“የፌደራል መንግስቱ ሁሉንም አይነት ዛቻዎች እያደረሰብን ነው። አሁን አንድ አይነት አይደለንም፤ የፌዴራል መንግስቱ ቴክኖሎጂ እንዳለው እየነገረን ነው። እኛም ከትላንትናው ጋር አንድ አይነት አይደለንም፣ ቴክኖሎጂ አለን፣ ትናንት ያልነበረን መሳሪያ አለን። የትግራይን ሉዓላዊነት ለመመለስ ዝግጁ ነን፣ አሁን ላይ ከመቼውም ጊዜ የተሻለ አቅም ፈጥረናል።
ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች ግራ የሚያጋቡ ናቸው። በትግራይ ሕዝብ ጦርነት እንደሰለቸው የሚሰማው በሁሉም አቅጣጫ ፣ ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ዕድሜ፣ ጾታ፣ የትምህርት ደረጃና የፖለቲካ ልዩነት ሳይለይ በአንድነት ነው። የሰላም ጩኸቱ ብርቱ የመሆኑን ያህል ሕገመንግስቱን በጣሰ መልኩ ከሻዕቢያ ጋር፣ እንዲሁም ከሌሎች የአገር ውስጥ ታጣቂዎች ጋር ግምባር ፈጥሮ ሰፊ የጦርነት ዝግጅት የማድረጉ ጉዳይ የመንግስትን ትዕግስት እየፈተነ መሆኑን ያሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ነው።
መንግስትም የሕዝቡን ጦርነት ያለመፈለግና የሰላም ጥሪ በመደገፍ፣ የሕዝብን ፍላጎት እንደሚያከብር ደጋግሞ ቢያስታውቅም የጊዜያዊ መንግስቱን በኃይል ከማፍረስ ጀመሮ በትግራይ እየተከናወነ ያለው ሁሉ መታገስ የማይችልበት ደረጃ መዳረሱንም እያስታወቀ ነው። የመንግስት መገናኛዎችም ጠንከር ያሉ ጉዳዮችን በማንሳት ይህንኑ የመንግስትን ትዕግስት ደረጃ የሚያሳዩ ዝግጅቶች እያቀረቡ ይገኛሉ።

ከሻዕቢያ ለትግራይ ሰዎች በትግራይ እናቶች፣ እህቶችና ሕጻናት ማህጸን ውስጥ የተላኩ ደብዳቤዎች፤ ”
“እኛ የኤርትራ ልጆች ጀኞች ነን፤ ለዚህም እራሳችንን ጥተናል፤ በዚህ ተግባራችን ወደፊት እንቀጥላለን፤ የትግራይ ሴቶችን መካን እናደርጋለን ወይም ማሕጸናቸውን እናደርቃለ”
መንግስት በገሃድ መግለጫ አውጥቶ ሻዕቢያ ኢትዮጵያን ለማተራመስ እየሰራ መሆኑን፣ በውክልና ስልጠና እየሰጠ፣ ትጥቅ እያሸከመ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልክ ገልጾ የዓለም ዓቀፉ ሕዝብረተሰብ ” ተው ይበልልኝ” ቢልም የእነ ደብረጽዮን ቡድን ከሻዕቢያ ጋር የጀመረውን “ጥምዶ” ቀጥሏል።
ይህ በንዲህ እንዳለ ነው ” የትግራይ ሕዝብ ለጦርነት ተዘጋጅ” ሲሉ በእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን በኩል ያለውን የትግራይ ታጣቂ ኃይል ከሚመሩት መካከል አንዱ የሆኑት ጄነራል ኃይለ ሥላሴ ግርማይ (ወዲ እምበይተይ) ጥሪ ያሰሙት። ጥሪው “ጦርነት በቃኝ” ላለው ሕዝብ አስደንጋጭና አሳሳቢ ቢሆንም ራሱን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የለየው የትግራይ አባሰላማ ባወጣው መግለጫ ይህ አልታየውም። እንዳውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” ጦርነት ሳይጀመር ተረባረቡ” ሲሉ ለሃይማኖት አባቶች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ያገባናል ለሚሉ ሁሉ ያቀረቡትን ጥሪ ” የትግራይን ውሳጣዊ ሁኔታ ያልተረዱ” በሚል አውግዞ ነው ልዑክ እንደሚልክ ያስታወቀው።
የትግራይ ታጣቂዎችን ለማጠናከር በአድዋ ከተማ የካቲት 11 ስታዲየም አርሚ 42 ኮር 423 ኮማንዶ ብርጌድ ባስመረቀበት ወቅት ጄነራል ኃይለ ሥላሴ ግርማይ (ወዲ እምበይተይ) ሕዝብ ለጦርነት እንዲነሳ ጥሪ ሲያቀርቡ የትግራይ የሓይማኖት አባቶች ይህ እስከተጻፈ ድረስ ያሉት ነገር የለም።
የወልቃይት ጠገዴ አባቶች ” በሃይማኖት ስም የተሸፈነ የትህነግ ዓላማ አስፈጻሚ” ሲሉ የነቀፉት የትግራይ ኦርቶዶክስ በትግራይ ሰማይ ስር በርካታ አሳሳቢ ጉዳዮች በገሃድ፣ በምስልና በቃል ደረጃ እየተከወኑ ቢሆንም ሲቃወም አይሰማም።
በጦርነቱ ወቅት “ጠላት” ሲሉትና በርካታ ሰዎችን በጅምላ ሲገድል፣ ሲደፍርና ሲዘርፍ የነበረው ሻዕቢያ በትግራይ እንዳሻው ሲናኝ የትግራይ “አባቶች” ዝም ማለታቸውን አድሮ የተገለጸላቸው የትግራይ ተወላጆች ሳይቀሩ ነቅፈዋል።
የትግራይ እህቶችና እናቶች ማሕጸን ውስጥ ደብዳቤና የዛጉ ሚስማሮች በመክተት ሰው ሊያስበው የማይችል ግፍ ሲፈጽሙ የነበሩ፣ ይህንን ግፍ ታዘውና ሆን ብለው ይፈጽሙ እንደነበር፣ ግፉን በአስከፊ ደረጃ ሲፈጽሙ እንደሚገመገሙ፣ ሲገመገሙ ከተባሉትና ከታዘዙት በታቸ እንደሚፈጽሙ፣ ይህንኑ የሚያደርጉት ዛሬ በትግራይ ጥምዶ የፈጠሩት ጄነራሎችና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች መሆናቸው ተጠቅሶ የቀረቡ ሪፖርቶችን በዝምታ ማለፋቸው በርካቶችን አስገርሟል። የሓይማኖት አባቶቹን ብቻ ሳይሆን፣ የትግራይ ሕዝብ መብት ተቆርቋሪ መሆናቸውን የሚገልጹ አክቲቪስቶችና የሚዲያ ባለቤቶች ዝምታ መምረጣቸው ” ገንዘብ ሲናገር ፍትህ ጭጭ ይላል” የሚለውን ብሂል ያስታወሰ መሆኑን በርካቶች እየገለጹ ነው።
የጄነራሉ በምስል የተደገፈ ንግግራቸውን በማጋራት ተርጉመው ካሰራጩ የሚታወቁ የማህበራዊ አውዶች ለመረዳት እንደተቻለው ጄነራሉ “የትግራይ ህዝብ ለጦርነት ተዘጋጅ” የሚል ጥሪ ሲያሰሙ ” አዎ እየተዘጋጀን ነው። እኛ እየተዘጋጀን ያለነው ግን ለመውረር አይደለም” የሚል ምክንያት ሰጥተዋል።
አክለውም ዝግጅት እያደረጉ ያለበትን ምክንያት ሲያስረዱ “እንድንዘጋጅ ስለተገደድን ነው” ብለዋል። አክለውም “ከሻዕቢያ ጋር ፅምዶ (ቅንጅት) እየፈጠራችሁ ስለሆነ እናጠፋችኋለን ስለተባልን ነው የምንዘጋጀው” በማለት አስረድተዋል። ይህ አግባብ በኢትዮጵያ ህኛ ማዕቀፍ ውስጥ የሚቻል እንዳልሆነ እያወቁ በአደባባይ ከሻዕቢያ ጋር እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል።
በቅርቡ ዶክተር ደብረጽዮን ከሻዕቢያ ጋር ህብረት ለመፍጠር የማንንም ፈቃድ መጠየቅ እንደማያስፈልጋቸው ገልጸው መናገራቸው አይዘነጋም።
የትግራይ ሕዝብ ለጦርነት እንዲዘጋጅ ጥሪ ያቀረቡት ጄነራል አዳዲስ ሰልጣኞችን ሲያመስርቁ፣ “መንግስትን አስገድዶ ያስፈረመ የፀጥታ ሃይል (ታጣቂ ወጣት) ነው ያለን።በፀጥታ ሃይላችን ላይ አንጠራጠርም።አሁን ጠላቶቻችን እየፎከሩ ያሉት ግን በፀጥታ ሃይላችን ላይ ብቻ አይደለም። በመላው ህዝባችን ላይ ነው እየፎከሩ ያሉት።በመሆኑም ህዝባችን መዘጋጀት አለበት።በተለይ ሃብት ላይ ትኩረት ያድርግ።በሰርግና በተዝካር የሚባክን ሃብት ሊኖር አይገባም….” በማለት ማሳሰቢያና አቅጣጫ ሲሰጡ ተሰምተዋል።
“አቅማችን እንደ ትናንቱ አይደለም። ጦርነቱን ለምደነዋል። እኛ ከሌሎች ጋር አጋርነትን በዓይነት ስንጨምር ጠላት (አራት ኪሎ ያለው) ወዳጆቹን አጥቷል። ትናንት ያልነበረ ቴክኖሎጂ የጦር መሳሪያ አለን እያሉ ይዝታሉ። እንደውም ትናንት ያልነበረን መሳሪያ ያለን እኛ ነን፣ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያ ታጠቅናል። ቀደም ሲል ያለውንም ያፈረሰ እና ያዋረደ ጠላት ነው” ሲሉ ከሻዕቢያና ጋር የፈጠሩትን ጥምረት አድንቀዋል። ከሻዕቢያ ጋር ሆነው ኢትዮጵያን በጠላትነት ፈርጀዋል።
ይህ ሁሉ የሚሆነው ከፌደራል መንግስት በሚላክ በጀትና በህገወጥ በኤርትራ በኩል በሚጋዝ ወርቅ እንደሆነ የጠቆሙ፣ እንዲህ ያለው ንግግር ለታሪክ የሚቀመጥ መሆኑን አመልክተዋል።
በተመሳሳይ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ በትናንትናው ዕለት ከውቅሮ ህዝብ ጋር ውይይት ሲያደርጉ፣ የሰጡት ማብራሪያ “እኚህ ደው ሹመኛ መሆናቸውን ረሱት እንዴ” ያስባለ ሆኗል።
ነጥቦችን ዘርዝረው ለመፈጸም ቃል በመግባት ክልሉን ለመራት ከፌደራል መንግስት የተሾሙት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ፣ አጠቃላይ ፀጥታውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ “እኛ” ሲሉ ራሳቸውን ከመንግስት ገንጥለው ምላሽ ሰጥተዋል።
በምላሻቸውም “ሰራዊት እያሰለጠንን ነው። ግን ለጦርነት እየተዘጋጀን አይደለም” ካሉ በሁዋላ ራሳቸው የፌደራል መንግስት ሹመኛ ሆነው ሳለ፣ ” ጦርነቱን የፌደራል መንግስቱ ካልጀመረ በስተቀር እኛ ጦርነቱን አንጀምርም” ብለዋል።
ነፃ መሬት ላይ ሰፍሮ ያለውንና ራሱን “የትግራይ ሰላም ኃይሎች” ሲል የሚጠራውን ከአስራ ሁለት በላይ ክፍለጦር፣ “እዚህ ግባ የሚባል አይደለም” ሲሉ ተሰምተዋል። አክለውም ” በአፋር እና በፌዴራል ስለሚደገፉ በድርድር እንዲፈታ እየሰራን ነው” በማለት መልሰው ንግግራቸውን አባርደዋል።
ይህን ኃይል ፌደራል መንግስትም ሆነ አፋር እንደሚደግፈው መግለጻቸውን ተከትሎ ከአፋር ክልልም ሆነ ከመንግስት ይህ እስከተጻፈ ድረስ የተባለ ነገር የለም።

