የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ከሻዕቢያ ጋር በመሆን እንዳዘጋጀው የተነገረለት የአየር ላይ ትዕይንት በመሳተፋቸው ከፓርቲያቸው አመራርነት ታገዱ የተባሉት ዶ/ር ራሔል ባፌ እግዱ ህገወጥና የተጭበረበረ መሆኑን አስታወቁ። መግለጫው የተሰራጨው ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት በታገዱ ሰዎች ሐሰተኛ ማህተምና ቲተር የተዘጋጀ መሆኑንም አመልክልተዋል።
ዶ/ር ራሔል ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ነበር በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ አውዶች ከሚመሩት ከኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲን ሊቀመንበርነት መነሳታቸውን የሚያስታውቅ መግለጫ የተሰራጨው። መግለጫውን ዶከተሯ ከፓርቲያቸው ፈቃድ ውጪ አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ ጅዋር መሐመድና ቴዎድሮስ የሚባለው የርዕዮት ሚዲያ ባለቤት በጋር ከሻዕቢያና ትህነግ አንድ ክንፍ ጋር በመሂን ባዘጋጁት የአየር ላይ ትዕይንት ላይ ከፓርቴው እውቅና ውጭ መሳተፋቸውን ተከትሎ ነበር።
ይህ ጦርነት እንዲቆም፣ ሰላም እንዲመጣና አገዛዝ እንዲቆም በሚመጠይቀው የተጠቀሱት ክፍሎች ያቀነባበሩ የአየር ላይ ትዕይንት “አቶ ስብሃት ነጋ ሻኧቢያን በመወከል ተጋብዘዋል፣ የአማራ ሕዝብን የሸጡት አቶ አንዳርጋቸው አሉበት፣ አማራ ታሪካዊ የኦሮሞ ጠላት ነው ባማለትና በአማራ ክልል ውስጥ የተለያዩ ቤረሰቦችን በማደረአጀትና በሚዲያ የትርምስ አጀንዳ በመስጠት ክልሉን ለመበጣጠስ ሰርቷል የተባለው ጃዋር መሪ ሆኖበታል፣ ተጋባዦች በሚስጢር ተመልመለው ተሸዋደናል ” ወዘተ የሚሉ ወገኖች ወዲያው የተነሱበት ይህ የአየር ላይ ትዕይንት ቀጣይ ዕቅድ እንዳለው ጃዋር መሐመድ በማህበራዊ ገጹ አስታውቋል።
ሶዴፓን በምክትል ሊቀመንበርነት የሚመሩት ራሔል ባፌ በዚሁ ከላይ በተጠቀሱት አዛጋጆች የተደረገውን ውይይት አዲስ አበባ ሆነው በመከታተላቸው ሳቢያ መንግስት እንዳሰራቸው፣ ከፓርቲያቸው እንዲባረሩ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዝብይን እየጠቀሱ በርካታ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች፣ ደጋፊዎች፣ አክቲቪስቶችና የሻዕቢያ ደጋፊዎች በቅብብል ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ነበር። በተለይም የሻዕቢያ ደጋፊዎች ኢሳያስ አፉወርቂ ያደቀቋትን፣ በአምባገንነት የደቆሷትን አገራቸውን ትትተው እንስቷ ባያዙት አቋም አፈና እንደተደረገባቸው ደጋግመው ሲያስታውቁ በረካቶችን አስገርሞ ነበር።
ይህ ሁሉ ከሆነ በሁዋላ ነበር ” የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ምክትል ሊቀመንበሯን ከኃላፊነት አገደ ” በሚል የተሰራጨው መግለጫ ሃሰተኛ መሆኑን ራሔል ባፌ (ዶ/ር) ያመልከቱት። እሳቸው ይህን ቢሉም ቀደም ሲል የተሳሳተ መረጃ ሲያቀርቡ የነበሩት ሁሉም ማለት እስከሚቻል ማስተባበያ፣ ማስተካከያ ወይም ይቅርታ አልጠየቁም።
” አሁን የሶዴፓ ምክትል ሊቀመንበር ነኝ፣ ሙሉ የሊቀመንበርነትን ስልጣን ይዤ ነው የምሰራው፡፡ በጠቅላላ ጉባኤያችን ሊቀመንበር እስክንመርጥ ድረስ ማለት ነው፡፡ የመተዳደሪያ ደንባችንም የሚለው ይህንን ነው፣ የማዕከላዊ ኮሚቴውም የሰጠኝ ስልጣን ይህ ነው” ሲሉ ለቲክቫህ ዝርዝር መረጃ የሰጡት ሊቀመንበሯ ሌሎችንም ጉዳዮች አካተዋል። ከስር ያንብቡ።
የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ባለፈው መስከረም ወር ላይ ከዚህ አለም መለየታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ/ሶዴፓ የስራ አስፈፃሚ አባላት መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡
ይኸው አለመግባባት የሊቀመንበራችንን ህልፈት ተከትሎ፣ ባለፈው ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሔደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዳይካሔድ፣ አራት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አሉታዊ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ ምርጫ ቦርድንም ስብሰባውን እንዲያግድ በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
ለምርጫ ቦርድ ባስገቡት ደብዳቤ ላይ፣ ሌሎች ሁለት አባላትም አብረዋቸው እንደሆኑ በማስመሰል በአጠቃላይ ስድስት አባላት ሆነው የጥር 4ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ የስብሰባ ቀን እንዲራዘም መጠየቃቸውን በሐሰት ገልፀዋል ሰዎቹ፡፡
ሆኖም፣ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን በማየትና ለእኛም በማሳወቅ፣ 31 አባላት የሚሳተፉበትን የማዕከላዊ ኮሚቴውን ስብሰባ መከልከል እንደማይችል ገልፆላቸዋል፡፡ ለምርጫ ቦርድ ባስገቡት ደብዳቤ ላይ የሁለት ሰዎችን ስም በሐሰት በማስገባትና ፊርማቸውንም አስመስለው በመፈረም ለፈጠሩት ችግርም ለፖሊስ አመልክተን ክትትል ሲደረግባቸው ነበር፡፡
በዚህ አመት ባለፈው ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሔደ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ፣ አራቱ ሰዎች በፈጠሩት ችግር ምክንያት ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል፡፡
31 አባላት ያሉት ማዕከላዊ ኮሚቴው፣ ከ 10 ስራ አስፈፃሚ አባላት 4ቱን በማገድ፣ የፓርቲው ስራ በ6ቱ አባላት ብቻ እንዲከናወን፣ እንዲሁም ጉዳያቸው በሚቀጥለው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጠው ወስኗል፡፡
የሚቀጥለውን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ለመጥራት በዝግጅት ላይ እያለን ነው አሁን ሐሰተኛ ማህተምና ቲተር በማስቀረፅ፣ የትናንትናውን ሐሰተኛ መግለጫ የለቀቁት፡፡
በመግለጫው ላይ እንደተጠቀሰው፣ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበሯን አግዷል ይላል፡፡ ስራ አስፈፃሚ እንዲህ ዓይነት ስልጣን አልተሰጠውም በመተዳደሪያ ደንባችን፡፡
ሐላፊዎችን መሾምና መሻር የሚችለው በትንሹ 500 አባላት የሚሳተፉበት ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ በመሐል ግን 31 አባላት ያሉት ማዕከላዊ ኮሚቴው ሐላፊዎችን የማገድ ስልጣን በውክልና ተሰጥቶታል፡፡ ግን የመጨረሻውን ውሳኔ በጠቅላላ ጉባኤ ነው አቅርቦ የሚያፀድቀው፡፡
ይህን ባደረጉት አባላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በነገው ዕለት ለፖሊስ እናመለክታለን፡፡ በቅርቡ አስቸኳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጠርተን በጎደሉት የስራ አስፈፃሚ አባላት ምትክ እናሟላለን፣ በታገዱት ሰዎች ጉዳይ ላይም የመጨረሻ ውሳኔ እንሰጣለን፡፡ “

