ሰሞኑን እየወጡ ያሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ስጋት የሚያመላክቱ መሆናቸውን ጉዳይን የሚከታተሉ እየጠቆሙ ነው። የግብጽ ፐሬዚዳንት አልሲሲ በሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ደብዳቤ ልከዋል። የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ባሉበት ቅጸበት የካቢኔ አባሎቻቸው አስመራ መግባታቸውና የትህነግ ዳግም ምሰንጠቅ ከሕዝብ እምቢታ ጋር ተዳምሮ ፖለቲካው ወዴት እያመራ ነው የሚል ጥያቄም እያስነሳ ነው።

ኢትዮጵያና ጣሊያን በጋራ ባዘጋጁት ሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ (UNFSS+4) ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡት የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ከግብጽ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ የተላከ መልእክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማቅረባቸው ይፋ ሆኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሀሰን ሼኽ ከግብጽ በአደራ ይዘውት የመጡት መልዕክት ይዘቱን ጠቅሶ ይፋ ያደረገው ዘ ዴይሊይ ሶማሊያ የተሰኘ ለፕሬዚዳንቱ ቅርበት ያለው የሶማሌያ ድረገ ገጽ የዜና አውታር ነው።
ድረ ገጹ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው አብደል ፈታህ አል ሲሲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ረዥም እድሜና ጤና ተመኝተዋል። ሀገራቸው ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው በይፋ አስታውቀዋል።
በደብዳቤያቸው ሃገራቸው ግብጽ የኢትዮጵያን ልማት እንደምትደግፍ ያስታወቁት አልሲሲ ፣ በዓባይ ወንዝ አጠቃቀምና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዝርዝር ኦፕሬሽን ዙሪያ በሁለቱ ሃገራት በመሪዎች ደረጃ ውይይት እንዲካሄድ የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን መልካም ፈቃድ ጠይቀዋል። ይህንኑ መልዕክት ይዘው የመጡት ሐሳን ሼኽ የማግባባት ስራ እንደሚሰሩም ተመልክቷል።
የግብጽ፣ የሶማሊያና ኤርትራ መሪዎች እ.ኤ.አ 10 October 2024 አስመራ ተሰብስበው የደረሱበትን ሥምምነት መግለጫ (The Asmara Declaration) እንደሚባል ይታወሳል። በዚሁ ስምምነት ኢትዮጵያ ላይ ያበሩት ሶስቱ አገራት አቋም ኢትዮጵያና ግብጽ በግል ከተገናኙ ምን ሊሆን እንደሚችል የጠየቁ እንደሚሉት የሰሞኑ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዲስኩር ከዚህ ፍርሃቻ የተቀዳ እንደሚሆን ገልጸዋል።
በመጀመሪያው ቀን ብሪክስን አራክሰው ወደ አሜሪካ በቀጣዩ ቀን አሜሪካን በመቀስ የፈረጁት ኢሳያስ አፉወርቂ የአሜሪካን መንግስትን ለመዳጀት ዳር ዳር ቢሉም በቀይ ባሕር ጉዳይ እስራኤል፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ ወዘተ አገሮች የያዙት አቋም ግብጽ በጀመረችው መንገድ እንዳትቀጥል እንዳደረጋት ውስጥ አዋቂዎች እየተናገሩ ነው።
ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መቀላቅሏ የማይቀር መሆኑን የተረዱት ግብጾች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመደራደር ጉዳዩ ያለቅለት በመሆኑ በቀሪ ጉዳዮች በእኩል አሸናፊነት ለመግባባት ፍላጎት እንዳልት እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ። በዚሁ መሰረት ሁለቱ መሪዎች ለንግግር ከተቀመጡ ግብጽ መጀመሪያ የምትወስደው እርምጃ ኢትዮጵያ ላይ የሚተኩሱና የሚያስተኩሱ አካላት ጋር ያላትን ግንኙነት ማቆም ነው። ይህ ካልሆነ ኢትዮጵያ ግድብ መስራቷን፣ ውሃውን መከተሯን ተቀጥላለች። ይህ አስተያየት የሰጡ “ኢትዮጵያ ኒኩሌር ታጠቀች” ሲሉ የግብጽ ሚዲያዎች የዘገቡት አስቀድሞ አካሄዱ ስለገባቸው እንደሆነ አምልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “እኛ የምናደርገውን ጠላቶቻችን ይረዱታል” ማለታቸውም የሚታወስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም አባይ ሲገደብ የኢትዮጵያን የመደራደሪያ አቅም እንደሚያሳድግ በተደጋጋሚ መናገራቸው አይዘነጋም። የአባይ ግድብና ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ሕልውና መሆናቸውን ደጋግመው ማሳሰባቸውም የሚታወስ ነው።
ይህ በንዲህ እንዳለ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒን አዲስ አበባ መግባታቸውን ተከትሎ የካቢኔ አባሎቻቸው አስመራ መግባታቸውም ታላቅ የፖለቲካ ፋይዳ እንዳለው እየተገለጸ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ የተካሄደው ስብሰባ አገራቸው ተባባሪ ከመሆኗም በላይ ልዩ መስተንግዶ እየተደረገላቸው ባለበት በዚህ ወቅት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ በኤክስ ገጻቸው እንዳሉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ ከጣሊያን ግብርና፣ የምግብ ዋስትናና ደን ሚኒስትር ፍራንሲስኮ ሎሎብሪጋዳ እና ከውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር እድሞንዶ ጋር አስመራ መገናኘታቸውን መግለጻቸው ዜናውን ከግጥምጥሞሽ በላይ አድርጎታል።
አቶ የማነ ሁለቱ አገራት በልማት፣ ኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ዘርፍና ስፖርት በርካታ ስምምነት ማድረጋቸውን ካመለከቱ በሁዋላ “The two sides also discussed regional peace, security and stability” በቀጣዊ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ መምከራቸውን አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ ዝርዝር አላስታወቁም። የተስማሙበትን ጉዳዮች ለመገምገም ተደጋጋሚ ቀጣይ ውይይቶች እንደሚደረጉ አስታውቀዋል።
የቀጣናውን በተለይም የኢትዮጵያንና የኤርትራን ሁኔታ የሚከታተሉ እንደሚሉት ጣሊያን የሽምግልና ሚና እየተጫወተች መሆኑ ይገልጻሉ። ኢሳያስ ሳዑዲ አረቢያ የጀመረቸውን ሽምግልና እንድታጠናክር በግልጽ ከተማጸኑ በሁዋላ የጣሊያን በጉዳዩ መግባት ምን አልባትም የተፈራውን ጦርነት ሊያስቀረው እንደሚችል ተገምቷል።
ግብጽ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በግልጽ የመወያየት እድሉ ከተመቻቸላትና ስምምነት ላይ ከደረሰች፣ ኢሳያስ ያላችው ብቸኛ አማራጭ ለሰላም እጅ መዘርጋትና መደራደር ብቻ እንደሆነ የሚነገሩ፣ በእነ ዶክተር ደብርጽዩን የሚመራው የትህነግ ፍንካች ዳግም መከፈሉ፣ እንዲሁም በትግራይ ሕዝብ ጦርነት በቃኝ በሚል ሰልፍ እየወጣ ትህነግን መቃወሙና ከሻዕቢያ ጋር እየተደረገ ያለውን ጥምረት ማውገዙ ሻዕቢያን ስጋት ላይ ጥሎታል።
ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሻዕቢያ ላይ ከፈተኛ ጥላቻና መንግስት ድጋፍ ከሰጠ ሻዕቢያን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ከአፋር፣ ከኤርትራ ተቀናቃኞች ጋር በመሆን የመቀናጀት እንቅስቃሴ አለ። ይህ በይፋ የሚታወቅ እንቅስቃሴ ሻዕቢያን ክፉኛ ስላሳሰበው አስቀድም መናዘዝ እንዲመርጥ እንዳደረገው በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው።
እነ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ስምረት ፓርቲ ያዘዋል የሚባለው ታጣቂ ኃይል አመራሮች ለቢቢሲ ትግርኛ ዓላማቸው ለሻዕቢያ ተገዛ ያሉትን ቡድን ጭምረ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እንደሆነ መናገራቸው ይታውሳል። ኢሳያስ አፉወርቂ ይህ ኃይል አስቀድሞ እንዲመታ ለእነ ምግበ መመሪያ ምስጠታቸውን አቶ ጥዑም ማናገራቸው የሚዘነጋ አይድለም።
የትግራይ ምሁራን፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች እና ሕዝብ በደፈናው ከሻዕቢያ ጋር እየተደረገ ያለውን ግንኙ እያወገዙ ሲሆን፣ የትግራይ ሕዝብ መንግስት እንዲያናግራቸው ጥያቄ ማቅረባቸው አይዘነጋም። ኤርትራን የሚደግፉና ኢትዮጵያ የባህር በር እንደምያስፈልጋት አንስተው የሚከራከሩና የሳይበር ዘመቻ ላይ ያሉ አካላት የትግራይ ሕዝብ፣ ምሁራን፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሻዕቢያን አብዝተው ስለመቃወማቸው አመለምዘገባቸው አቋማቸውን ግልጽ አድርጎ ያሳየ እንደሆነ እየተገልጸ ነው።
ከትናንት በስቲያ የወጣ አዲስ መረጃ ደግሞ የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ትህነግ ዳግም ለሁለት ተከፍሏል። ጦርነት የሚቃወሙና አቋማቸውን የቀየሩ በአንድ በኩል ሆነ እንደ ዶከር ደብረጽዮን ተቃውመዋል። ልዩነቱ እንደሚሰፋና መለያየታቸው ይፋ መሆኑ እንደማይቀር የሚናገሩ እንደሚሉት ልዩነቱ ወደ ኃይል እርምጃ እንዳያመራ ስጋት አለ።
የቀድሞ የትህነግ ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ስዬ ሰሞኑን “ድንቁርና የወለደው ትምክህት ወደ ውድቀት እየነዳቸው ነው” ላሉዋቸው ለነዚሁ ቡድኖች “እኔ ልምከራችሁ፣ ዓለም ጠባብ ናት፤ ወደ የትም ማምለጥ አይቻልም። እሳቱን አጥፉ” ማለታቸውን ጠቅሰን መዘገባችን የሚታወስ ነው።

