Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የትግራይ ህዝብ የሰላም፣የህልውናው እና ደህንነቱ ዘብ እራሱ ህዝቡ ነው -ዶ/ር አብርሃም በላይ

    May 29, 20210

    በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው አሸባሪ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ ተወሰደበት

    September 4, 20210

    Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD

    July 4, 20210

    በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ተቀጡ

    June 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

    July 23, 20210

    መከላከያ በኦሮሚያና አማራ ክልል የማጽዳት ስራ እንደቀረው አስታወቀ፤ አማራ ክልል መዋቅሩን እያጠራ ነው፤

    September 1, 20230

    “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”

    April 17, 20210

    “በተለመደው አሰራር ማስቀጠል የምንችለው ድህነትን ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ

    June 3, 20220

    “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች?”

    March 9, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  SOCIETY  መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?
SOCIETY

መታወቂያዎን ከብጉር፣ ከማድያትና መቃጠል እየተከላከሉት ነው?

Ethioreview newsEthioreview news—May 4, 20250
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ዶክተር ጽዮን ተስፋ በአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ  ሆስፒታል የቆዳ ህክምና ስፔሻሊስት  ሀኪም ናቸው።

በራሳቸው ተነሳሽነት ደግሞ «አለርት ጉርሻ»  በሚል በኦን ላይን ፕሮግራማቸው «ትኩረት ያልተሰጣቸው» በሚባሉ የበሽታ አይነቶች ዙሪያ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። 

በዘፈቀደ ከምንንከባከባቸው አለያም ጭልጥ አድርገን ከምንረሳቸው የአካል ክፍሎችችን አንዱ መታወቂያና መለያችን የሆነው ፊታችን ነው።

የፊት ቆዳ ተጋላጭ ከመሆኑም በላይ ሲቻል ሳይንሳዊ እንክብካቤ ሊደረግለት የሚገባ ትኩረት የሚሻ የአካል ክፍል ነው።

ዶክተር ጽዮን እንደሚሉት  በአለርት ሆስፒታል በተመላላሽ ህክምና  ክፍል በብዛት የሚታከመው ታካሚ ወደ ሆስፒታሉ ብቅ የሚለው በቆዳ ህመም ምክንያት ነው።

የቆዳ ድርቀት፣ በፈንገስ፣ በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት  ኢንፌክሽን፣ ብጉር፣ ለምጽ፣  የቆዳ ካንሰር፣ የጸጉርና የጥፍር  በሽታዎች፤ ስጋደዌ እና  የተዘነጉ የሚባሉ ሌሎች  ህመሞችም ጭምር ናቸው።

እነዚህ በቆዳ ላይ የሚከሰቱ  በሽታዎች መነሻ ምክንያታቸው  የተለያየና በርካታ መሆኑን ዶክተር ጽዮን ይናገራሉ።

ዋነኛው መነሻው ግን   በፈንገስ፣ በባክቴሪያ  ወይም በቫይረስ  ምክንያት የሚመጣ ኢንፌክሽን ነው ይላሉ። 

የራሳችን ሴሎች በራሳችን ላይ ጉዳት በሚያመጡበት ጊዜ  እንደ ቆዳ ድርቀት እና ለምጽ ሊከሰት ይችላልም ይላሉ።

የአኗናር ዘይቤችን፣ የጸሀይ ብርሀን፣ የጸሀይ ጨረር፣  አለርጂ፣ የሆርሞን መዛባት እንዲሁም በተፈጥሮ የሚመጡ  በከፍተኛ ጭንቀት የሚከሰቱ የቆዳ በሽታዎች እንዳሉም ይጠቅሳሉ።

አብዛኛው የቆዳ በሽታ የሚከሰተው  በአንድ  ምክንያት ሳይሆን የተለያዩ ምክንያቶች   በአንድ ላይ በመደራረብ  መሆኑን የሚያስረዱት ዶክተር ጽዮን፤ በተለይ የሴቶችን ፊት የሚያበላሹ እንደ ቡጉር፣ ማዲያት እና  የፊት  መቃጠል የሚባሉ  በሽታው ምንነትና ህክምና ማወቅ ይገባል ይላሉ።

ብጉር   በሴቶች ላይ በብዛት የሚታየው የቆዳ በሽታ በማለት  ዶክተር  ጽዮን የገለጹት፤  በተለይ በታዳጊ ሴቶች ላይ በብዛት የሚከሰተው  ብጉር እና የቡጉር ጠባሳ ወይም  ሁለቱም አንድ ላይ  ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ።

ሁሉም አይነት ቡጉር ተመሳሳይ አይደለም።  ስለዚህ  በተመሳሳይ ህክምናም ሊታከም አይችልም። ብጉር ሶስት አይነት ደረጃ አለ። ይሄውም  አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ደረጃ የሚባል ነው።

አነስተኛ የሚባለው የብጉር አይነት ፊት ላይ ብቻ የሚታይ፣ ትናንሽ  ሽፍታ፣ እንዲሁም በጠቅላላው ከ30  በታች ቁጥር ያለው ሲሆን ይሄን አይነቱ በቀላሉ በቤት ውስጥ  መታከም  የሚችል መሆኑን ይጠቅሳሉ።

መካከለኛ  የሚባለው የቡጉር አይነት ደግሞ ጥቁር ወይም ነጭ ሽፍታዎች፣ እብጠት፣  ከ30 እስከ 125   ቁጥር ያለው ሲሆን ይሄም ከፊት አልፎ ጀርባ  ላይ ይገኛል። 

የዚህ አይነት ብጉር በመታጠቢያ እና በሚቀባ መድሀኒት መታከም ያለበት በመሆኑ  ወደ ህክምና ተቋም  መሄድ የተሻለ  መሆኑን ይመክራሉ።

ከፍተኛ ደረጃ  የሚባለው መጠኑ  ትላልቅና  መግል የያዘ ሲሆን ከፊት ላይ አልፎም   በሌሎች ቦታዎች   ላይ ይገኛል።የጠለቀ የቆዳ ላይ ጠባሳንም የሚያስቀር ነው። 

በቁጥርም  ከ125 በላይ በመሆኑ የዚህ አይነቱ የቡጉር አይነት   ከሚቀባው መድሀኒት በተጨማሪ የሚዋጥ መድሀኒት  ሊሰጥ ይችላል።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሆርሞን የሚከሰት  የቡጉር አይነት መኖሩን ዶክተር ጽዮን ይጠቅሳሉ። ይሄ በመንጋጋ አካባቢ   ከ30 ዓመት በላይ በሆነች ሴት ላይ  ሲከሰት የተለየ ህክምና ያስፈልገዋል።

በቤት ውስጥ ብጉርን ለመቀነስ የሚደረገው  ጥንቃቄ  በማለት ዶክተር ጽዩን የነገሩን ደግሞ ፊትን በቀን አንድ ወይም  ሁለት ጊዜ   ለሰስ ባለ ውሀ መታጠብ፣  ሀይለኛ የሚባሉ ሳሙናዎችን አለመጠቀም፣ በምትኩ  ሳሙና ያልሆኑ የፊት ማጽጃዎችን   እንደ ክሌንዘር አይነት መታጠቢያዎችን  መጠቀም ተመራጭ መሆኑን ይመክራሉ።

ሌላው ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ ሰውነት ላብ ሲኖረው መታጠብ ፣ፊትን  ደጋግሞ አለመነካካት ፣ ፊትን ፈትጎ አለመታጠብ ፤ ብጉርን አለመነካካትና አለመጭመቅ ሲሆን ብጉርን  ማፍረጥ የበለጠ ያባብሳል፤ቆዳን  ሊጎዳና ወደ ኢንፌክሽን  ሊያደርስ ይችላል።

ሰዎች ከልክ በላይ ብጉርን የመነካካትና የማፍረጥ ልምድ ይኖራቸዋል። ይሄ የታከከ ብጉር  የሚባለው  ነው። ቆዳቸው በሚመረመርበት ጊዜ ብጉር የላቸውም  ነገር ግን   ብጉሩን በማፍረጥ   ጠባሳ እንዲቀር  ሆናል። ይሄ አንዳንድ ጊዜ ከአእምሮ ህሙማን ጋር ይገናኛል።

በመስታወት ፊት ለፊት ብዙ ሰዓት ማሳለፍ ሰዎች  ብጉርን ለማፍረጥ  ያላቸውን ፍላጎት ይጨምራል። ስለዚህ  ይሄ መጥፎ ልማድ ሊቀር የሚገባው መሆኑን ዶክተር ጽዮን ይገልጻሉ።

እንዲሁም ወዝ ላይ የተመሰረተ  ሜካአፕ  እና የቆዳ ማሳመሪያዎችን  ማስወገድ ያስፈልጋል። ፊት ላይ የሚደረግ ሜካፕ ወዝ የማያመጣ፤ ብጉር የማያባብስ  መሆን አለበት።  ስለዚህ ሜካፕ መጠቀም የሚፈልግ ሰው በጣም በጥንቃቄ መሆን አለበት።

የውበት ማሳመሪያ ምርቶች  ከወዝ (ኦይል)  ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ። «ይህም ሲባል የፊት ቅባት መጠቀም የለብንም ለማለት አይደለም።

ወዛም ቆዳ፣ ቡጉር ያለበት ሰው  የሚጠቀመው የፊት ቅባት  ለወዛም ፊት ተብለው የተሰሩትን መሆን አለበት። ወዛም ቆዳ ያለው ሰው ቅባት አይጠቀምም የሚለው የተሳሳተ ነው።

ወዝ አለው ማለት እርጥበት አለው ማለት አይደለም።ወዝ ያለውን ፊት ድርቀትም ሊያጠቃው ይችላል። ስለዚህ  የፊት ቅባቶችን  መጠቀም ይኖርብናል። 

የፊት ቅባት መጠቀም ሰውነታችን ከልክ በላይ  ወዝ  እንዳያመርት  ይረዳዋል። በተለይ ደግሞ የቡጉር መድሀኒቶችን በሚጠቀሙ ወቅት ፊትን ስለሚያደርቀው ሰውነታችን ብዙ ወዝ ያመርታል።ስለዚህ  ድርቀትን ሊከላከል የሚችል ቅባት መጠቀም ያስፈልጋል።»በማለት ሙያዊ  ምክራቸውን ይለግሳሉ።

ሌላው መረሳት የሌለበት ጉዳይ በማለት  ዶክተር ጽዮን  የነገሩን፤ የመኝታ  ትራስ  ጨርቅና  የፊት  ፎጣዎችን   ማጽዳት ነው።  የትራስ  ጨርቆችን በየሳምንቱ ማጠብና መቀያየር   እንዲሁም የፊት   ማድረቂያ ፎጣዎችንም ጽዳት  መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን አስምረውበታል።

  «ብዙ  ጊዜ  የትራስ ላይ ቅባት የተለያዩ  ቆሻሻ  (ባክቴሪያ) ይስባል። ይሄ ደግሞ  ቡጉሩ ድጋሚ እንዲከሰት ያደርጋል።  በመሆኑም  ተገቢው   ጥንቃቄ ማድረግና ንጽህናን መጠበቅ ያስፈልጋል» ብለዋል።

ብጉርን ለማጥፋት ወይም ለመቀነስ በሚል ሰዎች የተሳሳተ መንገድን እንደሚከተሉ  ዶክተር ጽዮን ይጠቅሳሉ። ይሄውም አንዳንድ ጊዜ ሎሚን ለብጉር ማጥፊያ ተጠቀሙ ሲባል ይሰማል።  ሎሚ ግን ፊትን የበለጠ ያደርቃል። እንደነዚህ አይነት ነገሮችን ከባለሙያ ምክር ውጪ መጠቀም ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላው  ፊት በማበላሸት የሚታወቀው በሴቶች ላይ ጎልቶ  የሚታየው  የቆዳ ቀለም ለውጥ ሲሆን ይህም  እንደ ማድያት ፣ የፊት ቃጠሎ የሚባለው ነው።የዚህ መነሻ ምክንያቱ   ቅባቶች፣ የጸሀይ ብርሀን፣ የቆዳ  ድርቀት እንዲሁም ከመድሀኒት ጋር ተያይዞ የሚመጣ  መሆኑን ያስረዳሉ።

ለምሳሌ ማዲያት የቆዳ ቀለም በሽታ ሲሆን ቡኒ ወይም ግራጫ ቡኒ  የሚመስል በጉንጭ፣በአፍንጫ፣ በግንባር እና በላይኛው ከንፈር ላይ የሚወጣ ነው።

ማዲያት የሚነሳው በጸሀይ ብርሀን ወይም  በሆርሞን መዛባት ምክንያት  ሊሆን እንደሚችል ዶክተር ጽዮን ይናገራሉ።  ለምሳሌ በእርግዝና እና የእርግዝና መከላከያ መድሀኒት በመውሰድ ወይም ደግሞ በዘር የሚመጣ አለ።

ዶክተር ጽዮን ማዲያትን መከላከያ ዋነኛው መንገድ በማለት የገለጹት ጸሀይን መከላከል ሲሆን ጸሀይንና የጸሀይ ጨረር ለመከላከል አንድ ላይ የተሰራ መድሀኒት መጠቀም  አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ። 

የጸሀይ መከላከያ መድሀኒት ከመጠቀም ባለፈ  ሰፋፊ ኮፍያ ማድረግ ፣ጃንጥላ መያዝ  እንዲሁም  ሀይለኛ  ጸሀይ በሚኖርበት ወቅት  ከቤት አለመውጣት የመሳሰሉት የመከላከያ መንገዶች መሆናቸውን አብራርተዋል።

ማድያትን ማከም እንደሚቻል ነገር ግን ጊዜ የሚወስድና ከፍተኛ ክትትልና ጥንቃቄን የሚጠይቅ ነው ።ለህክምናውም  ተቀምመው የሚቀቡ መድሀኒቶች ይታዘዛሉ። 

ማዲያቱ እንዳይመላለስ ለማድረግ  ሜንቴናንስ የሚባለው ህክምና በጣም ወሳኝ ነው።ይሄ በህክምና አንዴ ከተሻለ በኋላ መልሶ  ሊመጣ ይችላል። ስለዚህ ድጋሚ እንዳይነሳ የሚሰጠው መድሀኒት  ተከታትሎ መጠቀም ወሳኝ  መሆኑን ያስረዳሉ።

ዶክተር ጽዩን እንደሚሉት፤ማዲያት ብዙ ጊዜ  ፊት ላይ ይወጣል፤ በእርጉዝ ሴቶች ላይም የተለመደ ነው። ይሄ ማለት ግን እርጉዝ  ያልሆኑት ላይ አይከሰትም ማለት አይደለም።

በተለይ  ጸሀይ ላይ የሚውሉ ሰዎች ላይ በርከት ብሎ ይታያል።ብዙ ጊዜ በሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ወንዶችም ላይ  ይታያል።

ማዲያት ሶስት አይነት ነው። ይሄውም የላይኛው ቆዳ ላይ፣ የውስጠኛው የቆዳ አካል ላይ  ወይም ደግሞ  በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል።  የመጀመሪያ ቆዳ ላይ የሚወጣው በቀላሉ የሚታይ ነው። 

ቀለሙም  ደመቅ ያለ ቡኒ ሲሆን በህክምና ለመመለስም ቅርብ  መሆኑን ያስረዳሉ።  የውስጠኛው የቆዳ አካልን በሚያጠቃ ጊዜ   ነጣ ያለ ቡኑ  ወይም ወደ ግራጫ  ቀለም የሚሆን ሲሆን፤    ለመድኃኒት የሚሰጠው ምላሽ ግን አነስተኛ ነው። 

አንዳንዴ ደግሞ  የላይኛውንም የውስጠኛውንም የቆዳ ክፍል  አንድ ላይ በሚጎዳበት ጊዜ ምላሹም ግማሽ በግማሽ  እንደሚሆን ይናገራሉ።

ዶክተር ጽዮን እንዳሉት፤ የማድያት ህክምና በማጉያ   መሳሪያ በባለሙያ የሚታይ ይሆናል። ከሌሎች አይነት በሽታዎች ( የቆዳ ጥቁረቶች)   የተለየ መሆኑን ሀኪሞች ይለዩታል።

ህክምናው በዋነኛነት ግን  ከጸሀይ   ፊትን መከላከል ሲሆን ይሄ ደግሞ   እድሜ ልክ የጸሀይ መከላከያን መጠቀም ነው። 

በቤት ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ መስታወት አጠገብ አለመሆን ተመራጭ ነው። ጸሀይ የመከላከል አቅሙ 50+ የሆነ ሰንስክሪን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ። ከሆርሞን ጋር የተገናኘ ከሆነም ያንን ያመጣውን መድሀኒት ማቆም ወይም መቀየር ይገባል።

የማዲያት ህክምና የተለያየ ሲሆን  በባለሙያ የሚቀመም ፣ ታሽጎ የሚሸጥ  እና የሚዋጥ መድሀኒት  መኖሩን  ይናገራሉ። ይሄ የሚሆነው  በሀኪም ታዞና አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ መሆን እንዳለበትም ይጠቅሳሉ።

የማዲያት መንስኤው የተለያየና ውስብስብ ሲሆን  ዋናው ነገር ግን  በጸሀይ ጉዳት የሚመጣ ነው። በዘር የሚመጣም ይኖራል። 

በቤተሰብ ደረጃ ካለ  60 በመቶ  በማዲያት የመጠቃት አጋጣሚ ይኖራል። አንዳንድ ጊዜ ከስጋደዌ በሽታዎች ጋርም የተገናኘ   ሊሆን ይችላል። ከሌሎች አዳዲስ መድሀኒቶች ፣ የካንሰር መድሀኒቶች  ጋር ተያይዞም የመከሰት አጋጣሚው መኖሩን  አስረድተዋል።

«የፊት  መቃጠል»  የሚባለውም ሌላው በሴቶች ፊት ላይ ጎልቶ የሚታየው  በሽታ ነው። ይሄ በሽታ የሚመጣው በፋርማሲ ውስጥ ወይም በሱቅ ደረጃ  እየተሸጡ በሚገኙ «ፊት ማሳመሪያ» የሚባሉትን ፤ያለ ሀኪም  ትዕዛዝ  የተዘጋጁ መድሀኒቶችን   ወይም ደግሞ   በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ቤት  የሚገቡ የመዋቢያ  ምርቶችን   በመጠቀም የሚመጣ  ነው።

በተለይ ደግሞ  ለፊት ጥራት እየተባለ የሚወሰድ  መድሃኒት   ዘላቂ የሆነ ጉዳት እንደሚያስከትል ይገልጻሉ። 

የተቃጠለ ፊት ምልክቱ ፊት  ቀይ ቀይ  የመሆን ፣ ቀጫጭን ደም ስር የማውጣት፣የመቀንቀን በተለይ  ጸሀይ ላይ በሚቆዩበት  ጊዜ    የሚያቃጥል ስሜት ያስከትላል።

ጸሀይ ላይ በሚኮንበት  ሰዓት በጣም የማቃጠል ስሜት ይኖረዋል።   ይሄንን  ለመከላከል የሚቻለው ከውጪ የሚመጣን መድሀኒቶች በማቆም  ብቻ ነው።

ህብረተሰቡ  እንደዚህ አይነት ለሰው ልጆች ጤና መቃወስ ምክንያት የሆኑ ምርቶች  ወደ ሀገር ቤት እንዳይገባና ህብረተሰቡም እንዳይጠቀማቸው ተገቢውን ትምህርት መስጠት ተገቢ መሆኑን ይናገራሉ። በተለይ «ስቶይሪድ » የሚባል የቆዳ መድኃኒትን ካለ ሀኪም ትእዛዝ መጠቀም ትርፉ  ጉዳት መሆኑን ይጠቅሳሉ።

« እነዚህ መድሀኒቶች የተሰሩትም ለፊት ተብሎ አይደለም። ማንኛውንም  መድሀኒት ከሀኪም ጋር ምክክር ሳይደረግ  ፊት ያጠራል ስለተባለ ብቻ መጠቀም  ከሚያመጣው ጥቅም ይልቅ ዘላቂ ችግር ያስከትላል።

ይሄ ፊትን  በከፍተኛ ደረጃ  የሚጎዳና ዘላቂ  የሆነ የፊት መሳሳት የሚያስከትል  ነው» ሲሉ የተናገሩት አጽንኦት ሰጥተው ነው።

Via በአልማዝ አያሌው GazettePlus


ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡  @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter


SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር የሁል ጊዜ ስራችን ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
የቶማስ ሳንካራ ባለቤት ደብዳቤ ለካፒቴን ትራኦሬ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 20250
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 20250
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
Load more
Recent Posts
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
  • International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies June 3, 2026
  • ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤ June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news