Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  POLITICS  ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ
POLITICS

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ

Ethioreview newsEthioreview news—March 4, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ ከየካቲት 22 እስከ የካቲት 24/ 2017 ዓ.ም. ሲያደርግ የነበረው ስብሰባ በድርጅቱ አሠራር ሒደት እና ወቅታዊ ሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በቀጣይ ስለሚኖሩ ድርጅታዊ ተግባራት ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

1)     ድርጅታዊ ጉዳዮች፤

1.1) የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ: በኢዜማ መተዳደርያ ደንብ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሲሆን የሥልጣን ዘመኑም 3 ዓመት መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ይህ ጉባኤ የሥልጣን ዘመኑ ሊገባደድ ጥቂት ወራት የቀረው መሆኑን ከግንዛቤ በመውሰድ ሥራ አስፈጻሚው በድርጅታዊ መተዳደሪያ ደንቡ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መሠረት  ጉባኤውን ለማካሄድ ወደ ዝግጅት እንዲገባ ውሳኔ አስተላልፏል።

1.2) የፓርቲ መዋቅሮችን ማጠናከር፡ ሰኔ 2013 ዓ.ም. ከተካሔደው 6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ወዲህ ባሉት ጊዜያት በፍጥነት ተለዋዋጭ የሆነው የቀጠናው እና የሀገሪቱ ፖለቲካ እና የጸጥታ ችግር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ተዳምረው ባለፉት ዓመታት የድርጅታችንን መዋቅሮች እና አባላት የታለመለትን ያህል የፖለቲካ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ ተግዳሮት ገጥሞን ቆይቷል። በመሆኑም ይህንን ችግር በሚያርቅ መልኩ ከፍ ያለ ትኩረት የሚሰጠው የድርጅት መዋቅር ግንባታ ሥራ አጠናክሮ መቀጠል ይደር የሚባል ተግባር እንዳልሆነ በመገንዘብ በዲጂታል ሥርዓት ማጠናከርን ጨምሮ ዘመኑ በሚፈቅደው ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ወስኗል።

1.3) የኢዜማ አካዳሚ እና ተከታታይ አቅም ማጎልበቻ ውይይቶች፡ ኢዜማ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ተቀዳሚ ተግባር ማኅበረሰብን ወደተሻለ ቦታ የሚያደርስ የጠራ አስተሳሰብ መያዝ፣ ይህን አስተሳሰብ መሬት ላይ ማውረድ የሚችል ዘመን ተሻጋሪ ድርጅታዊ መዋቅር መገንባት እንዲሁም በየጊዜው ተለዋዋጭ የሆኑ ሀገራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ስልታዊ በሆኑ ዘላቂ ግብ ላይ ተመስርተው እየተነተኑ ውሳኔዎችን ማሳለፍ የሚችሉ አመራሮችን ማፍራት መቻል ትክክለኛ የሆነው መንገድ ከመሆኑም ባሻገር ዘላቂ የሆነ የሕዝብ ይሁንታን ያስገኛል ብሎ  የሚያምን ፓርቲ ነው። ይህንን ሕልም በሀገራችን እውን ማድረግ ግን እንደሚታሰበው ቀላል የሚባል እንዳልሆነ በቅጡ ይረዳል፤ ረዥም ጊዜ እንደሚያስፈልገውም ይገነዘባል፡፡ በተለይ ልኂቃን የሚባሉት የሀገሪቱ ዜጎች በፖለቲካው ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማድረግ ያላቸው ተነሳሽነት ደካማ መሆን እና በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ሥልጣን በሃሳብ የበላይነት ሳይሆን በጡንቻ መፈርጠም ላይ የተመሠረተ መሆኑን የተቀበለ የአስተሳሰብ ውቅር የበላይነት መያዙ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ፖለቲካ ላይ የዳር ተመልካች እንዲሆኑ ከመግፋቱም በላይ አምባገነን የሆኑ ሥርዓቶችም በሥልጣን ኮረቻ ላይ ተፈናጥጠው ለመቆየት ምቹ ሁኔታ አድረገው እንዲወስዱት አድርጓል።

ይህንን አስተሳሰብም ሆነ አሠራር በሂደት ሊያርቅ በሚችል መልኩ የፖለቲካ አመራሮችን ማብቃት እንደ ተቀዳሚ ሥራ መውሰድ ይገባል። በዚህ ረገድ ኢዜማ አባላቱንም ሆነ ፍላጎቱ ያላቸውን ሀገር ወዳድ ዜጎች ለማሰልጠን ዝግጁ የሆነ አካዳሚ ገንብቶ መጨረሱን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ሠልጣኞችን ወደ አካዳሚው ለማስገባት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተመዘገቡ አባላት በመመልመል ላይ ይገኛል። ከአካዳሚው ዘላቂ የአቅም ግንባታ ሥራ ጎን ለጎን ከዚህ ቀደም ሲያደርገው ከነበረው የፖለቲካ ውይይቶች በተለየ ትኩረት ለአመራርነት እና ለጠራ ግንዛቤ አስተዋጽኦ ባላቸው የተመረጡ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ የውይይት መድረኮች በተለያዩ አማራጮች እንዲካሄድ ወስኗል።   

2)    ሀገራዊ ጉዳዮች

2.1) ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ፡ በውይይቱ በልዩ ትኩረት ከታዩት አጀንዳዎች መካከል ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አንዱ ሲሆን ውስጣዊ የጸጥታ ችግሮች፣ የኑሮ ውድነት እና ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮችን በየፈርጁ ተመልክቶ አሁናዊ ሀገራዊ ፖለቲካችን ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ሁኔታ እየተለወጠ መምጣቱን ፓርቲው ተገንዝቧል። ከ2010 ዓ.ም. ለውጥ በኋላም ቢሆን በዘውግ ማንነት ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሂደት የሀገራችንን  እድገት እና ዴሞክራሲ ወደኋላ በማስቀረት ዛሬም እልባት ስላላገኘ ለዜጎቻችን መፈናቀል፣ ሞት እና ሰላም ማጣት መንስኤ መሆኑን ቀጥሏል፡፡ በእንደዚህ አይነት ሃገራዊ ሁኔታና በሚለዋወጡ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ምክንያት ሀገር ወዴት እየሄደች ነው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ባለመቻሉ ህዝባችን በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ መሆኑን እና ማህበረሰባችንን ከዚህ ግራ መጋባት በማውጣት ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚኖርባትን ሀገር ለመፍጠር የሚያስችል የፖለቲካ ስርዓት ለመዘርጋት ይቻል ዘንድ ፓርቲያችን ይህን ተለዋዋጭ የሆነ የፖለቲካ ሥርዓት በተረዳ መልኩ ለህዝቡ ጠንካራ የፖለቲካ አማራጭ ሆኖ ሊሰራ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ወቅቱን የሚመጥን የፖለቲካ አስተሳሰብ እና አሠራር ማስፈን ይረዳ ዘንድ የአጭር እና የረዥም ጊዜ ተግባራት የለየ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ በቅርቡ የተብራራ ሰነድ ይፋ እንደሚያደረግ ያሳውቃል።

ፓርቲያችን ኢዜማ ከድርጅታዊ መርኆዎቹ ቀዳሚው የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ሁሌም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። የፖለቲካ ፓርቲ (የቡድኖች) ጥቅም ከሀገር በታች የሆነ ፍላጎት መሆኑን በመገንዘብ የሀገርን ጥቅም ጉዳይ በምንም መልኩ በሁለተኛ ደረጃ የሚያየው እንዳልሆነ ዛሬም በድጋሚ ለማረጋገጥ ይፈልጋል። ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በተለይ በዘውግ ማንነት ላይ የተንጠለጠለው የፖለቲካ አስተሳሰብ እና መዋቅር እስካሁን ሀገራዊ አንድነታችን በማላላትም ሆነ ለዘላቂ ሀገራዊ ጥቅማችን ስጋት የሆኑ አያሌ ችግሮችን ያጋለጠን መሆኑ ሳያንስ በዚህ ስሁት አስተሳሰብ የተለከፉ ኃይሎች ከባእዳን ጋር ሳይቀር በመሰለፍ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ እንቅስቃሴዎቻቸውን በጥንቃቄ እየተከታተላቸው ይገኛል። በኢትዮጵያ ወስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ኃይሎች ምንም እንኳን የተለያየ አመለካከት እና ፍላጎቶች እንዳሉን ብናምንም የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚፈታተኑ እና የሕዝብን ሰላም የሚነሱ ጉዳዮች ሲከሰቱ ግን ከሁሉም ሀገር ወዳድ  ኃይሎች ጋር በጋራ የምንቆም መሆኑን በድጋሚ ለማረጋገጥ ይወዳል።

2.2) ሀገር አቀፍ ምርጫ፡ ኢትዮጵያውያን ምንም እንኳን በበርካታ ውስጣዊ እና ውጪያዊ ችግሮች የተከበብን ቢሆንም የፖለቲካ ሥልጣን ማግኛው ብቸኛ መንገድ በሃሳብ ፉክክር ላይ የተመሠረተ ነጻ እና ገለልተኛ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ብቻ መሆኑ ላይ አቋማችን የማይናወጽ ነው።  በሀገራችን ወደ ሥልጣን መውጫ መንገድ ምርጫና ምርጫ ብቻ እንዲሆንም አብክሮ ይሰራል፡፡በዚህም መሠረት አሁናዊ ሀገራዊ ፖለቲካ ላይ ፓርቲው እንደ አንድ ዋነኛ ባለድርሻ የሚጠበቅበትን ገንቢ ሚና ለመጫወት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊደረጉ ከሚገባቸው ፖለቲካዊ ተሳትፎዎች መካከል በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ መቅረብ አንዱ ነው። ይህንንም ማሳካት እንዲያስችለው በቅርቡ በፓርቲው መሪ የሚመራ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰይሞ ወደ ሥራ የሚገባ መሆኑን ያሣውቃል።

2.3) ሀገራዊ ምክክር፡ ሀገራችን ውስጥ ለዘመናት የዘለቀው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ኋላቀርነት ምክንያቶች አንዱ እስካሁንም ያልተጠናቀቀው የዘመናዊ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የፈጠራቸው ውስብስብ ችግሮች መሆናቸውን ግልፅ ነው። ከእነዚህ ችግሮች ጋር የተያያዙ የተለያዩ የታሪክ ዕይታዎችና ቁርሾዎች የሀገራችንን የፖለቲካ ሁኔታ ከድጡ ወደማጡ እንዲዘፈቅ በማድረግ ፍትሕ፣ ነጻነት እና እኩልነት የሰፈነባትን የተረጋጋች ኢትዮጵያን በጋራ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል። ከዚህ ችግር በዘላቂነት ለመላቀቅ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነትን ለድርድር ሳያቀርብ ቢያንስ መሠረታዊ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ የተለያየ እምነት እና ፍላጎት አለን የሚሉ ኃይሎችን ወደ ጋራ ሥምምነት የሚያደርስ ሀገራዊ ምክክር ማድረግ እንደሚያስፈልግ ፓርቲያችን ቀደም ሲል ባጸደቃቸው ድርጅታዊ ሰነዶቹም ሆነ የአቋም መግለጫዎቹ ሲያስገነዝብ ቆይቷል፡፡

ሀገራችንም ለዚህ ጥሩ መደላድል የመፍጠር እድል ያለው የሀገራዊ ምክክር ከሦስት ዓመታት በፊት መጀመሯ ይታወሳል። ሀገራዊ ምክክሩ የሚመራበትን ሕግ በመደንገግም ሆነ ኮሚሽነሮቹን በመሰየሙ ሂደት በርካታ እክሎች የነበሩበት ቢሆንም እንኳን ጉድለቶቹ እንዲስተካከሉ ግፊት እያደረጉ በምክክሩ ሂደት መሳተፍ የተሻለው አማራጭ መሆኑን በማመን ኢዜማ ለሀገር አንድነት፣ ለሕዝብ ሰላም እና እድገት ይበጃል የሚላቸውን ምክረ ሃሳቦች የያዘ ሰነድ አዘጋጅቶ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በሙሉ ልብ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ገዢው ፓርቲ በአንድ አንድ አካባቢዎች እንደተስተዋለው የተለያዩ ጣልቃ ገብነቶችን በመፈጸም አመኔታውን ከመሸርሸር እንዲቆጠብ ለማሳሰብ እንወዳለን። ከዚህ ባለፈ ከፍተኛ ሀገራዊ ሀብት ፈስሶበት የሚደረግ እና በስንት  አንድ ጊዜ የሚገኝን ሀገራዊ ምክክርን የመሰለ  እድል ከውስጥም ሆነ ከውጪ የሚመጡ ጣልቃ ገብነቶችን በጋራ መከላከል እንደሚገባም እናሳስባለን።

ሀገራዊ ምክክሩ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን በተለያዩ አከባቢዎች ነፍጥ አንስተው የሚፋለሙ ኃይሎች ተሳታፊ መሆን እጅጉን አስፈላጊ በመሆኑ መንግሥት ከመገናኛ ብዙኃን ጥሪ ባለፈ የሚያደርጋቸውን ሙከራዎች ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በድርድር፣ በሽምግልና ብሎም በሌሎች ሰላም ማምጣት በሚችሉ ማናቸውም አማራጭ መንገዶችን ተጠቅሞ ግጭቶቹ የሚቆሙበት ሁኔታን እንዲያመቻች እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን። የፖለቲካ ፍላጎቶቻቸውን ለማሳካት በምንም ምክንያት ይሁን ነፍጥ አንስተው ጫካ የገቡ ኃይሎች ሊያስታውሱት የሚገባው ዋና ቁምነገር ያለፉትን ሁለት ትውልዶች የአመጽ መንገድ ልብ ካልን ከብዙ ሕይወት እና ንብረት ውድመት በኋላ ምናልባት የመንግሥት ለውጥ ማምጣት ይቻል እንደሆነ እንጂ የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓትም ሆነ የተሻለ ማኅበረሰብ የሚፈጥር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማስፈን እንደማይቻል መገንዘብ ያሻል። በመሆኑም በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ ነፍጥ ያነሳችሁ ኃይሎች እንታገልለታለን ለምትሉት ማኅበረሰብም ሆነ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ጦርነት ጥፋት እንጂ አንዳች እርባና እንደማያመጣ በመገንዘብ ለሰላም ድርድር በራችሁን ክፍት እንድታደርጉ እና በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በድጋሚ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለሀገራዊ የጋራ ጥቅሞቻችን በጋራ እንድንቆም በውስጣዊ ችግሮቻችን ሳቢያ በምንም ሁኔታ ቢሆን ለውጭ ኃይሎች በር እንዳንከፍት ሀገራዊ ጥሪ ማስተላለፍ እንፈልጋለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
የካቲት 25/2017 ዓ.ም.

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የአዲስ አበባ መጅሊስ – ከዚህ በኋላ በመስጂዶች ጉዳይ አይታገስም
በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 2026
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 2026
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2