የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ወንጀል ምርመራ በማጣራት ለፌደራል ዐቃቤ ህግ በማስተላለፍ ክስ እንዲመሰረት አድርጓል።
ተከሳሾቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከሌሎች የግል ባንኮች የሚደውሉ በማስመሰል እንዲሁም የኮምፒውተር ስርዓትን በመጠቀም አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት ወንጀሉን እንደፈጸሙ ፖሊስ ገልጿል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያብራራው፣ ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመሰወር፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን እና መታወቂያዎችን በማዘጋጀት እና በመጠቀም የተበዳዮችን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በምርመራ ተረጋግጧል።
በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቀረበው ክስ በዋናነት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ እና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008ን እንዲሁም የብሄራዊ የክፍያ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003ን የተላለፉ መሆናቸው ታውቋል።
ለወንጀል ድርጊቱ ማስፈጸሚያነት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የባንክ አካውንቶች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ሲም ካርዶች እና ኮምፒውተሮች የተያዙ ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራት ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።
በክሱ ከተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች መካከል፡-
1,ራያን አዳም መሀመድ፡
2,አስራት አስፋቸው የቦ/ሀብታሙ ገብሬ
3,ገለታ ገነም ገበሬ/አማን አበበ አምቦ፣ አቤል አለማየሁ፣ ታምሩ ዘውዴ/፡
4,አክሊሉ አየለ አላቶ/አገኘው አየለ አደፎ/፡
5,ጌታቸው የኔው በሬ/ ታምራት ታከለ ገብሬ/
6,አሻግሬ ኬሮ አላቶ፡
7,ዋለልኝ ማሰሬ አበጀ፡
8,ቅዱስ ያሬድ ግርማዬ
9,አሸናፊ ሰለሞን ቸሩ፡
10,እንየው ተሰራ ዳኜው፡
11,ቃለአብ ታየ እታለማሁ
12,ዳንኤል ከበደ አያና፡
13,ድሪባ በቀለ ለማ
14,ጋሻው ታገለ ቢሻው፡
15,ተመስገን ተሰማ ፋንታሁን
16,አቤል ወንዱ ተከል፡
17,ረድኤት ደረጀ ፀጋ፡
18,አማኑ አንተነህ ሙላት/ ታዲዎስ መንጌሻ መኩሪያ/
19, አይናለም አንሙት ታደሰ፡
20, ቤቲ አደመ አንጋሞ/አዲስዓለም አደመ አንጋሞ/፡
21,ብርቱካን ሀይሌ ገ/ሚካኤል/አስቴር አበበ ግበሬ፣ አበዛሽ አለማየሁ/፣
22,ከይረዲን ሁሴን ፎጌ/ከይረዲን ጀማል ሳላ/ ፣
23,ሙሉዓለም መከተ ተፈራ፣
24,ብሩክ ጌታቸው ይርዳው
25, ዳንኤል ተስፋዬ በቀለ፣
26,ሚኪያስ ሔኖክ ባይዶ፣
27,ታምሩ ገ/የሱስ የባ/ሳሙኤል ገሮ የባ፣ ዮሐንስ ገረው የባ/፣
28,ታምራት እሸቱ ሀይሌ፣
29, አሲያ ሁሴን መሀመድ/ኢሲያ ሁሴን አባዲኮ፣
30,ሳሙኤል ላጵሶ ዳለሎ ፣
ህብረተሰቡ ከማያውቋቸው እና አጠራጣሪ ከሆኑ የስልክ ጥሪዎችና መልዕክቶች ራሱን እንዲጠብቅ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
ፌደራል ፖሊስ የተከሳሾቹን ፎቶ እዚህ ላይ ይመልከቱ

