Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  FEATURED  የ “ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ፋይዳ ያልገባቸው … “ፋይዳ መታወቂያ ምን ያደርግልኛል?” አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን ለማወቅ ቆርጣለች!
FEATURED

የ “ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ፋይዳ ያልገባቸው … “ፋይዳ መታወቂያ ምን ያደርግልኛል?” አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን ለማወቅ ቆርጣለች!

Ethioreview newsEthioreview news—April 7, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የፋይዳ ዲጂታል ብሄራዊ መታወቂያ ጥቅም ገና ያልተገለጸላቸው ብዙ ናቸው፤ ቢገባቸውን ፍላጎት የማያሳዩም በርካቶች ናቸው፤ ይህን ዓለም ድሮ የጨረሰውን አሰራር “ስለላ ነው” በሚል የሚቃወሙ ተቃዋሚዎችም አሉ፤ አውሮፓና አሜሪካ በተመሳሳይ መታወቂያ ወደውና ፈቅደው የሚኖሩ አይናቸውን አጥበው ሲተቹ ይሰማል።

” ከዚህ ቀደም አንድ ሰው አንድ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ባለመቻላችን በሁለት በሦስት ማንነት መታወቂያ ማውጣት፤ የታክስ ማጭበርበር እንዲሁም በተጭበረበረ ማንነት የንብረት ቅሚያ ይከናወን ነበር ” ይላሉ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ለአገልግሎቶች ግንዛቤ ማስጨበጫ በተዘጋጀ መድረክ ላይ፡፡

ዋና ስራ አስኪያጁ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ስም መታወቂያ ያወጣ ሰው ዳግም በዛ ስም መታወቂያ የማያወጣበትን ሥርዓት መፈጠሩን አስታውቀው በሲቪል ምዝገባ ረገድ እየተሰራ ያለውን ስራ ጠቀሜታ አስመልክቶ ስለላው ግንዛቤ ያወሳሉ።

አብዛኛው ሰው የፋይዳ መታወቂያ የሚመዘገበው በአስገዳጅ መልኩ መሆኑን ሲገልጹ ኢንጂነር ወንድሙ ይህ መሆን ያልነበርበት እንደሆነ በማመላከት ነው፤ ” ለምንድነው ፋይዳ የማትመዘገበው ?” ሲባል “ምን ያደርግልኛል” የሚል ሰው በጣም ብዙ መሆኑን ያመለከቱት ባለስልጣኑ፣ ከፋይናንስ፣ ከታክስ፣ ከቤት ኪራይ፣ ከመንጃ ፈቃድ፣ ከንብረት ባለይዞታነት አገልግሎት ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ጠቁመዋል።

More stories

“የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማየት ሁላችንንም ያብቃን፤ እኔ እንደማይ አምናለሁ፤ ያመነ ከእኔ ጋር ይጓዝ” አብይ

October 8, 2025

ያልተነቀለው ሰንኮፍ – ዩሪ ቢስሜኖቭ እንዳለው፣ እኛም እንዳየነው…

February 11, 2025

ሻዕቢያ በአቅም ችግርና በዕቅድ መዛባት የውጊያ ዕቅዱን ቀየረ፤ ድርድር ከጅሏል፤ ትህነግ እያፈገፈገ ነው

April 14, 2025

አዲሱ ሚኒስትር “የሰላም እጦት”

February 23, 2024

ከዚሁ ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ የስበት ማዕከል መሆኗን በመጥቀስ ህጋዊ ያልሆኑ ፍልሰቶች መኖራቸው በከተማው መሰረተ ልማት ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አንስተዋል።

” አዲስ አበባ ውስጥ ያለውን ሰው ማወቅ አለብን ፤ በአግባቡ የተመዘገበ መሆን አለበት። የአዲስ አበባ አስተዳደር አገልግሎት የሚያቀርበው ለምን ያህል ሚሊዮን ነዋሪ እንደሆነ መታወቅ አለበት” ብለዋል።

ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ሰዎች የተመዘገቡ መሆን እንድለባቸው ሲያወሱ፣ ” በአንድ ቦታ ወንጀል ሰርቶ  የመጣ ሰው አዲስ አበባን መደበቂያ ማድረግ የለበትም፤ ከተማ አስተዳደሩ ያወቀው ነዋሪ መሆን አለበት። ያንን ማድረግ የሚያስችል ሥራ እየሰራን ነው ያለነው ” ሲሉ የፋይዳ መታውቂያን ጠቀሜታ ከአገልግሎት በዘለለም ገልጸዋል።

አስገራሚ ጉዳይ የተባለውና እሳቸውም በግልጽ ያነሱት በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ ያለው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጉዳይ ነው። ለሚቀጥለው ዓመት የትምህርት ዘመን ምዝገባ የፋይዳ መታወቂያ በመስፈርትነት በማስቀመጥ ለዚህም በአንድ ወር ውስጥ 450 ሺ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ ስራ ቢጀመርም መመዝገብ የተቻለው 130 ሺ የሚሆኑትን መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

” ወላጆች የተሟላ መረጃ አይልኩልንም ” ያሉት ኢንጂነር ወንድሙ አንዳንዶቹ ለራሳቸውም የፋይዳ መታወቂያ የሌላቸው መሆኑን በመጥቀስ የግንዛቤ እጥረት ለሥራው ፈተና መሆኑን አንስተዋል። ይህን መግለጫቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ አድራሻ የሌላቸውና መታወቂያ እንዲያወጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ ያልሰጡ በመጪው ዓመት ምዘግባ ምን ምላሽ ሊሰጡ ነው?

በተመሳሳይ ከሞት እና ጋብቻ ሰርተፊኬት ጋር ተያይዞ የማስመዝገብ ባህሉ ደካማ መሆኑን በማንሳት በተለይ ከሞት ምዝገባ ጋር ተያይዞ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት እዛው ሰርተፊኬት የሚያገኙበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው ብለዋል።

የጀርመን ድምጽና ቲክቫህ ከዘገቡት ተዋህዶ በተጠናከረው ዘገባ ለማሳየት የተሞከረው የፋይዳ መታወቂያ አስመልክቶ ያለውን መንሸዋረር ነው፤ ፋይዳ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ዲጅታል መታወቂያ በተለመደው መንገድ በካርድ መልክ የሚቀርብ ሳይሆን ዲጅታል በሆነ የመለያ ቁጥር ማንነትን ለመለየት የሚያስችል ነው። ይህ ፋይዳ ቁጥር ቴክኖሎጂን በመጠቀም የግል መረጃዎችን አንድ ላይ የያዘ እና እያንዳንዱን ግለሰብ ማንነት የሚለይ ነው።

ፋይዳ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ

በነጮቹ አቆጣጠር 1983 ዓ/ም በዓለማችን የበይነመረብ መምጣትን ተከትሎ በርካታ አገልግሎቶች ከነባሩ የወረቀት አሰራር ወደ ዲጅታል ተለውጠዋል።ከነዚህም መካከል ዲጅታል የሆነ የማንነት መለያ አንዱ ነው። የዲጅታል  የማንነት መለያ ከ1980ዎቹ ጀምሮ በተለያዩ ሀገራት ስራ ላይ የዋለ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ  ይህ ዲጅታል መታወቂያ በሙከራ ላይ ነበር። 
በመጋቢት 2015 ዓ/ም ግን በአዋጅ ደረጃ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል። ፋይዳ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ዲጅታል መታወቂያ የአዋጁን መፅደቅ ተከትሎ  ከሙከራ ወደ ትግበራ ተሸጋግሯል።በቅርቡ ደግሞ ይህን ዲጅታል መታወቂያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ዋና አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ገልፀዋል።
ወደዚህ  ዲጅታል  ስርዓት  ስንገባ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰርተናል የሚሉት ሀላፊው፤ ኢትዮጵያ ይህንን መታወቂያ አገልግሎት ላይ በማዋል የመጨረሻ ሀገር መሆኗን ገልፀዋል።

ምንም እንኳ ይህንን መታወቂያ ወደ አገልግሎት ለማምጣት ኢትዮጵያ የዘገየች ቢሆንም እንደ አቶ ዮዳሄ ገለፃ መታወቂያውን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ለማስተሳሰር ጥሩ እድል ፈጥሯል።


ግንዛቤ ከማስጨጥ በተጨማሪ አዋጁም ቢሆን ዲጅታል አገልግሎቶችን ከዚህ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰርን እንደሚፈቅድ ሃላፊው ጠቅሰዋል።ከተወሰነ ወራት በኋላ ብሄራዊ ባንክ ከነባር እና ከአዲስ ደንበኞቹ የባንክ አካውንት ጋር ለማስተሳሰር በአራት የተከፈለ የአተገባበር መርሃ ግብር ማውጣቱን ገልፀዋል።

አዲስ አበባ ከተማ አዲስ ለሚከፍቱ የባንክ ደንበኞች  ዲጅታል መታወቂያ የግድ ሲሆን፤ከሶስት ወር በኋላም ክልሎች ይሄው ግዴታ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል።በአጠቃላይ ከአንድ አመት በኋላ ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የባንክ አካውንት ማውጣት እና አገልግሎት ማግኘት ያለዚህ መታወቂያ ቁጥር  የማይቻል ይሆናል።ይህም እንደ አቶ ዮዳሄ ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖር  ጠቃሚ ነው ።

የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ በተለመደው መንገድ በካርድ መልክ የሚቀርብ ሳይሆን ዲጅታል በሆነ የመለያ ቁጥር ማንነትን መለየት የሚያስችል  ነው። ይህ ፋይዳ ቁጥር ቴክኖሎጂን በመጠቀም የግል መረጃዎችን  አንድ ላይ የያዘ  እና እያንዳንዱን ግለሰብ ማንነት የሚለይ ነው።ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት ያለው ነው። ፋይዳ መታወቂያ በአዋጁ መሰረት የአንድን ሰው ማንነት ለማረጋገጥ እንደ ሕጋዊ እና በቂ ማስረጃ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ያም ሆኖ በየአካባቢው ከሚሰጡ የቀበሌ መታወቂያዎች በአገልግሎቱ የተለዬ መሆኑን አስረድተዋል።ነገር ግን ሁለቱን ማስተሳሰር እንደሚቻል ገልፀዋል።

አቶ ዮዳሄ እንደሚሉት ፋይዳ በዕድሜም ሆነ በዜግነት ገደብ ያልተደረገበት ዲጅታል መታወቂያ ነው።በመሆኑም ይህንን ዲጅታል መታወቂያ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ልጆች  እንኳ ወላጆቻቸው ሊያወጣላቸው ይችላል።ከአምስት ዓመት በላይ ለሆኑት ግን አሻራቸውን ሰጥቶ የፋይዳ ቁጥር ማግኘት ይቻላል። ከ18 ዓመት በላይ ሲሆኑ ደግሞ ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል።ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ መሠረታዊ የግል መረጃን በመስጠት ማንኛውም ሰው ይህንን ዲጂታል መታወቂያ የማግኘት መብት ያለው ቢሆንም፤ ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ሰዎች ግን መውሰድ አይችሉም።

በሌላ በኩል ይህ መታወቂያ የአንድን ሰው ስም እና የመኖሪያ አድራሻን ጨምሮ በርካታ የግል መረጃዎችን የያዘ በመሆኑ ለመረጃ ምንተፋ እና ባልተገባ ሁኔታ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ ሊሰጥ  ይችላል የሚል የመረጃ ደህንነት ስጋት ይነሳል።አቶ ዮዳሄ ግን በህግም በቴክኖሎጅም በሁለት መንገድ የመረጃ ጥበቃ እንደሚደረግ አብራርተዋል።
ዲጅታል አገልግሎት ሲነሳ የበይነመረብ እና የዲጅታል መሰረተ ልማት እጥረት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳጊ ሀገራት የሚነሳ ችግር ነው።አቶ ዬዳሄ እንደሚሉት ግን ያለበይነመረብ  መስራት የሚያስችል  በመሆኑ  በዚህ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባና አገልግሎት ላይ እንቅፋት የለም።

በኢትዮጵያ አሁኑ ወቅት 13 .5 ሚሊዮን ሰዎች የመታወቂያው ተጠቃሚ ናቸው። ከተለያዩ አጋሮች ጋር የምዝገባ ስራው በተለያዩ አካባቢዎች የእየተካሄደ መሆኑን የሚገልፁት ሀላፊው፤ እስከ 2018 ዓ/ም መጨረሻ የተጠቃሚውን ቁጥር ቢያንስ 70 ሚሊዮን ለማድረስ እቅድ ተይዟል።
ፋይዳን ፤መውሰድ በአዋጁ መሰረት አስገዳጅ ባይሆንም በርካታ ተቋማት አገልግሎታቸውን ከፋይዳ ጋር መታወቂያ ጋር የሚያስተሳስሩ ተቋማት እየጨመሩ በመጡ ቁጥር ግን ያለዚህ ዲጅታል መታወቂያ አገልግሎት ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ ይመጣል። በአሁኑ ወቅትም በርካታ ተቋማት አገልግሎታቸውን በማስተሳሰር  አገልግሎት ለመስጠት ፋይዳ መታወቂያን አስገዳጅ ማድረግ ጀምረተዋል።በመሆኑም ተጠቃሚዎች መታወቂያውን ከወዲሁ እንዲያወጡ አቶ ዬዳሄ አሳስበዋል።

featured
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የትህነግ – “ከሻዕቢያ፣ፋኖ እና ሸኔ ጋር በጣምራ ጦርነት እንጀምር ዕቅድ አላስማማም፤”ፋኖ ወልቃይት እየገባ ነው እንጠቀምበት”
አብን ዶ/ር በለጠ ሞላን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ ሰየመ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
FEATURED

የጸረ – ቤተሰቡ የአንዳርጋቸው ጽጌ የፖለቲካ ውርዴ ውርስ፣ ባንዳነትና ክህደት

November 7, 2025
FEATURED

የአስገድዶ መድፈርና የግፍ ወንጀል – ከትግራይ የወጣው አዲስ ሪፖርት ገለልተኛነት?

October 23, 2025
ECONOMY

“የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማየት ሁላችንንም ያብቃን፤ እኔ እንደማይ አምናለሁ፤ ያመነ ከእኔ ጋር ይጓዝ” አብይ

October 8, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2