Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ዶ/ር አንዷለም በባህር ዳር በሶስት ታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ መኪናቸው ውስጥ ተገደሉ፤ ባልደረባቸው ከግድያ አመለጡ
News

ዶ/ር አንዷለም በባህር ዳር በሶስት ታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ መኪናቸው ውስጥ ተገደሉ፤ ባልደረባቸው ከግድያ አመለጡ

Ethioreview newsEthioreview news—February 2, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በባህር ዳር ዛሬ የተሰማው የሞት ዜና መረን የወጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማሳያ ነው። የዓይን እማኞች እንዳሉት ሶስት ዩኒፎርም የሚመስል ነገር የለበሱ አንጋቾች ናቸው ዶክተር አንዷለም ከስራ ሲወጡ ጠብቀው መኪናቸው ውስጥ የገደሉዋቸው። ባልደረባቸው መኪናቸው በተመሳሳይ በጥይት ብትመታም አምልጠዋል። ይህ አስደንጋጭ ዜናው ለሕዝብ ይፋ የሆነበት አግባብም ይህንኑ መረን በወጣ ፖለቲካ ፍርሃቻ የታጀበ ይመስላል።  “ ዜናው አንባቢ ይፍረደው” አይነት እንደሆነ አስተያየት የሰጡ አሉ።

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊቲ ሃኪም፣ ተመራማሪ፣  መምህር እና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት  ዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ተገድለዋል። ተገደሉ የተባሉት ባልታወቁ ኃይሎች ነው። ዶክተር አንዷለም ብዙ መስራትና ህዝብን ማገለገል የሚችሉ፣ ተተኪ ማፍራት ላይ የተሰማሩ ባለሙያና መምህት ነበሩ። 

|ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው በተወለዱ በ37 ዓመታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ ሞት የተሰማንን መሪር ሃዘን እየገለፅን ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን” ሲል የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ገልጿል። 

“ዶ/ር አንዷለም በዩኒቨርሲቲያችን፣ ብሎም በአገራችን  አሉን ከምንላቸው በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በአጋጠማቸው ግድያ ህይወታቸውን አጥተዋል።  በሐኪማችን ላይ ያጋጠመውን ግድያ እና በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ያልተገባ መሰል ድርጊት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ ያወግዛል። በየትኛውም አካል ሊሰነዘር የሚችል ይሄን አይነት መሰል ድርጊትም ለአገርም ሆነ ለወገን አጉዳይ እንጅ አንዳች የሚጨምር ነገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው” ነው ሲል ዩኒቨርስቲው ሃዘኑን አስታውቋል። 

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ግድያው ባልታወቁ ሰዎች መፈጸሙ ቢገለጽም ዩኒቨርስቲው ባስራጨው የሃዘን መግለጫው ተግባሩን በጥብቅ ኮንኗል።  “ዶክተር አንዷለም ተተኩሶበት ተመትቶ የተገኘው መኪናው ውስጥ ነው ። አንድ ሀኪማችንም ተተኩሶበት መኪናው ሁለት፤ ሦስቴ ተመትቶታል” የጤና ኮሌጁ ሰራተኞች እማኝነታቸውን ገልጸዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው ጥር 24/2017 ዓ.ም ምሽት 1፡30 ሰዓት ገደማ ዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ሥራ ቆይተው ጥበብ ግዮን ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እየሄዱ ባለበት ወቅት በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እስካሁን በውል ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን እንድተናገሩ አሚኮ ጽፏል።

ሁለት ተሽከርካሪዎች ተከታትለው እየሄዱ ባለበት ወቅት አንደኛው ተሽከርካሪ ሲያመልጥ ዶክተር አንዱዓለም በነበሩበት ተሽከርካሪ ላይ በተደጋጋሚ ጥይት በመተኮስ የግድያ ወንጀል መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ ድርጊቱ እንደተፈጸመ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወደ ቦታ በመሄድ የማጣራት ሥራ እየሠራ መኾኑን ነው የተናገሩት፡፡ በሥፍራው የተገኙ የቴክኒክ ማስረጃዎችን የማንሳት እና ሌሎች ሥራዎች መሠራቱን ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ ድርጊቱን ማን ፈጸመው እንዴት ተፈጸመ የሚለውን ለመለየት ሥራ ላይ መኾኑን ነው ጅጃላፊው አመልክተዋል፡፡ ዶክተር አንዱዓለም እያሽከረከሩ በነበረበት ወቅት በተተኮሰ ጥይት መገዳላቸውንም አረጋግጠዋል፡፡ ፖሊስ አጥፊዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ጥረት እያደረገ መኾኑንም አስታውቋል፡፡

ፖሊስ እንዳለው እማኞችም በተመሳሳይ  ዶክተር አንዷለም መኪናቸውን እያሽከርከሩ ሳለ በተጠቀሰው ቦታ ሲገልጹ፣ ተኩስ ተከፍቶባቸዋል።

ለቲክቫህ እማኝነታቸውን የሰጡትና ስማቸውን የደበቁ የኮሌጁ ባልደረቦች ስለገዳዮቹ ለጊዜው በውል የታወቀ ነገር እንደሌለ ገልጸዋል። ከዶ/ር አንዷለም በፊት በራሱ ተሽከርካሪ ሲጓዝ በነበረ ሌላ ሀኪም ላይ በተመሳሳይ ለመግደል ጥይት ቢተኮስበትም ሊያመልጥ ችሏል። 

እነዚህ ምስክሮች እንዳሉት ግድያው ሲፈጸም ‘ሦስት የሚተኩሱ ሰዎች እንደነበሩ አመልክተዋል። መለየት ባይችሉም “ዩኒፎርም ነገር” ሲሉ የገለጹትን ለብሰው ነበር።

በጥበበ ግዮን ግቢ ህክምና ጤና ሳይንስ ኢንተርን ሀኪሞች በበኩላቸው፣ “ ዶክተር አንዷለም ከከተማ ከሥራ ውሎ ሲመለስ ምሽት ላይ ነው የተመታው። ግን ማን እንደመታው የተረጋገጠ ነገር የለም ” ሲሉ ነግረውናል።

“ አስከሬኑም ለፓሊስ ተደውሎ ነው ማታ የተነሳው ” ያሉት ኢንተርን ሀኪሞቹ፣ “ አሁን ሀኪሞቹም፣ ነዋሪዎችም ሁሉም የባሕር ዳር ዩኑቨርሲቲ ተማሪዎችና ሠራተኞች ሀዘኑን እየተካፈልን ነው ያለነው ” ብለዋል።

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶክተር መንገሻ  ከሰዓታት በፊት በሰጡን ቃል “ አስከሬን ይዘን ከቤት ወደ ቤተክርስቲያን እየወጣን ነው ” ብለዋል። 

ስለገዳዮቹ ማንነት የታወቀ ነገር እንዳለ የጠየቅነው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጸጥታ ክፍል በሰጠን ምላሽ፣ “ ግድያው ከግቢ ውጪ ስለተፈጠረ ምንም ያወቅነው ነገር የለም ” ብሏል።

“ ያወቅነው መረጃ የለንም። እኛም እንደማንኛውም ሰው መሞቱን ብቻ ነው የሰማነው ” ሲል አክሏል።

የሚመለከታቸውን የከተማውን የጸጥታ አካላት ለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ የምናቀርብ ይሆናል።

ዶክተር አንዷለም ዳኘ የዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስፔሻሊስት፤ የጉበት፣ የቆሽት፣ የሀሞት ጠጠር መስመር ሰብ ስፐረሻሊስት ሀኪም፣ እንዲሁም የልጆች አባት ነበሩ። የሚያውቋቸው ደግ፣ ሩህሩህ፣ ለሁሉም ምሳሌ የሚሆኑ፣ መልካም ሰው እንደነበሩ ተናግረዋል። ኮሌጁ ጉዳቱ ለአገርና ለህዝብ እንደሆነም አመልክተዋል። 

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ካናዳ ለጉልበተኞች አትበረከክም”
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ለትግራይ ህዝብ በዋናነትም ለትግራይ ልሂቃን የ”አስቡበት” መልዕክት አስተላለፉ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2