Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  POLITICS  የእስራኤል ኢራን ጦርነት ድንበሩን እያሰፋ፣ አሰላለፉ እየለየ ነው፤
POLITICS

የእስራኤል ኢራን ጦርነት ድንበሩን እያሰፋ፣ አሰላለፉ እየለየ ነው፤

Ethioreview newsEthioreview news—June 23, 20250
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኢራን አሜሪካን ላይ የአጸፋ እርምጃ ከሞከረች ስህተቱ ከቀደመው ሁሉ የከፋ ስህተት ይሆናል ተባለ፤ ምላሹ የከፋ ነው  ብትልም ዛቻው አልቆመመ። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ ጥቃት “የማያባራ መዘዝ” ያስከተላል” ነው ያሉት። ይሆናል አይሆንም የሚታይ ቢሆንም እስራኤልን ግን እየተመታች ነው። እሷም የተመረጡ ስትራቴጂክ ስፍራዎችን እያወደመች ነው። 

ይህ አሰላለፍን እያጸዳ ያለው ጦርነት አገራት አቋማቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ይፋ እየሆነ ነው። ዩናይትድ ኪንግደም ከአሜሪካ ጎን መቆሟን በግልጽ አሳይታለች፡፡ ለኢራን ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈች። የዩናይትድ ኪንግዶም አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ “ኢራን በአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጥቃት ከፈጸመች፣ ጥቃቱ በኔቶ (NATO) ሀገራት ላይ እንደተፈጸመ ጥቃት እንቆጥረዋለን” ብለዋል። ጀርመንና ፈረንሳይም ተመሳሳይ አቋም አላቸው። 

የዩናይትድ ኪንግዶም ባለስልጣን ንግግር ኢራን በአሜሪካ ላይ የምትወስደው ማንኛውም እርምጃ መላውን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ወደ ግጭቱ ሊያስገባ እንደሚችል የሚያስጠነቅቅ ሲሆን፣ የውጥረቱን መጠን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ መሆኑ ተዘግቧል። 

ይህ የተባለው አሜሪካ  የኢራንን የኒውክሌር ማብላያዎችን  የመጨረሻ ባለችው ቴክሎጂና ቦምቦች ተጠቅማ  የተሳካ ያለችውን ጥቃት መፈፀሟን ማስታወቋን ተከትሎ ኢራን የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ በማስታወቋ ነው። 

More stories

ቴዲ አፍሮ ለጥምቀት የተዘቀዘቀ መስቀል ያለበት ጥበብ መልበሱ እያነጋገረ ነው

January 21, 2024

ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!

April 28, 2024

ስንዴ በገፍ – ለምን ገበያው አይረጋጋም?

February 14, 2024

ኢዜማ እስር ላይ ያሉት መሪው ዶክተር ጫኔ የድርጅቱን መርህ መጣሳቸውን በይፋ አስታወቀ

October 2, 2023

አሜሪካ እጅግ ውጤታማ ያለችውን ድብደባ የኢራን አልካደችም። ነገር ግን ይህ ነው ሚባል ጉዳት  እንዳልደረሰና  ጥቃቱ ያረፈው የኒውክሌር ማብላያ ተቋሞቹ  ህንፃዎች ላይ እንጂ  አብዛኛውን የኒውክሌር ማብላያ ግብዓትና መሳሪያዎች ራቅ ወዳሉ አከባቢዎቸ  ከተዘዋውሩ መሰነባበቱን የሚጠቁም መረጃ  ተሰምቷል። ይህ መረጃ ግን ብዙም የሚታመን አልሆነም። እንደውም የልጆች ቀልድ ዓይነት እንደሆነ የሚገልጹም አሉ። እንደዚህ የሚሉት አካላት የሚያስጨንቃቸው ኢራን በዕልህ ልቅ ወደ ሆነ ጥቃት እንዳታመራ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ አሜሪካ ውሳኔዋ ይከፋል። 

ጥቃቱ ምን ይመስል ነበር?

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ንግግር ሲያደርጉ ዓለም ትንፋሹን ውጦ ያዳምጥ ነበር። ቃላቶቻቸው እንደተወነጨፈ ጥይት ቀጥተኞች ነበሩ። “ዛሬ ማታ፣ ለአሜሪካ ህዝብ እና ለመላው ዓለም አስታውቃለሁ” አሉ ፕሬዝዳንቱ በልበ ሙሉነት። “የአሜሪካ ጦር በኢራን በሚገኙ ሦስት የኑክሌር ተቋማት ላይ እጅግ በጣም የተሳካ ጥቃት ፈጽሟል። ፎርዶው፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። ፎርዶው ከጥቅም ውጪ ሆኗል!”

ይህ መግለጫ፣ ለዓመታት ሲጠበቅ የነበረው ነገር ግን ማንም እንዲሆን ያልደፈረው ቀይ መስመር መሻገሩን የሚያበስር ነበር። የአሜሪካ B-2 ስውር ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች፣ በተራራ ውስጥ በጥልቀት የተገነባውን የፎርዶው የኑክሌር ማበልጸጊያ ምሽግ ለመስበር ተብለው የተሰሩትን “ባንከር በስተር” የተባሉ ከባድ ቦምቦችን አዝንበውበታል።

የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተከትሎ ይፋ የሆኑ የሳተላይት ምስሎች፣ የጥቃቱን አስፈሪነትና የኢራንን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቷል። ጥቃቱ ከመፈጸሙ ከቀናት በፊት፣ በፎርዶው መግቢያ ዋሻዎች ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነበር። የጭነት መኪኖችና ከባድ ማሽነሪዎች፣ የአየር ጥቃትን ለመቋቋም በማሰብ ይመስላል፣ ዋሻዎቹን በአፈር ሲሞሉ ታይተዋል።

ነገር ግን ከጥቃቱ በኋላ የተነሱት ምስሎች፣ የኢራን ጥረት እንዳልተሳካ አሳይተዋል። ተራራው ራሱ የቆሰለ ይመስላል፤ መሬቱ ወደ ውስጥ ተደርምሷል፤ ምሽጉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የሚያሳዩ ምልክቶች በግልጽ ይታያሉ። የቴክኖሎጂ ጦርነት በሰማይ ላይ ሳይሆን፣ በመሬት ውስጥ በሚስጥር በተገነባው የኢራን የኑክሌር ህልም ላይ የተፈጸመ ይመስላል።

የኢራን ምላሽ ምን ሆነ?

የሌሊቱ ጸጥታ በድንገት በሚያስገመግሙ የፍንዳታ ድምጾች እና በከተማዋ ላይ በሚያስተጋቡ የአደጋ ጊዜ ሳይረኖች ተሰማረ። ከኢራን የተተኮሱ ከ20 በላይ ኃይለኛ ሚሳኤሎች የእስራኤልን ሰማይ ሰንጥቀው በቴል አቪቭ እና ሃይፋ ከተሞች ላይ ሲያርፉ፣ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የፍርሃትና የትርምስ ማዕበል ተቀሰቀሰ። የመኖሪያ ህንጻዎች ወደ ፍርስራሽነት ተቀየሩ፤ የቆሙ መኪኖች ተጨማደዱ፤ የተጎዱ ሰዎችን ለማውጣት የነፍስ አድን ሰራተኞች በተሰባበሩ ኮንክሪቶችና ብረቶች መካከል ሲሯሯጡ ይታያል። ጦርነቱ ከስውር ጥላ ወደ ግልጽ እውነታ የተቀየረበት ምሽት ነበር።

ይህ አስደንጋጭ የበቀል እርምጃ፣ ከመላው ዓለም ሰዓታት በፊት የተነገረውን አንድ ዜና ተከትሎ የመጣ ነበር።ከጥቂት ሰዓታት በፊት፣

የኢራን ምላሽ ፈጣንና ግልጽ ነበር። በእስራኤል ከተሞች ላይ የሚሳኤል ውርጅብኝ እየዘነበ ባለበት ወቅት፣ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቱርክ ለተሰበሰቡ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጡ። ፊታቸው በቁጣ ተሞልቶ ነበር። “የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሰላማዊ የኑክሌር ተቋሞቻችንን በመደብደብ የተመድን ቻርተር፣ ዓለም አቀፍ ህግን እና የኑክሌር ስምምነትን ክፉኛ ጥሳለች” ሲሉ ከሰሱ።

ቃላቶቻቸው ከክስነት ወደ ማስጠንቀቂያ ተሸጋገሩ። “በተመድ ቻርተር መሰረት ራሳችንን የመከላከል ህጋዊ መብታችንን ተጠቅመን፣ የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ ጥቅም እና ህዝብ ለመጠበቅ ማንኛውንም አማራጭ እንወስዳለን።” ሲሉ ነበር ሚኒስትሩ ንግግራቸውን የደመደሙት፣ “በበላይ መሪያችን ላይ የሚቃጣ ማንኛውም እርምጃ ሁሉንም ቀይ መስመሮች መሻገር ነው፤ ምላሻችንም ገደብ የለሽ ይሆናል” በሚል አስፈሪ ዛቻ ነበር። 

ይህን ቢሉም አሁን እየወጡ ያሉት መረጃዎች የኢራን መሪ ከስልጣን ሊነሱ እንደሚችሉ ነው። በሌላም በኩል ለማንኛውም በሚል ራሳቸው ተጠባባቂ እሳቸውን የሚተኩ መሪዎች መሰየማቸው ተሰምቷል። 

ዛቻው አለቀረም። እስራኤል ከኢራን በተተኮሱ ሚሳይሎች ህንጻዎቿ እየፈረሱ ነው። ውድመቱ ከቀድሞዎቹ የባሰና ከፍተኛ ጉዳይ ያደረሱ መሆናቸው ከሚወጡ የቪዲዮና የምስል መረጃዎች ማረጋገጥ ተችሏል። 

እስራኤልም በበኩሏ በተመረጡ ስፋራዎች ላይ ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን ስድስት የአየር ማረፊያዎችንና አስራ አምስት አውሮፕላኖች ማውደሟን አስታውቃለች።  ክድብደባው ጀርባ የሹም ሽር ወሬም እየወጣ ነው። 

ለክፉውም መዘጋጀት ይበጃል ያሉት የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ኻምኒ ሶስት ተተኪዎችን መርጡ።

ጦርነቱ ተባብሶ በቀጠለበት እና  በቀጣይም በጦርነት ውስጥ የሚሆነው ለማይታወቅበት ኢራን  ከእስራኤል እያደረገች ባለው ፍልሚያ እና አሜሪካ ወደ ጦርነቱ ለመግባት ጫፍ ላይ ባለችበት ቅፅበት የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ  ኻምኒ ለክፉው ራሳቸውን አዘጋጅተዋል ተብሏል።

ኒውዮርክ ታይምስ  የኢራንን ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ኻሚኒ እሳቸው ሲሞቱ በእጩነት ለመሾም ሶስት ከፍተኛ የሀይማኖት አባቶችን ቢያቀርቡም ማንነታቸው አልተገለጸም ሲል ሚድል ኢስት የአረበኛው ክፍል ዘግቧል።

ከእስራኤል ጋር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ፈጣን እና ሥርዓት ያለው የስልጣን ሽግግር ማረጋገጥ ይፈልጋሉም ተብሏል። የኢራን የስለላ ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሞባይል ስልኮችን ወይም ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ዘዴዎችን መጠቀም እንዲያቆሙ እና ከመሬት በታች ባሉ ጋሻዎች ውስጥ እንዲቆዩ መጠየቁን ገልጿል ሲል ሚድል ኢስት ዘግቧል።

በደቡባዊ እስራኤል  በከባድ ሚሳኤሎች  ዋና ዋና የእስራኤል የስለላ ተቋማት፣ የሞሳድ መስሪያ ቤት፣ ለወታደራዊ ጥቅም የሚውሉ የቴክኖሎጂ ማእከሎች እና በቴል አቪቭ፣ በሀይፋና ቤርሸባ ያሉ ከተሞች ከተመቱ በኋላ  አያቶላህ አሊ ኻሚኔ  በስልጣን ላይ እንዲቆዩ “ሊፈቀድለት አይችልም” ስትል እስራኤል ሐሙስ  ተናግራ ነበር ብሏል ዘገባው።

እስራኤል እንደ ኢራን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ያሉ የኒውክሌር ወይም የባላስቲክ ሚሳኤል ስፍራዎች ላይ ኢላማ መደረጉን ተከትሎ የእስራኤል ትክክለኛ አላማ የኢራንን የኒውክሌር እና የባሊስቲክ አቅም ከማዳከም ባለፈ የጠቅላዩ መሪ  አሊ ኻሚኒን ከስልጣን መውረድን ትፈልጋለች ተብሏል።

የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ

ሌላው አዲሱ ትኩሳት የኢራን ፓርላማ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ እንዲዘጋ የቀረበውን ውሳኔ ማጽደቁ ነው። ይህ ርምጃ በኣለም የነዳጅ ስርጭት ላይ ከፈተኛ ጫና ስላለው ቻይና እንድታረግበው ተጠይቃለች።

የሆርሙዝ ወንዝ የዓለም ኢነርጂ የደም ቧንቧ የሚባልለት ሲሆን፤ በግምት 20 – 30 በመቶ  የሚሆነው የዓለማችን የነዳጅ ዘይት በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ያልፋል። የዚህ ሰርጥ መዘጋት ዓለም አቀፍ የኢነርጂ ደህንነት ላይ ስጋትን የሚደቅን ተደርጎ ይወሰዳል። ሰርጡ ከተዘጋ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ እና የአቅርቦት መቆራረጥ ያስከትላል ተብሏል።

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

“ሰው ከመሬት በላይ ከፍ ብሎ መታየት አለበት፤ ትህነኛ የትግራይ ሕዝብ አንድ አይደሉም “አቶ ጌታቸው
ኢትዮጵያ ድፍድፍ ነዳጅ የማምረት ሙከራ ጀመረች፤ በመጪው መስከረም ጋዝ ወደ ውጭ ይላካል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
POLITICS

ኢራን እኛ ላይ ምን ልታደርግ ትችላለች?

March 28, 20260
POLITICS

አስቸኳይ የአርበኛነት ጥሪ ለኢትዮጵያን

March 4, 20260
POLITICS

ትራምፕ ኢራንን እንደሚወጉ ፍንጭ ሰጡ

January 28, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news