Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው፤ እንዳያልቅ ተጀምሮ ተጠናቀቀ
News

ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው፤ እንዳያልቅ ተጀምሮ ተጠናቀቀ

Ethioreview newsEthioreview news—August 30, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣውን፤ በ4 ወራት ይጠናቀቃል የተባለውን እና 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በዓመት ማምረት ይችላል ተብሎ የተነገረለትን የማዳበሪያ (የዩሪያ) ፋብሪካ ለመገንባት ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ስምምነት ሲፈረም በሰጡት አጭር መግለጫ ፋብሪካው እንደ ዓባይ ግድብ እንደማይሆን ተናግረው ነበር። 

ይህ ፕሮጀክት “በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚመራ ስራቴጂክ ፕሮጀክት ነው፤ በከፍተኛ ዲሲፒሊንና ቁጥጥር የሚደረግ ነው፤ እንደ ሕዳሴ ግድብ ሜጋ ፕሮጀክት ነው፤ ሕዳሴ ላይ የነበረው ስህተት እዚህ አይደገምም፤ በጥንቃቄና በጥናት የተጀመረ ፕሮጀክት ነው፤ በዕውቀትና በጥንቃቄ ብቻ ነው የሚመራው፤ ምክንያቱም አንድ ፕሮጀክት መጀመራችን ሳይሆን በጥንቃቄ ካልመራነው ተጨማሪ ኃብትና ጊዜ ስለሚያባክን እንደዚህ ዓይነት ስህተት እንዳይፈጠር በጥንቃቄ ነው የምንጀምረው፤ በጥንቃቄ ነው የምንጨርሰው፤ ዋናው ማረጋገጥ የምፈልገው ነገር በተባለው ጊዜ ይህንን ፕሮጀክት እንጨርሰዋለን” ብለዋል።

መለስ ዜናዊ ስሙ በውል ያልታወቀውን ግድብ ሲያስጀምር፤

  • መጀመሪያ ላይ የሚሊኒየም ግድብ ተባለ
  • በኋላ ታላቁ ሕዳሴ ተባለ
  • ግድቡን መገንባት የተጀመረው መጋቢት 24/2003 ዓ.ም.
  • በአምስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር
  • ወጪው አራት ቢሊዮን ዶላር ወይም እስከ 4.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ነበር የተባለው። 

ይህ ያለ ዕውቀትና ያለ ዕቅድ መለስ ዜናዊ እንዳያልቅ አድርጎ ያስጀመረው ግድብ ለቀድሞውና አሁን ሕገወጥ ለሆነው ትህነግ ተሰጥቶ ሲሚንቶ ከኤፈርት (መሶበ)፤ ሥራው ደግሞ መርከብ በጠራራ ፀሐይ ሲሸጥ ለነበረውና ክንፈ ዳኘው ይመራው ለነበረው ሜቴክ ለተባለ ድርጅት ነበር የተሰጠው። 

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

ከለውጡ በኋላ ሥራው ቆሞ የነበረውን የዓባይ ግድብ እንደገና ለማስጀመር ጥረት ሲደረግ በወቅቱ ከአራት ኪሎ የተባረረው ትህነግ የፈጸመው ግፍና በደል ይፋ መሆን ጀመረ። ምሥጢሩ እንዳይጋለጥበት የፈለገው ትህነግ፤ በገዳይ ስኳዶቹ ሰዎችን ማስወገድ፣ ሰነድ ማጥፋት፣ መረጃ መሰወር ጀመረ። 

ሌላው ይፋ የሆነ ነገር ሥራውን እንደገና ለማስጀመር ኮንትራክተሩ ሳሊኒ በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ያልተከፈለኝ ውዝፍ ዕዳ አለና ይከፈለኝ የማለቱ ዱብዕዳ ነበር። በመጨረሻም በተደረገ ድርድር 450 ሚሊዮን ዩሮ ወይም ወደ 28 ቢሊዮን ብር ተከፍሎት ሥራው እንደገና ተጀመረ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ልዩ ክትትል እየተደረገለትና በኮንስትራክሽን ሥራው ላይ በርካታ ለውጦች ተደርጎ አሁን ለምረቃ ደርሷል። 

በዕውቀትና በጥንቃቄ ሳይመራ ቀርቶ ግድቡ ተጨማሪ ወደ 10 የሚጠጋ ዓመታትን አስጨምሯል፤ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ተጨማሪ ወጪ አስወጥቷል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ያገራችንን ዜጎች 10 ዓመት ሙሉ በጨለማ እንዲቆዩ አድርጓል፤ ለጎረቤት አገራት ተሽጦ የሚገባውን በቢሊዮን የሚቆጠር ገቢ አሳጥቷል። 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሥሪያ ቤት እንዳወጣው መረጃ ከዓባይ ግድብ ኃይል ሽያጭ፤ ባለፈው ዓመት 140 ሚሊዮን ዶላር፤ በዚህ ዓመት ደግሞ 300 ሚሊዮን ዶላር፤ ግድቡ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ደግሞ በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያገኝ ተናግሯል።  

ግምቱን በግማሽ ብናሳንሰውና ዓባይ ግድብ በዓመት 500 ሚሊዮን ዶላር ከኃይል ሽያጭ ያስገባል ብንል፤ በተባለበት ጊዜ ተጠናቅቆ ቢሆን ኖሮ ባለፉት 10 ዓመታት በትንሹ አምስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ከኃይል ሽያጭ ማድረግ ይቻል ነበረ። በሌላ አነጋገር ግድቡ ወጪውን ሸፍኖ ነበር ማለት ነው።

ያለ ዕቅድ፣ ያለ ዕውቀት የሚጀመር ሥራ ዕዳው ብዙ፤ ጉዳቱ የማይገመት ነው።  

ከሚዲያው ሰፈር ደግሞ አንድ ጉዳይ እንጥቀስ። የዓባይ ግድብ ሥራ እንደማይቀጥል ብዙ ከተወራ በኋላ፤ የታሰበው አልሳካ ሲልና ግንባታው እንደገና ሲጀምር “ዐቢይ ሸጦታል”፣ “ዐቢይ ከግብፅ ጋር ተስማምቶ የኃይል ማመንጨት ዓቅሙ እንዲቀንስ ተደርጓል”፤ ወዘተ እየተባለ ሲነገር ቆየ። ይህም አልሳካ ብሎ ግንባታው እየተፋፋመ ሲሄድ ባንዳነትን ጌጥ ያደረጉና ለዶላር የተሸጡ በሌላ ሰበር ዜና መጡ።

የዛሬ አምስት ዓመት ከስድስት ወር ላይ ዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግስት የመፈረም ፍላጎት እያሳየ ነው፤ ዋዜማ ራዲዮ የስምምነት ረቂቅ ሰነዱን አግኝታለች” ብለው በሰበር ኢትዮጵያን ሊሰባብሩ ሞከሩ። ጎልጉል በነጻ የሕዝብ አስተያየት ዓምዱ ጥያቄ አቀረበ፤ ዋዜማዎች በድፍረት ለጻፉት በስውር መልስ ሰጡ። መልሳችንን አታትሙብን ስላሉን አክብረን ዝም አልን፤ እነሱ ግን እስካሁን አግኝተነዋል ያሉትን “የስምምነት ረቂቅ ሰነድ” አላወጡም። ይቅርታም አልጠየቁም።

በወቅቱ ዋዜማ ከጻፈው ውስጥ አንድ አንቀጽ ብቻ ሕዝብ እንዲታዘብ ከዚህ በታች አቅርበነዋል፤

“ዋዜማ ራዲዮ ያገኘችው ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሞላልና ድርቅ ቢከሰት ማካካስ እንዲቻል በሚል እንዲፈርሙበት የተዘጋጀው ረቂቅ የስምምነት ሰነድ፣ ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት ችለናል። በዚህ ረቂቅ ስምምነት ላይ ሁለት የኢትዮጵያን ጥቅም አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ይዘቶች እንዳሉ ዋዜማ ራዲዮ ሰነዱ ላይ ከባለሙያዎች ማብራሪያን አግኝታለች። ሁለቱም አደጋዎች ያሉት ድርቅ፣ ተከታታይ ድርቅና ረጅም ዝናብ አጠር አመታት ቢከሰቱ የሚደረገው ማካካሻን የተመለከተው የሰነዱ አካል ላይ ነው።”

የዓባይ ግድብ 13 ተርባይኖች የሚኖሩት ሲሆን አጠቃላይ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅሙ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት እንደሚደርስ ተገልጿል። ይህም በአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ አመንጪ ያደርገዋል። 

ግድቡ 145 ሜትር ከፍታና ወደ ጎን ደግሞ 1,780 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ሙሉ በሙሉ ሲይዝም ውሃው የሚተኛበት ስፍራ ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር (ከአዲስ አበባ ሻሸመኔ) እንደሚደርስ ከሰባ በላይ ደሴቶች እንዳሉት ተገልጿል።

የዓባይ ግድብ ያለ ዕቅድና ያለ ዕውቀት ቢጀመርም በዕቅድና በዕውቀት ተመርቶ ተጠናቋል። የዓባይ ግድብ የውኃ ጠብታ ጥርቅም ብቻ አይደለም የደም፣ የላብ፣ የዕንባ ጠብታም ነው።

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ የውኃ ኒውክሊየር የታጠቀች፤ ማንም የማይደፍራት፤ ለሌሎች አፍሪካ ሀገራትና ለመላው የጥቁር ሕዝብ እንደ ዓድዋ የኩራት ተምሳሌት ሆናለች።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
እውነታው ይኼው ነው! “የህዳሴውን ግድብ ለግብጽ ሸጡት”
Dangote-Ethiopia Deal: A New African Renaissance
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2