አገራቸው በሶማሊላን በርበራ ወደብ የባህር ሃይል ሰፈር በምታቆምበት አግብብና በለሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ከሶማሊላንድ ጋር መክረው አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (አፍሪኮም) ጀነራል ሚካሄል ላንግሌይ የተመራ ልዑክ ቡድን ከመከላከያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ጋር መምከራቸው ተገለጸ። አብረው ለመስራት ተሰማሙ።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (አፍሪኮም) ጀነራል ማይክል ላንግሌይ የተመራ ልዑክን ተቀብለው በቢሯቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ያስታውቀው የአገር መከላከያ የኦንላይን ሚዲያ ነው።
አሜሪካ ጀነራል ማይክል ላንግሌይ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቃለች። ውይይቱም በአፍሪካ ቀንድ የአልሸባብ እና የአይኤስ የሽብር ስጋትን መከላከል ላይ ያተኮረ እንደነበረም ጠቁማለች። ከዚህም በተጨማሪ ጀነራል ማይክል ላንግሌይ ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ጋር መምከራቸውን ገልጻለች።

ሁለቱ አገሮች በቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት፣ በቀጠናው ውስጥ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት፣ በሱማሊያ ያለውን ሽብርተኝነት በጋራ በመዋጋት ፣ በአፍሪካ ቀንድ የረዥም ጊዜ መረጋጋትን መደገፍ በሚቻልበት አግባብ ትኩረት ያደረገ ምክክር መደረጉን አሜሪካ አሳውቃለች።
በምክክሩ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ አሜሪካና ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት በላይ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው አገራት እንደሆኑ አመልክተዋል። አክለውም ” ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በመከላከያ ዘርፉ በቀጣይም በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል ” ብለዋል።
ሁለቱ ከፍተኛ መኮንኖች ባካሄዱት ውይይት በቀጠናው አሁን ላይ ባለው ሁኔታ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተመልክቷል። በተለይም በቀይ ባህር ፣ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በሚታዩ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸው ይፋ ሆኗል።
የአፍሪኮም አዛዥ ጄነራል ሚካኤል ላንግለይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ከፍተኛ ሚና ያላት ሀገር ናት ሲሉ መናገራቸውን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ገጹ አመልክቷል።
ጄነራሉ አሜሪካና ኢትዮጵያ በቀጣይ በወታደራዊና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን እንደተናገሩ ከመከላከያ ገጽ ለመረዳት ተችሏል።
ቀደም ሲል ኢትዮጵያ የአሜሪካ የቀይ ባህር ቁልፍ አጋር እንደሆነች መገለጹ አይዘነጋም። ኢትዮጵያ የባህር በር እንዲኖራት የያዘችው አቋም በግለት እንደሚቀጥል የአገሪቱ ከፍተና የሰጸጥታ ኃይል አቋም ማስተላለፉ አይዘነጋም።
ይህንኑ አቋም ተከትሎ ሻዕቢያ “ለምን ቀይ ባህር ተባለ” በሚል በይፋ ከግብጸና ሶማሊያ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ መጀመሩ አይዘነጋም። ከግብጽ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ በመዝለቅ ከትህነግና በተለይ ከጎጃምና ምሬ ወዳጆ ከሚመራው አሁን ላይ ኮረም አካባቢ ካለው የፋኖ ኃይል ጋር ግንባር ፈጥሮ ጦርነት ለመቀሰቀስ ክተት ባወጀበት ወቅት ኢትዮጵያና አሜሪካ በቀይ ባህር ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ለኢትዮጵያ ታላቅ የፖለቲካ ድል ተደርጎ ተውስዷል።
ሰሞኑን በሰብአዊ መብት አያያዝና በስውር በሰው ልጆች ላይ በሚያደርሰው ግፍ በአስቸኳይ ሊጠየቅ እንደሚገባ በተባበሩት መንግስታት በኩል መግለጫ የወታበት፣ን ላለፉት 33 ዓመታት ኤርትራን እስር ቤት እንዳደረገና እንዳወላለቋት በስፋት ተቃውሞ እየወታባቸውና ከሽብር ወንጀል ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ያሉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይህ ዜና መርዶ እንደሚሆንባቸውም እየተገለጸ ነው።
አምባሳደር ብናልፍ በዋይት ሃውስ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸው ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያደረጉት ውይይትና የዲፕሎማሲ ድል፣ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (አፍሪኮም) ጀነራል ማይክል ላንግሌይን ጉብኘት አስመልክቶ ሻዕቢያን ወግነው የተሰለፉ ” ኢትዮጵያዊ ” ስም ያላቸው ሚዲያዎች አልዘገቡትም።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኤርትራ ሳዋ ውስጥ የሶማሌ ጦር አስልጥነው ከላኩና ግብጽ ከፍተኛ መተን ያለው መሳሪያ ወደ ሃርጌሳ ካራገፈች በሁዋላ የአልሸባብ ማንሰራራት በቀጣናው ትልቅ ጥያቄ መሆኑ መገለጹ አይዘነጋም። ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት “ወደ ሶማሊያ የሚጋዘው መሳሪያ የሽብር እንቅስቃሴውን እንዳያስፋፋው ስጋት አለን” ማለታቸው አይዘነጋም።
ሁለቱ አገራት ቀይ ባህርን አስመልክቶ የሰላም ቀጠና እንዲሆን ሲስማሙ በትክክል የያዙት አቋም ለጊዜው ግልጽ አልሆነም። ግልጽ ባይሆንም ሻዕቢያ ኢትዮጵያን ለማተራመስ አበክሮ እየሰራ መሆኑ፣ ቀደም ሲል ጀመሮ ከአልሸባብ፣ አሁን ደግሞ ከየመን ቱሲዎች ጋር የተገናኘ መረጃ ስለወጣበት ስምምነቱ 33 ዓመት ኤርትራን ነክሶ የይዛወን አምባገነን መንግስ መንቀልን ሊያካትት እንደሚችል አስተያየት እየተሰጠ ነው። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቀይ ባህር ላይ ለኢራን የጦር መሰረት መስጠታቸው የሚታወስ ነው።

