Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  በሀገራችን የዓይን መነጽር ጥራትና ደረጃን የሚቆጣጠር አካል የለም
SOCIETY

በሀገራችን የዓይን መነጽር ጥራትና ደረጃን የሚቆጣጠር አካል የለም

Ethioreview newsEthioreview news—March 30, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በሀገር አቀፍ ደረጃ የዓይን መነጽር ጥራትና ደረጃን የሚቆጣጠር አካል አለመኖሩ ተገለጸ። በሀገር አቀፍ ደረጃ የዓይን መነጽር ጥራትና ደረጃን የሚቆጣጠር አካል አለመኖሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ህክምና ትምህርት ቤት የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ሳዲቅ ታጁ አስታወቁ፡፡

ዜጎች ጥራቱ የተረጋገጠ መነጽር ስለማያገኙ ለከፋ የዓይን ጤና ህመም እየተጋለጡ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ዶክተር ሳዲቅ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ መነጽር በዓይን ጤና ሥራ ውስጥ ልክ እንደ መድኃኒት የሚያገለግል የሕክምና ቁስ ነው፡፡

ሆኖም በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደ መድኃኒት ሁሉ ጥራቱንና ደረጃውን የሚለይለት አካል የለም፤ ቁጥጥርም አይደረግበትም፡፡

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022

በዚህም ምክንያት ዜጎች ጥራቱ የተረጋገጠ ምርት ስለማያገኙ ለተደጋጋሚ ወጪ እና ለተጨማሪ የዓይን ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

የመነጽር ጥራትና ደረጃ ቁጥጥር ባለመኖሩ ሰዎች በትዕዛዝ የተሰጣቸውን መነጽር አውቀው አይገዙም ያሉት ዶክተር ሳዲቅ፤ በዝቅተኛ ዋጋ ያገኙትን እየገዙ ለተጨማሪ የዓይን አደጋ ተጋላጭ እየሆኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የመነጽርን ጥራትና ደረጃ የሚቆጣጠር አካል ባለመኖሩ አሁን ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ መነጽር ቤቶች እና በየመንገዱ መነጽር የሚያዞሩ ከመበራከታቸው ባሻገር እንዳሻቸው ሠርተውና ቆርጠው እንዲሁም ዋጋ ተምነው ለተጠቃሚው የሚያቀርቡ ሆነዋል፡፡

ይህ ደግሞ በርካቶችን ለከፋ የዓይን ጤና ችግር እያጋለጣቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከዓይን ጤና ችግር ጋር በተያያዘ ብቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ እድሜያቸው እስከ 16 የሚደርሱ ልጆች ከ10ሩ አንዱ መነጽር እንደሚያስፈልገው፤ በከተሞች አካባቢም 20 በመቶ የሚሆኑ ልጆች መነጽር የግድ መጠቀም እንዳለባቸው በጥናት መመላከቱን የጠቆሙት ዶክተር ሳዲቅ፤ ማንኛውም እድሜው ከ35 ዓመት በላይ የሆነ ሰው መነጽር መጠቀም እንዳለበት አስታውሰዋል፡፡

በትዕዛዝና በተፈጥሮ የግድ መነጸር መጠቀም ያለባቸው ዜጎች እንደ ሀገር በርካታ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የመነጽሮች ጥራትና ደረጃን አለመቆጣጠር የዓይን ጤና ችግርን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

እንደ ሀገር ይህ ጉዳይ ትኩረት ያለማግኘቱ ብዙዎችን ተጎጂ ያደረጋቸዋልና መንግስት ሊያስብበት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

አሁን ላይ ተጠያቂነት ያለበት አሰራርን በሕግ ማስቀመጥ ካልተቻለ በትንሹ ከ35 ዓመት በላይ ያሉት የማህበረሰብ ክፍሎች ለከባድ የዓይን ጤና ችግር ተጋላጭ እንደሚሆኑ ጠቅሰውም፤ ከአዋቂዎች ይልቅ መነጽር የሚያስፈልገው ልጆች በመሆናቸቸው እነርሱ ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራትም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የልጆች ዕይታ ቀድሞ መቀነስ ከአደጉ በኋላ ለመመለስ ያስቸግራል፡፡ በዚህም ልጆች ጥራትና ደህንነታቸው የተጠበቀ መነጽሮችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገበባል ብለዋል፡፡

እንደ ኢትዮጰያ የዓይን ሐኪሞች ማህበር እና እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዓይን ሕክምና ክፍል ከመንግሥት አካላት ጋር ንግግር እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ምርቱ ከቀረጥ ነጻ ገብቶ በአነስተኛ ዋጋ የሚቀርብበት እድል እንዲፈጠር እየተሠራ ስለመሆኑም አመላክተዋል፡፡

ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው መንግሥት በቻለው መጠን በመነጽር ሥራና የጥራት ደረጃ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

እንደዓለማቀፍ ጥናቶች መረጃ እ.አ.አ በ2050 በአነጣጥሮ ማየት ግድፈት ምክንያት ብቻ 50 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ መነጽር ይፈልጋሉ የሚሉት ዶክተር ሳዲቅ፤ ምንም አይነት የዓይን መነጸር የጥራትና የደረጃ ቁጥጥር በማይደረግባት ኢትዮጵያ ደግሞ ይህ ቁጥር የት ላይ ሊደርስ እንደሚችል መገመት አያዳግትም ነው ያሉት፡፡

ጥራትንና ደረጃን ከማስጠበቅ አንጻር ተቆጣጣሪ አካል መመደብ ላይ ትኩረት ማድረግ ከአሁኑ ይበጃል ሲሉም መክረዋል፡፡

ዋጋን ከማረጋጋት አንጻርም መድኃኒትን በሀገር ውስጥ ማምረት እንደተቻለ ሁሉ የዓይን መድኒት የሆነውን መነጽርንም በሀገር ውስጥ በመንግሥት አለያም በግል አጋርነት ማምረት ቢቻል መልካም እንደሆነ ዶክተር ሳዲቅ አስገንዝበዋል፡፡

በጽጌረዳ ጫንያለው ጋዜጣ ፕላስ

SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በትግራይ አዲስ መሪ ይሾማል፣ ታደሰ ወረደ ምክትል ሆነው ይቀጥላሉ፤ ወዲ አሸብር የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ይሆናሉ
“ስልጣን ወይም ሞት ብሎ የተነሳው ኋላቀር ቡድን ወደሌላ ዙር የጥፋት አዙሪት ሊያስገቡን ቋምጠዋል”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2