Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  OPINION  የሚያዋጣን ግን ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ የኢትዮጵያን መስቀል መሸከም ነው
OPINION

የሚያዋጣን ግን ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ የኢትዮጵያን መስቀል መሸከም ነው

Ethioreview newsEthioreview news—April 19, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ሀገርን ለማዳን ወደ ትኅትና፣ ወደ ዕርቅ እና ወደ ምክክር መስቀል አውርዶ ራስን መሠዋት ያስፈልጋል። መስቀል መከራ ነው፤ ስድብ ነው፤ ግርፋት ነው፤ ውርደት ነው። ራሳችንን ለሰላምና ለዕርቅ መንገድ ስናዘጋጅ ከብዙዎች ዘንድ ስድብ፣ ርግማን፣ መከራ፣ ይጠብቀናል። የሚያዋጣን ግን ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ የኢትዮጵያን መስቀል መሸከም ነው። ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ስንል መስቀሏን መሸከም።”

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፤

ትንሣኤ የመሥዋዕትነት፣ የጽናት እና የተስፋ በዓል ነው።

የበደለው ዓለም ነው። የተሠዋው ግን ክርስቶስ ነው። ያጠፋው የሰው ልጅ ነው፣ የካሠው ግን ክርስቶስ ነው። ባለ ዕዳው ሰው ነው። ከፋዩ ግን ክርስቶስ ነው።

More stories

“በነዉጥና በኃይል የበለፀገ ሀገር የለም”

May 2, 2023

ወያኔያዊ አማራነትን አማራ “አማራ ነኝ”

December 6, 2022

ሰውን “ሰው” የሚያደርገው ምንድነው? ከእኛ ይልቅ የጥንቶቹ ዘመናዊ ነበሩ

November 1, 2024

ወግ አጥባቂው የኦክላሆማ ሴናትር ማ’ናቸው?

October 6, 2022

የክርስቶስ ሞት አንድም ለማዳን ነው፤ አንድም ለትምህርት ነው። ስለ ብዙዎች ሲባል መሥዋዕትነት ካልተከፈለ ብዙዎችን ማዳን አይቻልም። ሀገርን፣ ሕዝብን፣ ወገንን ማዳን ከተፈለገ መሥዋዕትነት መክፈል ይገባል። ቃል ክርስቶስ በቃሉ ብቻ አልተናገረም። በመስቀል ላይ ውሎ ፍቅሩን በተግባር ገለጠው እንጂ። ራሱ አስታራቂ፣ ራሱ ታራቂ፣ ራሱም መሥዋዕት ሆነ።

ዛሬ ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ መሥዋዕት ለመሆን የተዘጋጀ መሆን አለበት። በሌሎች መሥዋዕትነት መጓዝ የኦሪት ሰዎችም አድርገውታል። ሺ በጎችንና ሺ ፍየሎችን ሠውተው ነበረ። አልሆነም እንጂ። ሀገርን ማዳን የሚቻለው ሌሎችን በመሠዋት አይደለም። ራስን በመሠዋት እንጂ። የራስን ጉልበት፣ ጊዜ እና ዕውቀት በመሠዋት እንጂ። የራስን ክብርና ኢጎ በመሠዋት እንጂ።

ሀገርን ለማዳን ወደ ትኅትና፣ ወደ ዕርቅ እና ወደ ምክክር መስቀል አውርዶ ራስን መሠዋት ያስፈልጋል። መስቀል መከራ ነው፤ ስድብ ነው፤ ግርፋት ነው፤ ውርደት ነው። ራሳችንን ለሰላምና ለዕርቅ መንገድ ስናዘጋጅ ከብዙዎች ዘንድ ስድብ፣ ርግማን፣ መከራ፣ ይጠብቀናል። የሚያዋጣን ግን ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ የኢትዮጵያን መስቀል መሸከም ነው። ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ስንል መስቀሏን መሸከም።

ትንሣኤ ከጽናት በኋላ የሚገኝ ድል ነው። ከፊቱ የጅምላ ፍርድ አለው፤ ከፊቱ ውግዘት አለው፤ ከፊቱ ግርፋት አለው፤ ከፊቱ መራቆት አለው፤ ከፊቱ መከዳት አለው፤ ከፊቱ የፀሐይ መጨለም፣ የጨረቃ ደም መልበስ፣ የከዋክብትም መርገፍ አለው። በዚህ ሁሉ ግን በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ክርስቶስ በጽናት ቆመ። ስለ ዓላማ ሲባል መከራን ታገሠ። ስለ ሰው ልጅ ሲባል ሁሉን እየቻለ በጽናት ተጓዘ።

ሀገር ጽናት ትፈልጋለች። በመከራዎች እና በውግዘቶች ፊት በጽናት መቆም። በስድብና በንቀት ፊት በጽናት መቆም። እንደ ፀሐይ የሚታዩት ልሂቃን ሲጠፉ፣ እንደ ከዋክብት የሚታዩት ክቡራን ሲረግፉ በጽናት መቆም። አብረው የነበሩ ፈርተውና ተሽጠው ሲከዱ በጽናት መቆም – ሀገር ትፈልጋለች። በሚጸኑት ዘንድ የኢትዮጵያ ትንሣኤ እጅግ ቅርብ ብቻ አይደለም። የሚታይም ነው።

ትንሣኤ ተስፋ ነው። ፈተናው እንደሚያልፍ ተስፋ ይሰጣል። ዓርብን ላየ እሑድ የሚመጣ አይመስልም ነበር። የመቃብሩን ድንጋይ ላየ የሚነሣ አይመስልም ነበር። ማኅተሙን ላየ የሚፈታ አይመስልም ነበር። ጨለማውን ላየ ብርሃን ሩቅ ይመስል ነበር። ሁሉም ግን ተገለበጠ። ታሪክን የታሪኩ ጌታ ለወጠው።

ተስፋችን በደጅ ነው። ዓርብ ላይ እሑድን እናየዋለን። ከሞት ባሻገር ሕይወትን፣ ከመቃብር አልፈንም ትንሣኤን የምንመለከት ነን። የሚጨበጥ ሕልም የጠራ ምናብ አለን። ስለዚህም ወጀብና አውሎ ነፋስ አያስደንቀንም። ዛሬ ለነገ፣ ሞት ለትንሣኤ ቦታ እንደሚለቁ የምናውቅም፣ የምናምንም ነን።

ለኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚተጉ ብዙዎች ናቸው። የሕማማቱ ጊዜ እያለፈ ነው። አሁን ዓርብ ወደ ማታ ላይ ነን። ከጸጥታው ቀን በኋላ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይመጣል። ከሄዱት ብዙዎች ይመለሳሉ። ከተሳሳቱት ብዙዎች ያስተውላሉ። ዓርብ ዕለት በከንቱ የጮኹት ብዙዎች ያፍራሉ። ፈራጆች ይፀፀታሉ። ተገዳዳሪዎች ይበታተናሉ። የመቃብር ጠባቂዎች ይደነግጣሉ። ኢትዮጵያ ግን አይቀሬ በሆነው ትንሣኤ ትነሣለች።

ትንሣኤው ከእሥራኤል ለዓለም እንደተገለጠው ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ለዓለም ትገለጣለች።

የትንሣኤ በዓል የሚያስተምረንም ይሄንኑ ነው።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኬሪያ ኢብራሂም ትርክት ናዱ፤ “ጦርነቱን ማስቀረት ይቻል ነበር” አሉ፤ እኛም ሰማን!
“እባካችሁ ቆም ብላችሁ አስቡና ሰላምና ዳቦ አጥቶ ለተቸገረው ሕዝባችሁ ስትሉ ለሰላማዊ መፍትሔ ዕድል ስጡ” አቡነ ማትያስ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
OPINION

እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ…

April 8, 2026
OPINION

ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት!

April 8, 2026
OPINION

ሙስጠፌ ተረኛው ባለስልጣን – የሃሰት ትርክ ዘመቻ በደቦ

March 28, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2