“ ምን ዓየነት ዘመን ላይ ደረስን? ምን ዓየነት ትውልድ ገጠመን? እንዴት ያለ የክህደት ዘመን ላይ ደረስን? ምን ጉድ ነው የመጣብን?” በሚል ለምትብሰለሰሉ የሌተናል ጻድቃን ቃለ ምልልስ ወደ አማርኛ እንዲመለስ ጠይቁ፣ አስጨንቁ። የስብሃት ትህነግ አዲስ መደብና ትርክት ለመፍጠር ሲፈጽም የኖረው ሴራ ግልጽ ያደርገዋል።
“ዩሪ ቢስሜኖቭ በቀደመችው ሶቪየት ህብረት ኬጂቢን ሲያገለግል የነበረ፣ በጋዜጠኛናት የሰራ ሰው ነው። አሱ አንደሚለው አንድን አገር አንበርክኮ ለመግዛት ትውልድን ማላሸቅ፣ ትውልዱን አላሽቆ አውነትን እንዳይቀበል ማድረግ፣ በተቋማት ውስጥ የላሸቁትን በመመደብ ማንኮታኮት መበተን፣ ኢኮኖሚውን ማናጋት፣ ቀውስ መፍጠር፣ በቀውስ ወስጥ ማህበራዊ እረፍት መንሳት፣ ይህ ሁሉ ከሆነ በሁዋላ ኖርማላይዜሽን ወይም አረጋጊ መስሎ ወደ ቤተመንግስት መሮጥ” እዚህ ላይ ይጫኑና ይህን ጽሁፍ ያንብቡ። እጅግ የሚገናኙና ጻድቃን ይፋ ወደ አደረጉት ወደ ቀጣዩ “የአዲስ መደብ” ምስረታ ሚስጢር ይወስድዎታል።
አዲስ መደብ፣ አዲስ ትርክት የከሸፈው ዕቅድ
የመጽሃፉ መነሻና መድረሻ ስልጣንን በቤተሰብ በመቀራመት ኢኮኖሚውን፣ ፖለቲካውን፣ ወታደራዊ ክንፎችን ስለመቆጣጠርና ሚዲያው በክንድ ስር አድርጎ አዲስ ትርክት የተጋተ አዲስ ትውልድ በመፍጠር፣ አዲስ መደብን ስለመገንባት ነው። ከዚህ እሳቤ ውስጥ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ያልሆነው የቱ ነው? ዛሬ ኢትዮጵያ መረጋጋት ያቃታጽ ለምንድን ነው? እንዳትረጋጋ የሚያደርጓጽ እነማን ናቸው?
ሌተናል ጄነራል ጻድቃን የጠቀሱት ስም Milovan Djilas / ጂላስን ነው የመጻህፉ ባለቤት። ዲጅላስ የዩጎስላቪያ ኮሚኒስት ሊግ ተዋናይ ሲሆን በአገሩ ዘውዳዊ አገዛዝ ሲገረሰስና ስርዓት ሲለወጥ እንዴት አዲስ መደብ፣ አዲስ ትርክት፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እንዲሁም የወታደራዊ የበላይነትን በፍጹም የበላይነት መቆጣጠር እንደሚቻል በመጽሃፍ ያኖረ ነው። ትህነግም ዕለት ዕለት ገጽ በገጽ ሲተገብረው የነበረው ይህንኑ መጽሃፍ ስለመሆኑ ከቀባሪው አንደበት ተሰምቷል።
ሌተናል ጀነራል ጻድቃን ትህነግ ከስልጣን ከተወገድ ሰባት ዓመት በሁዋላ ያነሱት ጂላስ ይህንኑ ስልት የጻፈበት መጽሃፍ ርዕሱ NEWS CLASS/ አዲስ መደብ የሚል ነው። ጻድቃን ስሙን ጠቅሰው እንዳሉት የስብሃት ትህነግ ይህን መጽሃፍ መመሪያው በማድረግ በኢትዮጵያ አዲስ ትርክት የተጋተ አዲስ ትውልድ፣ ለመፈጠር፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የወታደራዊ ወዘተ ፍጹም የበላይነትን እንዴት ሊቆጣጠር እንደቻለ ይፋ አድርገዋል።
መንግስትን፣ ሚዲያን፣ ኢኮኖሚና ሚሊታሪውን የተቆጣጠረው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት በዚሁ መርህ መሰረት ይሰራ እንደነበር በርካቶች ቀድሞ የገባቸው ሲናገሩ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ትህነግ የፈጠራቸውን ድርጅቶች አሰልፎ የሽግግር ካውንስል ሲመሰርት ጀምሮ አካሄዱ የገባቸውና የተቃወሙ ከአስመሳዮቹ በስተቀር ዛሬ አብዛኞቹ የሉም።
ኢትዮጵያን ለአርባ ዓመታት በሁሉም አገባብ የበላይነት በመያዝ ለመግዛት ዕቅድ ነድፎ በ27ኛው ዓመቱ ሁሉንም ያጣው ትህነግ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ እንዳትረጋና እንዳታርፍ ቀድሞ በዘረጋቸው የደህንነት፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የወታደራዊ ወዘተ መዋቅሮቹ በከፍተኛ ደረጃ ሁከት ስፖንሰር በማድረግ እየሰራ መሆኑን በድፍረት ሲናገሩ ለነበሩ ትልቅ ምስክርነት የሚሆን መረጃ የሰጡት ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ቲቢኤስ ቲቪ በሚባል ሚዲያ ከአዲስ አበባ ነው።
” አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሁለት ነባር ወታደራዊ አመራሮች ‘ ምንቅስቓስ ደለይቲ ለውጢ ‘ (የለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ)
የጻቃን ሃዘን ሲገልጸ ከኮር በላይ የሰራዊት አመራር መሆናቸውን የሚናገሩ የፈጸሙት ድርጊት ቀድሞ ይነሳል እነዚህ አመራሮችና ፖለቲከኞና.በሻዕብያ ሰላይ ሰርገ ገቦች ምክንያት ወደ ትግራይ ለመግባት አይችሉም። ይህን ሲገልጹ “እጅግ እጅግ ይቆጨኛል” ይላሉ። ሻዕቢያ በሚፈነጭባት ትግራይ ጻድቃን ተባረዋል።
“የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ አዲስ የለውጥ ማዕበል እየመሩ መህኑን አስታወቀዋል። “ምንቅስቓስ ደለይቲ ለውጢ ፣የትግራይ ንቅናቄ ለለውጥ” የሚለውን አዲስ አደረጃጀት ይመራሉ።
የጻድቃን ትግራይ ብሮድካስቲንግ ስርቪስ TBS ከተባለው ሚዲያ ጋር ያደረጉት ረዥም ቃለ ምልልስ ከቀድሞዎቹ ሁሉ የተለዩና በትህነግ ተቀጣሪዎች ከሚነገረው አደንቋሪ ትርክ ሕዝብ ይገላገል ዘንድ ታላቅ ጠቀሜታ እንዳለው ቃለ ምልልሱን የሰሙ ገልጸዋል። እነዚህ ወገኖች በቃለ ምልልሱ የትህነግን አሟሟትና ሽኝት ለማጣደፍ የቀረቡትን ስትራቴጂዎች በማንሳት ጉዳዩ ለሻዕቢያ መርዶ እንደሆነ ገልጸዋል። ትህነግ ለፈለፈላቸውና ለሚያስታጥቃቸው ታጣቂዎችም አስደንጋጭ እንደሆነ ገልጸዋል።
ትህነግ ስርዓታዊ ይዘት ወይም systemic አካሄድ በመከተል እንዴት አድርጎ ኢትዮጵያን ይግጥ እንደነበር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው የጻድቃን ቃለ ምልልስ፣ ይህንን ድርጅት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመንቀል ድርጅት መመስረቱን ይፋ አድርገዋል።
“Movement of Tigreans for change / የትግራይ ንቅናቄ ለለውጥ” የተሰኘ አራት የትግራይ ፓርቲዎች የተካተቱበት ንቅናቄ መፈጠሩን ገልጸዋል። አርና፣ ባይቶና፣ ትግራይ ነጻነት ፓርቲና ስምረት ተጣምረው የሚንቀሳቀሱበትን የትግል አውድ የሚመሩት ደግሞ ራሳቸው ሌተናል ጄነራል ጻድቃንና ተክላይ አሸብር እንደሆኑ አስታውቀዋል።
ህብረቱ በፖለቲካ፣ በሕዝብ ንቅናቄና፣ በታጣቂ ኃይሎች እንዲሆም በእንቢተኛነት የትህነኝ ኃይል በማሽመድመድ ማስወገድ እንደሆነ ከቃለ ምልልሳቸው ለመረዳት ተችሏል።
ከእነ ዶክተር ደብረጽዮን ጋር አዲስ ጥምረት ለፈጠረውና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ “የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪቃ አለኝታ” ሲሉ በግርድና የሌለውን ማዕረግ ለሰጡት ሻዕቢያ ታላቅ ራስ ምታት እንደሚሆን የተነገረለት ሕብረት፣ ለቲዲኤፍ ኃይሎች ሶስት ጥሪ አስተላፏል።
ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ከእነ ዶክተር ደብርጽዮን ጋር ላሉት የቲዲኤፍ ታጣቂዎች፣ ቲፒፒን / የትግራይ ሰላም ኃይሎችን መቀላቀል፣ ካልሆነም ቤታቸው መቀመጥ፣ አለያም ባለመታዘዝ ትግሉን እንዲያግዙ ሶስት መልክ ያለው ጥሪ አቅርበዋላቸዋል።
ትግራይ ሰባ አምስት በመቶ በጀቷን ለወታደር የምታውል ክልል
ጻድቃን በለዚሁ ቃለ ምልልሳቸው ያነሱት ሌላ ጉዳይ ትግራይ የበከቷን ሰባ አምስት በመቶ ለወታደሮች እያዋለች ያለች ብቸኛ ክልል መሆኗን ነው። እሳቸው ይህን ሲሉ በትግራይ ያቄር ማእከላዊ ዞን ቆላ ተምቤን ወረዳ የምትገኝ የገጠር ቀበሌ በርሃብ መጠቃቷን ልብ ከሚሰብር ምስል ጋር ወረዳው ይፋ አድርጓል።
ትህነግ የክልሉን በጀት 75% ሲያምነዥግ የወረዳው አስተዳደር በቀበሌዋ የተከሰተው ድርቅ መፍትሄ ካልተበጀለት አስከፊ እልቂት ያስከትላል በማለት በመግለጫ አስጠንቀቀዋል።
በቀበሌው እስከ ሀምሌ 23/2017 ዓ.ም ዝናብ ስላልዘነበ ገበሬዎቹ የነበራቸው የምግብ እህልና የእንስሳት ቀለብ ተሟጦ አልቋል። በዚሁ ምክንያት 184 ከብቶች፣ 900 አህዮች፣ ከ17 ሺህ በላይ በጎችና ፍየሎች አልቀዋል። 200 ያህል የንብ ቆፎ ጠፍቶባቸዋል።
አቶ ጌታቸው በስልጣን እያሉ የፌደራል መንግስት 13 ቢሊዮን ብር ለክልሉ መስጠቱን ያወጉት ጻድቃን፣አቶ ጌታቸው 9 ቢሊዮን ብሩን ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ለሚመሯቸው ተቋማት ማስተላለፋቸውን መስክረዋል። ይህ ከፍተኛ ገንዘብ ለታጣቂዎች መዋሉንና፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ለማወክ ተግባር መዋሉን በሃዘኔታ ገልጸዋል።


