ልደቱ አያሌው ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር የሚያስተባብረው “አየር አንቀጥቅጥ” ትዕይንት ክፍል ሁለት የሻዕቢያ አጀንዳ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ እንደሚካሄድ ታወቀ። በቀጣይ የሚካሄደው ክፍል ሶስት “አየር አንቀጥቅጥ ትዕይንት” የሲቪክ ማህበራት ሲሆን የቀድሞ የቪኦኤ ኃላፊ አቶ ንጉሴ አክሊሉ በዋናነት ተጋባዥ ይሆናሉ።
በሰማይ ላይ ትዕይንቱ እንዲሳተፉ ተጋብዘው ” የሉአላዊነት” ጥያቄ በማንሳት ግብዣውን ያልተቀበሉ በሰጡት ጥቆማ መሰረት መድረኩ በቅርቡ “ሰማይ አንቀጥቅጥ” በሚል ስያሜ ተካሂዶ በቅብብሎሽ “የሻዕቢያ ተቀጣሪዎች” የሚባሉት እና የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን ደጋፊ ሚዲያዎች ያራገቡት የበይነ መረብ ትዕይንት ቀጣይ ነው።
የስማይ ላይ ሰለፉ የሻዕቢያና የበረከት ስምዖን ሤራ እንደሆነ የሚጠቁሙ ርዕዮት ዩቱብ ልዩ ገጸ ባህርይ ተዘጋጅቶለት ድራማውን ከልደቱ ጋር እንዲተውን ሲደረግ መስማማቱ ሻዕቢያንና የእነ ዶክተር ደብረጽዮንን ቡድን ለመስማት በሚከብድ ቃላቶችና ሃረጎች እየደጋገመ መሳደቡ ለዚሁ ኃላፊነቱ ማመቻቺያ እንደሆነ ጎልጉል ዘግቧል።
በስፋት የተቃውሞ ጽሁፍ በማዘጋጀት፣ በዩቲዩብ ቻናሎች በተደጋጋሚ በመቅረብ የሚታወቁ የሚሰባሰቡበት ይህ መድረክ ከሚታውቁት ውጪ አዳዲስ ሰዎች እንደማይጠበቁበት ዜናውን የሰጡን ነገረውናል።
” የአብይ ነገረኝ ንቅናቄን ተዋንያኖችን ሲያስተናግድ የከረመው ርዕዮት ሚዲያ በሚመራው በዚህ መድረክ የሚሳተፉትን አካላት የሚያግባባውና የመናገሪያ ድንበር የሚያበጀውና የቅድመ ውስወሳ ስራ የሚሰራው አቶ ልደቱ ነው” ያሉት እነዚሁ ወገኖች ቋሚ ” ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል በኦሮሞና በኦጋዴን በኩል የሚሳተፉትን ያስተባብራል” ብለዋል።
የምሁራን የሰማይ አንቀጥቅጥ ትዕይንት ሲካሄድ የሚሰጠው ርዕስ ምን እንደሆነ እንዳልሰሙ የዜናው ሰዎች ተናግረዋል። እነዚሁ ወገኖች ከዚህ በሁዋላ ቀጣዩ ትዕይንት የሲቪክ ማህበራት እንደሆኑ ገልጸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ የዘጉት የቪኦኤ ዋና አለቃ የነበሩትና ቦልቲሞር ግድም የሚኖሩት አቶ ንጉሴ አክሊሉ “ጋዜጠኛ” እያሉ ከሚመሩት ትረስት ኢትዮጵያ ተወክለው ተናጋሪ እንዲሆኑ ጥሪ ከሚቀርብላቸው መካከል መሆናቸው ታውቋል። ከጀርባ ሆነው የመስራት ባህሪ ያላቸው አቶ ንጉሴ ጥያቄው ሲቀርብላቸው ስለመቀበላቸው ለጊዜው አልተገለጸም። አቶ ልደቱ አብሮነትን የመሰረቱት እሳቸው በመሆናቸው ይታወሳል።
ዜናውን የሰሙ “አሜሪካ ያሉት የሲቪክ ማህበራት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከታጣቂዎች ጀርባ ያሉ፣ በታጣቂዎች ባለቤትነት የሚጣሉ፣ በብሄር ድርጅት እሳቤ የተቀኙና ብብሄሮች ውክልና የማይስማሙ ሲሆኑ፣ ጀርባቸው ፖለቲካና ፖለቲካ እንጂ ሌላ ባለመሆኑ ጊዜ ከማጥፋት ቁጥር ሁለት ኢህአዴግን በአዲሱ ስሙ ቢያስተዋውቁንና ወደ አራት ኪሎ ለመሳፈር የሚሳፈሩበትን የባቡር ስም ከወዲሁ ቢያስተዋውቁን ይሻላል” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
ጃዋር በሚዲያ ረሃብ እየተሰቃየ መሆኑ ተሰምቷል፤ በተጀመረው ሕብረት ላይቀጥል የሚችልበት አግባብ እንዳለ ተጠቁሟል። በግብጽ ዕርዳታ ሚኖሶታ ሳምፖል የነበረውን የኦኤምኤንን – OMN፣ አዲስ አበባ ከገባ በሁዋላ የገዛቸውንና የቋቋማቸውን ሚዲያዎች በስምምነት ችግር ከበተነ በሁዋላ አሁን ላይ የሚዲያ ችግር እንደገጠመው የሚቀርቡት እያስታወቁ ነው።
OMN ላይ ሲሰሩ የነበሩት እንደ ደጀኔ እንኳ የራሳቸውን OMN ቢያቋቁሙም መድረክ ከልክለውታል። በዚህም የተነሳ ሻዕቢያ ከሚረዳቸውና እነ ዶክተር ደብረጽዮንን የሚደግፉ ሚዲያዎች ብቻ አሁን የተጀመረውንና እሱም የተካተተበትን ትህነግንና ሻዕቢያን ከሃጢያታቸው የማጻዳት ንቅናቄ ከሚያርግቡ ሚዲያዎች በስተቀር አማራጭ አለማግኘቱ እረፍት ነስቶታል።
በቅርብ የሚያውቁት እንደሚሉት አዲሱ ትህነግንና ሻዕቢያን ከፈጸሙት ወንጀል የማጻዳቱ ንቅናቄ የወለጋ አካባቢ ተወላጆች የሚመሯቸው ውስን ሚዲያዎችን ብቻ የሚያምን ነው። በዚህ ሳቢያ ቀደም ሲል ሚዲያዎችን በሞኖፖል ይዞ የገፋቸው ባልደረቦቹ አሁን ላይ ገፍተውታል። የወለጋ አካባቢ ተወላጅ ባለመሆኑ የደረሰበትን መገፋት ለመቋቋም አዲስ ሚዲያ ለማቋቋም እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቋል።
ጃዋር አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት በርካታ ሚዲያዎች ስለነበሩት የሚፈልገውን መረጃ ያለተከራካሪ ያወራ እንደነበር የሚታወስ ነው።

