናንት አምርራችሁ ትጠሏቸው የነበረው ህወሃት ፣ ሻዕቢያና ኦነግ ሸኔ እግር ስር ወድቃችሁ ወደ ናጽነት መንገድ ውሰዱን ስትሉ መለመን ይሆናል።
Opinion by Samson Michailovich fb

