Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በትግራይ ሕግ ፈርሷል፤ የፌደራሉ ሹመኛ ከታገደው ኃይልና ሻዕቢያ ጎን ሆነው ማስጠንቀቂያ ሰጡ
News

በትግራይ ሕግ ፈርሷል፤ የፌደራሉ ሹመኛ ከታገደው ኃይልና ሻዕቢያ ጎን ሆነው ማስጠንቀቂያ ሰጡ

Ethioreview newsEthioreview news—July 16, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን እንዲወርዱ የተደረጉትን አቶ ጌታቸው ረዳን ሲተኩ በገቡት ቃለ መሰረት የትግራይ ሁኔታ ሊቀየር እንደሚችል ግምት ነበር። ይህ የአብዛኞች ግምት መነሻው ታደሰ ወረደ ቀድሞውንም ከአቶ ጌታቸው ጋር የጸጥታውን ኃላፊነት ወስደው ይሰሩ የነበሩት ይይስሙላ እንደሆነ በርካታ መረጃና ማስረጃዎች የሚጣቀሱበት ነው።

የእሳቸው ሹመት ይፋ እንደሆነ ‹‹ከጦርነቱ በኋላ እኛ ከጫካ ወደ ከተማ ስንገባ እነሱ ወደ ዝርፊያ ገቡ›› የሚሉና በጓሮ ከሻዕቢያ ጋር የተጀመረውን ሽርክናና የወርቅ ዝርፊያ የተቃወሙ የጦር አመራሮች ድምጽ ተሰማ።

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ ተኩስ ቢቆምም ትግራይ ውስጥ የተጀመረው አዲስ ፖለቲካ ሻዕቢያን በብርሃን ፍጥነት ከጠላትነት በተቃራኒ ሙሉ በሙሉ ወዳጅ አድርገ። “ከሻዕቢያ ጋር ፅምዶ (ቅንጅት) እየፈጠራችሁ ስለሆነ እናጠፋችኋለን ስለተባልን ነው ለጦርነት የምንዘጋጀው” ሲሉ በእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን በኩል ያለውን የትግራይ ታጣቂ ኃይል ከሚመሩት መካከል አንዱ የሆኑት ጄነራል ኃይለ ሥላሴ ግርማይ (ወዲ እምበይተይ) ሰሞኑን ኮማንዶ ሲያስመርቁ ተናገሩ። ይህ ንግግራቸው የሻዕቢያንና የወያኔን ዳግም ፍቅር አደባባይ ያወጀ ሌላኛው አዋጅ ሆነ።

“ይህ አዲስ ፍቅር በቅጽበት ሻዕቢያን ጽድቅ አደረገ። በጅምላ የጨፈጨፋቸውን የትግራይ ልጆች አስረሳ። በደቦ የተደፈሩትን፣ በቫይረስ እንዲበከሉ የተደረጉትን፣ ማህጸናቸው ውስጥ ባዕድ ነገሮች የተጨመረባቸውን እናቶችና እህቶች ስቃይ ፋቀ። በቅርሱ ሴንቸሪና ዘ ጋርዲያን ያወጡትን ለማንበበና ለመመልከት የሚከብድ ሪፖርት ሁሉ አስጣለ። ከፋብሪካ እስከ ቆርቆሮና በር ነቀላ፣ ከቤት ቂሳቁስ እስከ ሽሮና በርበሬ የዘረፈውን ክፉ ኃይል ‘ ጄኖሳይድ አልፈጸምክን፣ ሴቶችን አልደፈርክም’ በሚል ምህላ ትግራይ ምድር ላይ ዳግም እንዲፏልል አደረጉት” በሚል ሃዘናቸውን ገልጸው አቶ ግሩም ተስፋዬ ሃዘናቸውን ገልጸዋል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ጄነራል ኃይለ ሥላሴ ግን “… እኛ ከሌሎች ጋር አጋርነትን [ኤርትራና ግብጽና ሱዳንን ማለታቸው ነው] በዓይነት ስንጨምር ጠላት (አራት ኪሎ ያለው) ወዳጆቹን አጥቷል” በማለት ሕዝብ እየሰማ በጭብጨባ ታጅበው በይፋ እውነቱን አበሰሩ። ሌሎች በጅምላ ሲያወሩ እሳቸው የጉዳዩን እምባርት አስታወቁ።

ይህ በሆነ በቀናት ልዩነት የቀይ ባህር አፋሮች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በኤርትራ በሻዕቢያ የግፍ ቀበር ስር ያሉትን አፋሮች ነጻ ለማውጣት የትጥቅ ትግሉን እንደሚያጠናክር አስታወቀ። በሰመራ በሺህ የሚቆጠሩ አባላቶቹ ጋር ስብሰባውን ያደረገው የአፋር ነጻ አውጪ ፣ በመግለጫው ይፋ እንዳደርገው ሻዕቢያን ከሚቃወሙ ጋር ህብረት አድርጓል። በስብሰባውም ጋብዟቸዋል።

ከትናንት በስቲያ ” በትግራይ ላይ የሚታሰብና የሚደረግ የውክልና ግጭት (Proxy Conflict) ተቀባይነት የለውም ” ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ። “የውክልና ግጭት” ሲሉ ስም የሰጡት በአፋር ክልል ሰፍሯል ለተባለው የትግራይ ሰላማዊ ጦር ሲሆን፣ ጦሩ ሰሞኑን “ያለሁት ትግራይ ነጻ መሬት እንጂ አፋር አይደለም” ማለቱ አይዘነጋም።

እርስ በርሱ የሚጣረስ መግለጫና ሴራ እየናጣት ያለችው ትግራይ ለህጋዊውም፣ ለህገወጡም ጉዳይ ሕገመንግስት ይጠቀስባታል። ሕገመንግስት ጠቅሶ መጠየቅ፣ ቅሬታን ማቅረብ፣ የመብት ይከበር ግዴታን ማንሳት እንጂ ግዴታ የሚባል ነገር በትግራይ ፖለቲከኞች ዘንዳ የሚታሰብ እንዳልሆነ ታዛቢዎች መናገር ከጀመሩ ቆይቷል። ሻዕቢያ የጨፈጨፋቸውን ቀብረው ሳይጨርሱ በሻዕቢያ ፍቅር ተነድፈው ሕገመንግስቱን በመናድ በገሃድ ጥፋት እየሰሩ መልሰው “የሕገመንግስት ያለህ ሲሉ ያስደነግጣል። እንዴትስ ከነደነዚህ ዓይነት ኃይሎች ጋር በአመክንዮ መነጋገርና በግባባት ይቻላል?” በሚል እነዚሁ ታዛቢ ወገኖች ይናገራሉ። ሲያጠቃልሉም “በትግራይ ሕግ ፈሷል። መላ ካልተባለ አደጋ አለው፡፡ ጦርነት አያስፈልግም መመካከርና መፍትሄ መፈለጉ ከቀናዎች ይጠበቃል”

በመቐለ የሰማዕታት ሀውልት አዳራሽ በተካሄደው 36ኛው የሰማዕታት ቀን የማጠቃለያ ፕሮግራም ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ” ነፃ (ሓራ) መሬት ተብሎ ትግራይ ላይ ለሚቃጣ ማንኛውም ዓይነት ጥቃት ተጠያቂዎቹ የፌደራል እና የዓፋር ክልል መንግስታት ናቸው ” በማለት ታደሰ ወረደ ሲናገሩ ተሰምቷል።

“ይህን የሰሙና በማህበራዊ ገጾች ጥያቄ ያነሱ ጄነራሉ ሻዕቢያ ከድርጅታቸው ጋር ሕብረት መፍጠሩን ያውቃሉ፡፡ በአገሪቱ ሕግ መሰረት ይህ አይቻልም፡፡ ከፌደራል መንግስት አገልግሎትና በጀት እየተጠቀሙ፣ በፌደራል መንግስት ተሹመው፣ ለፌደራል መንግስት ተጠሪ ሆነው ሳለ ሻዕቢያንና ትህነግን ወግነው ወይም አባሪ ሆነው በዚህ መልኩ በግልጽ መናገራቸው ወንጀል ነው” ባይ ናቸው፡፡ እነዚሁ ወገኖች የፌደራል መንግስትን ከህግ አንጻር መረዳት ቢፈለግ እንኳን እነሱን መርዳት እንደማይቻል በርካታ መረጃዎችን እያጣቀሱ ያናገራሉ።

“በበፊቱ ጦርነት ወቅት እስከ ደብረሲና ሲዘልቁ እነሱ ትክክል ነበሩ። መንግስት ኃይሉን አሰባስቦ ሲመታቸው ጄኖሳይድ ይላሉ። እነሱ ሲገድሉ ጽድቅ፣ ለኤላው በጦርነት ራሱን ሲከላከልም ሆነ ሲያጠቃ ጄኖሳይደር ብለው ይከሳሉ” የሚሉ ወገኖች ” አራት ኪሎ ገብተን መንግስት ገልብጠን፣ እንደቀድሞው መከላከያን አፍርሰን … ስናደርግ ዝም በሉን ነው እያሉ ያሉት ወይስ ምንድን ነው? እንኳን ለመከራከር እንዴት እንደሚያስቡ ለመረዳት ያዳግታል” ሲሉ መሰላቸታቸውን የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም።

ቀደም ሲል በድርድር የሚያልቅ ጉዳይ እንደሆነ ገልጽው እዚህ ግባ የሚባል ኃይል እንዳልሆነ የጠቆሙትን የትግራይ ሰላም ኃይሎችን ጉልበት፣ ታደሰ ወረደ ከትናንት በስቲያ ባደረጉት ንግግር ደግሞ ” በዓፋር እንጂ በትግራይ ነፃ (ሓራ) መሬት ብሎ የለም ” ሲሉ አዲስ መረጃ ሰጥተዋል።

ራሳቸውን የትግራይ ሰላም ኃይሎች ብለው የሚጠሩትና አስር የሚጠጉ ጄነራሎች፣ እንዲሁም በርካታ ከፍተኛ መኮንኖችና 13 ክፈለጦር ያለው ኃይል ያደራጁት ወገኖች ” የምንገኘው በትግራይ ነጻ መሬት ውስጥ ነው” በሚል ካስታውቁ በሁዋላ፣ ትግራይን ወደ አልተገባ አቅጣጫ እየመራ ያለው ቡድን በሰላማዊ መንገድ ራሱን የማያስገዛ ከሆነ ከጌታው ጋር አንድ ላይ እናስወግደዋለን” ሲሉ ለቢቢሲ ትግርኛ መግልጻቸው ይታወሳል። ትግራይን እያስተዳደሩ ላሉት ሌ/ጄነራል ታደሰ በተደጋጋሚ መልዕክት መላካቸውንም አስታውቀዋል።

ለአፋር ሕዝብ ነጻነት ትግል ራሱን እያዘጋጀ ያለውን የአፋር ነጻ አውጪና የትግራይ ሰላም ኃይሎችን የውክልና ግጭት ለማድረግ እንደተዘጋጁ ጠቅሰው ማስጠንቀቂያ ያቀረቡት ታደሰ ወረደ፣ ” ነፃ (ሓራ) መሬት ተብሎ ትግራይ ላይ ለሚቃጣ ማንኛውም ዓይነት ጥቃት ተጠያቂዎቹ የፌደራል እና የዓፋር ክልል መንግስታት ናቸው ” ብለዋል።

ስምረት ፓርቲ በበኩሉ “ከአሁን በኋላ በትግራይ ላይ የሚፈፀሙ ጥፋቶች ብቸኛው ተጠያቂ ከዓለም አቀፍና አገራዊ ህጎች የተቃረነው ወመኔው ኋላ ቀር ቡድን እና መሰሎቹ መሆናቸው የኢትዮጵያ መንግስት መገንዘብ አለበት ” ሲል ይህ ቡድን እርምጃ እንዲወሰድበት ጠይቋል።

” የሃይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ወጣቶች በአገር ውስጥና በመላ ዓለም የሚገኙ ትግሬዎች ቡድኑ በስልጣን የሚቆይባቸው እያንዳንዱ ቀናት በህዝብ ላይ አስከፊ መከራና ስቃይ የሚያስከትሉ መሆናቸው በመረዳት ትግላችሁ አጠናክሩ ” የሚል ጥሪም አቅርቧል።

” ሌት ተቀን የጦርነት ነጋሪት ከሚጎስመው ኋላ ቀር ቡድን ራሳችሁን በማራቅ ከሰላም ፈላጊ ህዝብ ጎን ተሰለፉ ” ሲል አቶ ጌታቸው የሚመሩት ስምረት ፓርቲ ደጋግሞ አሳስቧል።

ጥሪውም ይሁን የሕዝብ ፍላጎት ከፊት ለፊት እንደሚታየው ሰላም ቢሆንም በትግራይ አሁን ላይ የኮማንዶ ምርቃት የሚያሳዩ መረጃዎች በስፋት በምስል እየወጡ ነው።

“ጦርነት ባህልህ ነው” እየተባለ በመጀመሪያው ጦርነት ሲደረግ እንደነበረው፣ እናቶች ልጆቻቸውን እየመረቁ የሚሸልሉበት ዓይነት የስታዲየም ድግስ ባይሆንም ኮማንዶዎች ሲመረቁ የሚያሳዩ ቪዲዮ ማየት የተለመደ ሆኗል። ኤርትራም በተመሳሳይ እያስመረቀች ነው።

” ነፃ (ሓራ) መሬት ብሎ በትግራይ የለም ” በማለት ሌተናል ጄነራል ታደሰ በንግግራቸው አንስተው ” በዓፋር ክልል ያለው የትግራይ ታጣቂ በፌደራልና በዓፋር ክልል መንግስታት እውቅና እገዛ የሚንቀሳቀስ ነው ” ሲሉ የሾማቸውን መንግስት ዘልፈዋል።

” በዓፋር በኩል ያሉ ታጣቂዎች ትግራይ ላይ የሚቃጡት ማንኛውም ዓይነት ጫናና ግጭት ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፌደራልና የዓፋር መንግስታት ፍላጎት እንጂ የነሱ አድርጎ አይመለከተውም ”  ያሉት ሌተናል ጄነራል ታደሰ፣ ” እዚያ ካሉት ታጣቂዎች ያለው ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ከውይይት ውጪ ሊፈታ አይችልም ” ብለዋል። አክለውም ” የፌደራልና የዓፋር መንግስታት ጉዳዩ ሰላማዊ ዕልባት እንዲኖረው ማገዝ አለባቸው ” የሚል ጥሪም አቅርበዋል። እሳቸው በሚመሩት ክልል የውጭ አገር ሰራዊት እንዳሻው ስለመቦረቁ ኝ ያነሱት አንዳችም የሕግ ጥያቄም አልተሰማም።

” የትግራይ ቁጥር አንድ ጥያቄ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዲተገበር ነው ፤ ከዚህ ውጪ የውክልና ግጭት (proxy Conflict) እንዲካሄድ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት የለውም የሚሳካም አይደለም ” በሚል ንግግራቸው የደመደሙት ሌተናል ጄነራል ታደሰ፣ የሾማቸው የፌደራሉ መንግስት ምን ማልሽ እንደሚሰጣቸው ለጊዜው አልታወቀም።

በትግራይ ያለው ሕገወጥ እንቅስቃሴ ለመግታትና መስመር ለማስያዝ የሚያስችል ስራ እየሰራ እንደሆነ የሚገልጸው የትግራይ ሰላም ኃይሎች፣ በትግራይ በጉልበት መንግስት ገልብጦ ያለውን የእነ ደብረጽዮንን ቡድን ለማስወገድ ከጫፍ መድረሱን ማስታወቁ አይዘነጋም።

በሶስት ዙር በተካሄደው ጦርነት፣ መንግስት ነዳጅ፣ በጀት፣ ተሽከርካሪ፣ ቀለብ፣ መድሃኒት ወዘተ እንዲያቀረበ ይዋጋ እንደነበር የሚታወስ ነው።
በትግራይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ሕዝቡ ጦርነትን አብዝቶ እንደሚቃወም መረጃዎች ያሳያሉ።

የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀዬያቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተመልሰው መግባባት ከተፈጠረ በሁዋላ ሕዝቡ ራሱ መክሮ በሚያቀርበው አሳብ መሰረት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው የሚለውን የገለልተኛ ወገኖች ምክረ አሳብ በርካቶች በበጎ ቢያዩትም ከትግራይ ኃይሎች አንጻር “ቀድሞ ትህነግ ይዳን” በሚል ተቀባይነት ሊያገኝ አለመቻሉ በተደጋጋሚ የሚሰማ መሆኑ ያታወሳል።


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ
 የአይ ኤስ የሶማሊያ ክንፍ ፑንትላንድ ያሰለጠናቸው 82 የአይ ኤስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2