Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News2  ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው
News2OPINION

ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው

Ethioreview newsEthioreview news—April 24, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ”የሰባ ገብዣ” በሚል ርዕስ ስቅለት ዕለት ያቀረቡትን መልዕክት በተመለከተ እጅግ በርካታ ውግዘትና ፍረጃ ሲሰጥ እየተሰማ ነው። የሊቀ ጳጳሱን ስብዕና እና ማንነት ከማዋረድ ጀምሮ የሚሰጡት ስድብ አዘል “አስተያየቶች” ኢ-መንፈሳዊ፣ ጽንፈኛና አምባገነናዊ ናቸው።   

ገና ከጅምሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪና ብዙ ተከታይ አለን የሚሉ በሚሰጡ አስተያየት ሊቀ ጳጳሱን ከመዝለፍና ከማዋረድ አልፈው ግለሰባዊ ማንነታቸውን በማጉላት ሲሳደቡ ተሰምተዋል። እነዚህ “መምህራን” ብለው ራሳቸውን የሰየሙ ወይም ጥቂት ጊዜያት በቤተ ክርስቲያኗ የትምህርት ደጃፍ በማለፋቸው ብቻ “መምህር” ተብለው የሚጠሩ፤ በአቡኑ ላይ ለርካሽ የፖለቲካ መጠቀሚያ የሚውልና ከወንጌል አስተምህሮ የለቀቀ እጅግ ጸያፍ ንግግሮች በማሰማት ከሊቃውንቱ ጉባዔና ሲኖዶሱ ውሳኔ በፊት የአደባባይ ፍረጃ እየበየኑባቸው ነው፤ የሲኖዶሱን እጅ እየጠመዘዙም ነው።

ድርጊቱ በዕቅድና በዘመቻ መልክ የሚካሄድ እንደሆነ አንዱ ማሳያ፤ ቪዲዮውን ያወጣው ፍኖተ ጽድቅ የተባለው ሚዲያ በዩትዩብ ቻናሉ ሲሆን ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ቀን ድረስ ቪዲዮው ከወጣ አራት ቀናት አልፈዋል። በእነዚህ አራት ቀናት ቪዲዮውን የተመለከተው ሰው ቁጥር 22ሺህ ብቻ ሲሆን አስተያየት ሰጪውና ነቃፊው ግን “22 ሚሊዮን” መድረሱ ዘመቻው ከዕውቀት የጸዳና ሌላ ስሁት ዓላማ ያለው መሆኑ አመላካች ነው።

አቡነ ገብርኤል ያደረጉት ፖለቲካዊ ወይም ተራ ንግግር ሳይሆን ሃይማኖታዊ መልዕክት ያለው ነው፤ የመልዕክታቸው ይዘት ደግሞ ነገረ መለኮታዊ ወይም ቲዎሎጂካል ነው። እርሳቸው የተናገሩትን ከቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ አንጻር ስህተት ነው ወይም አይደለም የማለት ሥልጣን ያለው ቤተ ክርስቲያኗ ሥርዓቱን ጠብቃ ያዋቀረችው የሊቃውንት ጉባዔ ነው እንጂ የቲክቶክ ነጋድራሶች፣ የቴሌግራም ፊት አውራሪዎችና የዩትዩብ ተጧሪዎች መሆን የለባቸውም።

More stories

“ሩስያ ከዩክሬን ጋር ሰላም ካልፈጠረች ከባድ ቅጣት ይጠብቃታል” ዶናልድ ትራምፕ ሩስያን አስጠነቀቁ

January 23, 2025

ጦርነት ምን እንደሚያስከፍል አይተነዋል ፣ የሰላምን ዋጋ ግን አልተገነዘብንም!

October 9, 2022

“የመርዓዊ ሕዝብ ወደ ጫካ እየገባ ነው”ባልደራስ፤ “ከተማችን የተለመደ እንቅስቃሴ ላይ ናት” አስተዳደሩ

May 22, 2022

የፋኖ ሚና እና የወደፊት እጣ ፈንታ…(ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ)

January 30, 2022

የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት በዚህ ዓመት የካቲት ወር ባወጣው መረጃ ይህንን ብሎ ነበር፤ “የሊቃውንት ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ኀላፊነት መሠረት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮ፣ ታሪክና ትውፊት፣ ልሳነ መጻሕፍትና የዕውቀት ሀብታት፣ ጥበባተ አበውና ባህለ ሃይማኖትን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ ማስፋፋትና በአግባቡ እንዲተረጐሙ ማድረግ፣ ዐቂበ እምነትን ማጠናከር፣ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ልዕልና፣ ህልውና፣ የትምህርቷን ጥራትና ርትዐት መጠበቅ ዋንኛ የሥራ ድርሻው ነው።

“በቀድሞ ዘመን መናፍቅና ከሓዲ ሲነሣ፣ ሃይማኖትና ሥርዐት ሲጣስ፣ ዐላውያን የሐሰት ትምህርትን በዐውደ ጉባኤ ሲያሠራጩ፡ ሊቃውንት ከየአሉበት ተሰብስበው ዘርዐ ኑፋቄን አርመው፣ ኀይለ ክሕደትን አድክመው ርትዕት ሃይማኖትን አቆይተዋል። በእኛም ዘመን በርካታ ውይይትና ምክክር የሚያስፈልጋቸው ዐበይት ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ጥያቄዎች በመኖራቸው፤ ያለፈውን ለማጽናት፣ የሚመጣውን ለማቅናት የሊቃውንት መሰባሰብ እጅግ ተገቢ ሆኖ ይገኛል።”

ቤተ ክርስቲያኗ ይህንን የመሰለ በርካታ ዘመናትን የተሻገረ፣ እጅግ የዳበረ አሠራር እያላት ክብሯ በማኅበራዊ ሚዲያ ለሚገኝ ፍርፋሪና “ዕውቅና (ላይክ)” ቀን ተሌት “በሚለፉ” መጻጉ የዕውቀት ድኩማን መዳፍ ሥር መውደቁ አብሮ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው።    

አቡነ ገብርኤል ያቀረቡት መልዕክትን በተመለከተ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ለረቡዕ” ቀጥሮት የነበረውን “የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት የሚገኙበትን” ውይይት ወደ አርብ አስተላልፎታል።

በተለመደው አሠራርና በበርካታዎች ዘንድ እንደሚጠበቀው በዚህ ዕለት ሲኖዶሱ ይህንን ስነ መለኮታዊ ጉዳይ በሊቃውንት ጉባዔ እንዲታይ ያደርጋል። ቀጥሎም የሊቃውንቱ ጉባዔ የሚሰጠውን አስተያየት ተመርኩዞም በአቡነ ገብርኤል ላይ ሲኖዶሱ ውሳኔ ያስተላልፋል። እስከዚያ ግን ዝምታ ወርቅ ነው።  

“ወኵሎ አመክሩ፣ ወዘሠናይ አጽንዑ።” “ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ” የሚለውን የቅዱሱን መጽሐፍ መመሪያ መከተል እየተቻለ (1ኛ ተሰሎንቄ 5:21) አስተዳደራዊውንም ሆነ አስተምህሮ ላይ ያነጣጠረውን ጉዳይ ሁሉ በግድ ለጥጦ ፖለቲካዊ ማድረግ፤ በተለይ ደግሞ ከርካሽ የዘር ፖለቲካ ጋር በማያያዝ በግድ እሳት ለማቀጣጠል መሞከር ወይ በሚያምኑት አስተምህሮ ላይ የዕውቀት እጥረት እንዳለ የሚያሳይ ነው ወይም አርነት የሚያወጣውን እውነት ማዳፈን ነው። ሁለቱም ያስኮንናል እንጂ አያጸድቅም።

ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።


ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡  @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter

homeOPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“አትደንግጡ፣ ማርያም የዓለም ቤዛ አይደለችም!” ያሉት ጳጳስ ሊገመገሙ ነው፤ ሲኖዶስ መከሮ ለውሳኔ ቀጠሮ ያዘ
ሶስት ኃይሎች ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳያመሩ ስጋት የገባቸው ጥሪ አቀረቡ፤ የታደሰ ወረዳ መፎረሽ ስጋቱን አብሶታል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
OPINION

እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

April 8, 2026
OPINION

ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

April 8, 2026
OPINION

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – የሃሰት ትርክ ዘመቻ በደቦ

March 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2