Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗል
SOCIETY

ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶች በመሸማቀቅ አገር ጥለው እንዲሸሹ እያደረገ ነው፤ ለበርካታ ችግሮች መንስዔ ሆኗል

Ethioreview newsEthioreview news—May 2, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይም ቲክ ቶክ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያባባሰ መሆኑን በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል።በቲክ ቶክ በሚደረግ ማሸማቀቅ ሀገር ጥለው የሚሰደዱ ሴቶች መኖራቸውም ተመልክቷል።የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በአገር ውስጥ ቋንቋዎች የጥላቻ ንግግሮችን መቆጣጠር አለመቻላቸው ደግሞ ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል ተብሏል።

ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሪሲሊንስ የተሰኘው የብሪታኒያ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በዚህ ወር ይፋ ያደረገው ጥናት እንዳመለከተው ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ የፖለቲካ፣ የብሔር እና የሃይማኖት ግጭቶችን እያባባሱ ነው ።
የድርጅቱ የጥናት እና ምርምር ሥራ አስኪያጅ ፌሊሺቲ ሞልፎርድ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት “በኢትዮጵያ በበይነመረብ  ላይ የጥላቻ ንግግር እስከ ግድያ የሚያደርስ አሉታዊ ውጤት አስከትሏል።
በጥናቱ  መሰረት ባህላዊ የሥርዓተ-ፆታ ሚናዎችን  የሚቃወሙ፣  በአመራር ቦታ ላይ ፣ በስፖርት ዘርፍ ያሉ ወይም ለሴትነት እና ለሴቶች መብት በሚሟገቱ   ሴቶች ላይ ከፍተኛ እንግልት ይደርስባቸዋል።የነፃነት ፖድካስት አዘጋጅ ፅዮን ብሩክ በጥናቱ ትስማማለች። ፅዮን እንደምትገልፀው በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይም በቲክ ቶክ በሚተላለፉ ይዘቶች የተነሳ በሴቶች ላይ ከበይነመረብ ዘለፋ አልፎ አካላዊ ጥቃት ይደርሳል።

ችግር የተሞላበት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህር የሆኑት ወርቅነህ ድሪብሳ በበኩላቸው ፣በኢትዮጵያ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም በተለይ ቲክ ቶክ ችግር የተሞላበት ነው ይላሉ።  
ድምፅ 2የጅማ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህር የሆኑት ወርቅነህ ድሪብሳ
በተለይ እይታን እና የተከታይን ቁጥር ለመጨመር ሆን ተብለው የሚሰሩ በሴቶች በአካል ጉዳተኞች የዘለፋ እና የጥላቻ የሰዎችን ክብር የሚነኩ ይዘቶች ላይ ቁጥጥር እና ቅጣት አለመኖሩ ችግሩን እንዳባባሰው ይገልፃሉ።

ያም ሆኖ እነዚህ የግለሰብን እና የማኅበረሰብን ክብር በሚነኩ ይዘቶች ከመወገዝ ይልቅ እነሱን የሚያበረታታ እና በተለያዩ ድርጅቶች ማስታወቂያ በማሰራት የተለዬ ጥቅም እንዲያገኙ  እየተደረገ  መሆኑ ደግሞ ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ የከፋ  እንዲሆን አድርጎታል ሲሉ ያብራራሉ።
ይህም ሴቶችን በማሸማቀቅ ከተሳትፎ በመገደብ  እና ያሉትን የጥላቻ ንግግሮች በማስፋፋት  በማኅበረሰቡ ያደረሰው አሉታዊ ተፅዕኖው ቀላል አይለም።
ተንታኞች እንደሚናገሩት እንደ  ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች  ብዙ ጊዜ በአገር ውስጥ ቋንቋዎች የሚነገሩ የጥላቻ ንግግሮችን መቆጣጠር እና ማጣራት ባለመቻላቸው  የከፋ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ።

በቲክቶክ ሴቶችን ማሸማቀቅ እና ከተሳትፎ መገደብ

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022

ታሪኳን ለአፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ያጋራችው  ሌይላ ምስክር  የዚህ ገፈት ቀማሽ ናት።በኢትዮጵያ የሥርዓተ-ፆታ መብትን በሚመለከት በበይነመረብ በምታቃርባቸው ፅሁፎች ብዙ ተከታዮችን ያፈራችው ሌይላ ነገር ግን የሀገር ውስጥ ቋንቋ ይዘት ክትትል ባለመኖሩ  በቲክ ቶክ በደረሰባት ዛቻ እና ማስፈራሪያ ለስደት መዳረጓን ተናግራለች።
የሌላ ችግር የጀመረው ጥቅምት 22 ቀን ሴቶች ከሚጎዷቸው ወንዶች እንዲርቁ የሚመክር ቪዲዮ በቲክ ላይ ከለጠፈች በኋላ ነው።የሌላ የቪዲዮ ይዘት በአንዳንድ የቲክ ቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ዘንድ መልዕክቱ  «በወንዶች ላይ የተደረገ የጥላቻ ዘመቻ» እና የሀገሪቱን ሀይማኖትና ባህል የማያከብር ነው መባሉንም የዜና ወኪሉ አስፍሯል። የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አያይዞም በሌሎች ፅሁፎች ሌይላ፤በኢትዮጵያ ህግ በወንጄል የሚያስቀጣውን ግብረ ሰዶማዊነትን እንደምትደግፍ  ተደርጎ መቅረቡንም ጠቁሟል።በዚህም የግድያ ዛቻዎችን ጨምሮ እሷን ዒላማ ያደረገ የቲክቶክ ቡድን እንደነበረም ለዜና ወኪሉ ተናግራለች።በደረሰባት ዛቻ ምክንያትም ቤተሰቧ፣ ስራዋን እና ያላትን ሁሉ ትታ  ወደ ጎረቤት ሀገር መሸሿን ገልፃለች።ይህ ክስተት የስነ ልቦና እና የገንዘብ ችግር እንደፈጠረባት ተናግራለች።

በአማርኛ ፣ በትግርኛ እና የአፋን ኦሮሞ  እንዲሁም ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚቀርቡ ይዘቶችን በተገቢ ሁኔታ ማስተካከል ባለመቻሉ ቲክክ ቶክ ለተከሰተው ችግር የተወሰነ ኃላፊነት እንደሚወሚወስድ ሌላ ተናግራለች።በስርዓተ ጾታ ላይ ያተኮረው የነፃነት ፖድካስት አዘጋጇ ፅዮን ጉዳዩን« አስፈሪ »ስትል ትገልፃለዋች።
ለይላ ለዜና ወኪሉ እንደተናገረችው «በቲክ ቶክ ላይ በኢትዮጵያውያን ወንዶች የተሰሩ ብዙ ቪዲዮዎችን ተመልክቻለሁ ስለሴቶች አሰቃቂ አስተያየቶችን ሲሰጡ አይቻለሁ ነገር ግን ምንም እየተደረገ አይደለም» ብላለች።ፂዮን ብሩክ የለይላን ሀሳብ ታጠናክራለች።

 የቴክኖሎጅ ኩባንያዎች ሀላፊነትን እንዲወጡ ማስገደድ

ቲክ ቶክ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደገለፀው «የጥላቻ ንግግሮችን እና ሴትነትን ዝቅ የሚያደርጉ ይዘቶችን እንደማይታገስ  እና 92 በመቶ የሚሆኑ ይዘቶችን ለእነርሱ ሪፖርት ከመደረጉ በፊት በቴክኖሎጂ እና በሰዎች ጥምረት  አማርኛን ጨምሮ ከ 70 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጠቀም ያስወግዳል።
ያም ሆኖ ባለሙያዎች እንደሚሉት ችግሩን ለመቀነስ የቴክኖሎጅ ኩባንያዎች ሀላፊነትን እንዲወጡ ማስገደድ ያስፈልጋል።የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የበለጠ ኃላፊነት እንዲወስዱ ለማስገደድ ከሚሞክሩ አገሮች መካከል ኬንያ አንዷ ነች። የኬንያ ፍርድ ቤቶች የፌስቡክ ዋና ኩባንያ በሆነው በሜታ ላይ በመድረኩ ላይ በቀረቡየጥላቻ ንግግሮችን  ላይ በቅርቡ ብይን ሰጥቷል። ከነዚህም አንዱ በጎርጎሪያኑ 2021 ዓ/ም በፌስ ቡክ ስሙን፣ ፎቶውን እና አድራሻውን ጨምሮ  የትግራይ ወታደራዊ ሀይሎች  አባል ነው ተብሎ ከተለጠፈ በኋላ፤ የተገደለውን የዩንቨርስቲ መምህር መአረግ አማረን ያካትታል። 
የጅማ ዩንቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህርሩ ወርቅነህ ድሪብሳ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች  በተለይ ቲክ ቶክ ካደረሰው ችግር ብዛት እና ጥልቀት አንፃር ለመፍትሄው ዘግይተናል ይላሉ። ያም ሆኖ አሁንም ቢሆን ችግሩን ለመፍታት የረዥም እና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን ይጠቁማሉ።
በሌላ በኩል የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ባለቤት የሆኑ ኩባንያዎችም የይዘት ክትትል እንዲያደርጉ ማስገደድ ሌላው መፍትሄ መሆኑንም ይገልፃሉ።

የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች የይዘት ክትትል መቀነስ እና መዘዙ

ሜታ በጎርጎሪያኑ ያለፈው ጥር ወር በዩናይትድ ስቴትስ የሚያደርገውን የእውነታ ማጣራት መርሃ ግብሩን ማብቃቱን አስታውቋል። ይህ  ርምጃ ደግሞ አፍሪካን ጨምሮ  በሌሎች ሀገራት ችግሩ እንዲባባስ ሊያደርግ  ይችላል የሚል ስጋት አለ።በእስያ-ፓሲፊክ፣ በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በላቲን አሜሪካ እና በአፍሪካ የእውነታ ማረጋገጫ አገልግሎቶችን በማቅረብ ላይ የሚገኘው የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፤እንዳሰፈረው «የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች የይዘት ክትትል  እንደገና ካልተጀመረ  እንደ ኢትዮጵያ ባሉ  የፖለቲካ ልዩነቶች እና ስጋቶች በበይነመረብ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ባለባቸው ሀገራት፤ አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።»ሲሉ፤ የሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሪሲሊንስ  ሀላፊ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል   የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች  ግጭት  እና ከጎረቤት ኤርትራ ጋር  ውጥረት በነገሰባት ኢትዮጵያ፤ሁኔታው ጥላቻ እንዲያጎለብት  ብቻ ሳይሆን  የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዳይታረም ያደርጋል። ሲሉ ኢትዮጵያዊቷ የዲጂታል መብት ባለሙያ መግደላዊት ጌታሁን ለዜና ወኪሉ አስረድተዋል።

ጸሃይ ጫኔ DW


ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡  @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter


SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ ታደርጋለች”
ብፁዓን አባቶች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ መንግስት ውሳኔ አሳለፈ፤ ሲኖዶስ ቀና ምላሽ ስላገኘ ምስጋና አቅርቧል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2