Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ሶስት ኃይሎች ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳያመሩ ስጋት የገባቸው ጥሪ አቀረቡ፤ የታደሰ ወረዳ መፎረሽ ስጋቱን አብሶታል
News

ሶስት ኃይሎች ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳያመሩ ስጋት የገባቸው ጥሪ አቀረቡ፤ የታደሰ ወረዳ መፎረሽ ስጋቱን አብሶታል

Ethioreview newsEthioreview news—April 24, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በትግራይ እየታየ ያለው የፖለቲካ ቀውስ ከቀን ወደቀን አዳዲስ ችግሮች እየተደረቡበት ሕዝብ ስጋት ላይ ወድቋል። ስጋት ናቸው የተባሉት ሶስት ክፍሎች በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ላይ የተካሄደውን ኩዴታ በመቃወም ቲዲኤፍን ጥለው በመውጣት ነጻ መሬት በመያዝ ትግል ለመጀመር የተዘጋጁ፣ የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ትህነግ ደጋፊ ሆነው በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደሩን ገልብጠው ስልጣን በያዙት የሚመሩትና ራሱን “የተከዜ ዘብ” በሚል አደራጅቶ ወልቃይትን ሃያ አራት ሰዓት እንደሚጠብቅ ይፋ ያደረገው ናቸው። በዚህ ሁሉ ችግር ላይ አዲስ የተሾሙት የክልሉ መሪ መፎረሻቸው ችግሩን እንዳባባሰው ተጠቁሟል።

“በሶስት የተከፈለው የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ ትግራይን ክፉኛ የሚጎዳ ነው” ያሉት የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር፤ “የታጠቁ ኃይሎች በዚህ እና በዚያ ስላሉ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊያጋጥም ይችላል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ “አደገኛ አካሄድ” ሲሉ የጠሩት አቶ ዓምዶም፤ የትግራይ ህዝብ እና የዓለም ማህበረሰብ ተጽዕኖ በመፍጠር የጦርነቱ ስጋት እንዲወገድ ጥሪ ፣አቅረባቸውን ኢትዮ ኢንሳይደር መገለጫውን ጠቅሶ ዘግቧል።

አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በቅርቡ ያቋቋመው ካቢኔ “ለአንድ ቡድን ያደላ ነው” በማለት እንደማይቀበሉት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሶስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታወቁ። በትግራይ ክልል በሶስት የተከፈሉ የታጠቁ ኃይሎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሳቢያ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊነሳ የሚችልበት እድል እንዳለም ፓርቲዎቹ ስጋታቸውን ገልጸዋል። 

ይህን አቋማቸውን እና ስጋታቸውን ረቡዕ ሚያዝያ 15፤ 2017 በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የገለጹት፤ ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት (ዓረና)፣  ወድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት) እና የብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ (ባይቶና) የተባሉት ፓርቲዎች ናቸው። ሶስቱ ፓርቲዎች “የተጋሩ ብሔራዊ ደህንነት ቃልኪዳን” የተሰኘ ጥምረት አቋቋመው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ናቸው። 

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

የፓርቲዎቹ የዛሬ መግለጫ በዋናነት ያተኮረው፤ በሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የሚመራው አዲሱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባዋቀረው ካቢኔ ላይ ነው። ሌተናል ጄነራል ታደሰ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የመምራት ስልጣን ከአቶ ጌታቸው ረዳ የተረከቡት፤ ከሁለት ሳምንት በፊት መጋቢት 30 በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደ ስነ ስርዓት ነበር።

ዓረና፣ ውናት እና ባይቶና በዛሬው መግለጫቸው፤ ሌተናል ጄነራል ታደሰን ጨምሮ በክልሉ የነበረውን ጊዜያዊ አስተዳደር “በኃይል እንዲገለል ላደረጉ አካላት” ሹመት መሰጠቱ “ተቀባይነት የለውም” ብለዋል። በስልጣን ርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር “አቃፊ እና አሳታፊ ይሆናል” ቢባልም፤ አዲሱ ካቢኔ ሲዋቀር ግን ቃል ከተገባው የታቃረነ እንደሆነ ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።     

የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ “ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወደዚህ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከህወሓት ጽህፈት ቤት አንጃ ጋር በመመካከር፣ ካቢኔው ከህወሓት እና የህወሓት ደጋፊ ከሚባሉ ብቻ በማወቀር፣ ‘አቃፊ እና አሳታፊ ይሆናል’ የተባለው ጊዜያዊ አስተዳደር የአንድ ቡድን ብቻ እንዲሆን አድርገዋል” ሲሉ ተችተዋል። አዲሱ ፕሬዝዳንት የሰጧቸውን የካቢኔ አባልነት ሹመቶች፤ የተለያዩ ፓርቲዎች ተወክለውበት ለተመሰረተው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክር ቤት በተቋቋመበት ደንብ መሰረት አቅርበው አለማጸደቃቸውንም ነቅፈዋል። 

ይህ አካሄድ የትግራይን ችግር ከመፍታት ይልቅ፤ ክልሉን ወደ በለጠ ችግር የሚወስድ አደገኛ አካሄድ እንደሆነ አቶ ዓምዶም አጽንኦት ሰጥተዋል። ሶስቱ ፓርቲዎች በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸው፤ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ውስጥ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት የትግራይ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታደለ መንግስቱ መታሰራቸውን በመግለጽም እርምጃውን ኮንነዋል። 

አቶ ታደለ የባይቶና ፓርቲን በመወከል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ካቢኔ የተቀላቀሉት በአቶ ጌታቸው ረዳ የስልጣን ዘመን ነበር። ሌተናል ጄነራል ታደሰ ካቤኒያቸውን ሲያወቅሩ እንደ እርሳቸው ሁሉ ባይቶናን በመወከል የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮን ሲመሩ የቆዩትን አቶ ሞገስ ገብረእግዚያብሔርን ከኃላፊነት አንስተዋል። 

የዛሬውን ጋዜጣዊ መግለጫ ከሰጡት የፓርቲ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት የባይቶና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ በርሀ “አቶ ታደለን ማሰር በካቢኔው የቀረን ብቸኛ የተለየ ድምጽ የሚያሰማ አካል ማፈን ነው” ሲሉ ድርጊቱን አውግዘዋል። አቶ ታደለ የታሰሩት በመቐለ ከተማ በሚገኘው ሃውልቲ ክፍለ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደሆነም ገልጸዋል። 

የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው የታሰሩት፤ የህወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) “በጦርነቱ ጊዜ የወሰዱትን የመንግስት መኪና ማስመለስ አልቻሉም” በሚል ምክንያት እንደሆነ የባይቶና ምክትል ሊቀመንበር ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከተወሰደ በኋላ በዛሬው ዕለት በነበረ የችሎት ውሎ፤ አቶ ታደለ ላይ የስድስት ወራት እስራት እንደተፈረደባቸው መረዳቱን ባይቶና ፓርቲ ከጋዜጣዊ መግለጫው መጠናቀቅ በኋላ አስታውቋል። 

ለአቶ ታደለ እስር ምክንያት የሆነው በወ/ሮ ፈትለወርቅ እጅ ይገኛል የተባለው ተሽከርካሪ ዛሬ ማምሻውን በመመለሱ፤ የቢሮ ኃላፊው ከእስር መለቀቃቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከሰዓት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአቶ ታደለ እስር ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ እንዲፈቱ ጠይቀው ነበር። 

በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ በትግራይ ክልል በተለያዩ ጎራ ሆነው እየተንቀሳቀሱ ስላሉ ታጣቂ ኃይሎች ጉዳይም ተነስቷል። በትግራይ ክልል ሶስት የተለያዩ የታጠቁ ኃይሎች እንዳሉ የገለጹት የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም፤ የመጀመሪያዎቹ ራሳቸውን “ከኮር በላይ” ብለው የሚጠሩ እና አንዱን የህወሓት ጎራ የሚደግፉ የጦር አዛዦች እንደሆነ አስረድተዋል።  

ሁለተኛዎቹ የታጠቁ ኃይሎች በምዕራብ ትግራይ የሚገኙ እና “የተከዜ ዘብ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው እንደሆነ አቶ ዓምዶም ገልጸዋል። ሶስተኞቹ የታጠቁ ኃይሎች፤ የክልሉ ወታደራዊ አመራሮች አንዱን የህወሓት ጎራ መወገናቸውን በመቃወም “ነጻ መሬት” ባሉት ስፍራ የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን አክለዋል።

በሶስት የተከፈለው የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ “ትግራይን ክፉኛ የሚጎዳ ነው” ያሉት የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር፤ “የታጠቁ ኃይሎች በዚህ እና በዚያ ስላሉ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊያጋጥም ይችላል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ “አደገኛ አካሄድ” ሲሉ የጠሩት አቶ ዓምዶም፤ የትግራይ ህዝብ እና የዓለም ማህበረሰብ ተጽዕኖ በመፍጠር እንዲቆም እንዲያደርግ አሳስበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡  @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው
“የጃልመሮ ሃይሎች በበቀለ ሕዝብ እየጨረሱ ነው፤ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች፣አክቲቪስቶች፣ የመብት ተቆርቋሪዎች የት ናቹህ”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2