ባንዳዎች ባዳዎቹ በሚቀርጹላቸው አጀንዳ ላይ ተመስርተው የህዳሴውን ግድብ ለግብጽ ሸጡት፣ ህዳሴ ፣ ህዳሴ የሚሉት የውስጥ ፖለቲካ አጀንዳ ለማስቀየር ነው በሚል በአንድ ወቅት ዘመቻ ከፍተውብን ነበር ። ግብዓቶች ወደ አካባቢው እንዳይጓጓዙ በትጥቅ የተገዛ መሰናክልን ጨምሮ የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል። በፀጥታው ም/ቤት ፊትም ከ13 ያላነሳ ጊዜ ቆመናል። እነዚህን ሁሉ በብቁ የአመራር ጥበብ፣ በደምና በላባችን ተሻግረን የኢትዮጵያውያን ኩራትና የወል አርማ የሆነውን የህዳሴ ግድብ አጠናቀናል። ታሪክም ተቀይሯል። የህዳሴው ጉዳይ አሁን ታሪክ ሆኗል።
የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ የበጋ ስንዴ፣ የሌማት ቱሩፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ብዙዎች ቀልደውበታል። ዛሬ እነዚህ ኢንሼቲቮች እጅግ ውጤታማ እና የኢትዮጵያ አለኝታ ሆነዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአድናቆት ተሻግረው ሀገራችንን ተሸላሚ እያደረጉ ነው። በስንዴ ምርት እራሳችንን ከመቻል አልፈን ከአፍሪካ ቁጥር አንድ ስንዴ አምራች ሀገር ሆነናል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሶስተኛው ቡና አምራች እና ላኪ ሀገርም ሆነናል። ከተረጅነት ወደ ምርታማነት እየተሸጋገርን ነው።
የኮሪደር ልማት ሥራ ሲጀመር ታሪካችንና ቅርሶቻችንን ሊያጠፉ፣ ነባሮችን በማፈናቀል የዲሞግራፊ ለውጥ ሊያደርጉ ነው፣ ወዘተ በሚል ሰፊ ዘመቻ ነበር። ዛሬ ከተሞቻችን በኮሪደር ልማቱ መጥፎ ገጽታቸው ተቀይሯል። በአስቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች የአኗኗር ዘይቤያቸው ተቀይረዋል። ከተሞቻችን ጽዱና ለነዋሪዎች የሚመቹ፣ አካታችና የተሳለጠ የመሠረተ ልማት ባለቤት መሆን ችለዋል። መዲናችን እንደ ስሟ ውብ አበባ ሆናለች። በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአንድ ዓመት ማዘጋጀት ችላለች። ከተማን መገንባት “እንደ አዲስ ነው” በሚል ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ምሳሌ መሆን ችላለች። በገነባችው መሠረተ ልማት ደህንነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከምርጦቹ ጋር ተወዳድራ የወርቅ ተሻለሚ ለመሆን በቅታለች። ተሞክሮዋን ወደ ስልሳ የሀገራችን ከተሞች አስፋፍታለች።
ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ስትገባ የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ግሽበት፣ አመጾች፣ ወዘተ ይፈጠራሉ በሚል በጣም በርካታ ሟርት፣ የሚዲያ ዘመቻ ነበር። በብልህ አመራርና ውጤታማ ዝግጅት ላይ ተመስርቶ በመከናወኑ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለየትኛውም ጫና አይበገሬነቱን በማረጋገጥ ከ8.4 በመቶ በላይ እንደሚያድግ ይጠበቃል። የዋጋ ግሽበት እየተሻሻለ መጥተዋል። የኢትዮጵያ ኤክስፖርት ከእጥፍ በላይ በማደግ 8.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቷል። ሪዘርቫችን በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። የመንግስት የማስፈፀም አቅም ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሯል። ከማንሰራራት ወደ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ የሚያፈጥኑ እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና ግዙፉን የአየር ማረፊያ፣ የፈጣን መንገዶች ግንባታ ለመሻገር ዝግጅቶች ተጠናቀዋል።
የባዳ እና የባንዳ አዲሱን የቅንጅት ድግስ በአይነ ቁረኛ እየጠበቁ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው መሠረታዊ ጉዳዮች እና ብሔራዊ ጥቅሞቻቸው ላይ የጋራ አቋም ይዘዋል።
በብልህ እና ቆራጥ አመራር እየተመሩ እንደ ግመሉ ሠራተኞቹ ጉዟቸውን ቀጥለዋል። አውሮቶ አደሮቹ ዛሬም እንደ…ጩኸታቸውን ቀጥለዋል። እውነታው ይኸው ነው
By Oluma views FB

