በኢትዮጵያ የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንደሚጠየቅ ተገለጸ። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መጠየቁ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ ፓስፖርት ለሚወስዱ እንቅፋት እንደሆነ ተመልክቷል።
ከሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ሰነዶች መካከል ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አንዱ እንደሚሆን ነው ተቋሙ ይፋ ያደረገው። በሂደት ላይ ያሉም ወይም ፓስፖርት ለመውሰድ በቀጠሮ ላይ የሚገኙ ዜጎችም ለመረከብ ሲመጡ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መያዝ እንዳለባቸው ተመልክቷል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ሰነዶች ውስጥ በማካተት አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እና የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት በትብብር ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል።
ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌላቸው በርካታ ሰዎች በማጭበርበር ፓስፖርት መውሰዳቸው ይታውቃል። በገንዘብና ሰነድ በማደለዝ፣ እንዲሁም እንደ አዲስ ቅጽ በመሙላት የቀበሌ አማራሮች በገንዘብ ሰነድ እንደሚያዘጋጁ፣ ይህም በትሥሥር ይሰራ እንደነበር በተደጋጋሚ ሲገለጽ መሰንበቱ ይታወሳል። አገልግሎቱ በሌብነት የተተበተበ በመሆኑ ይህ አሰራር ቁትጥሩን ለማጥበቅ አመቺ እንደሚሆንም ስለ አሰራሩ የሚያውቁ አስቀድመው ሲገልጹ ነበር።
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter

