Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News2  ጀርመን ለጋዛ ጦርነት የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችን ማቅረብ ለማቆም ወሰነች
News2

ጀርመን ለጋዛ ጦርነት የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችን ማቅረብ ለማቆም ወሰነች

Ethioreview newsEthioreview news—August 12, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጀርመን ለጋዛ ጦርነት የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችን ለእስራኤል ማቅረብ እንደምታቆም ማሳወቋ ሰሞኑን ትኩረት ከሳቡት ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። የጀርመን መንግሥት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የእስራኤል የፀጥታ ካቢኔ ጋዛ ሲቲን ለመቆጣጠር ያለመ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ ባለፈው ሳምንት ከተስማማ በኋላ ነው። እሥራኤል የጀርመንን ውሳኔ ተቃውማለች

በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ የሚመራው  የእስራኤል የፀጥታ ካቢኔ ባለፈው ዓርብ የጋዛ ከተማን በኃይል ለመቆጣጠር ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ነበር የጀርመን መንግሥት ወዲያውኑ መልስ የሰጠው። የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ ለጋዛ ጦርነት የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችን ሀገራቸው ለእስራኤል ማቅረብ እንደምታቆም ጊዜ ሳያጠፉ ነበር ውሳኔያቸውን በዕለቱ በጽሑፍ ለእስራኤል ያስተላለፉት ። የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ በጀርመንኛ ምህጻሩ የCDU መሪም ሜርስ በዚሁ መልዕክታቸው «የጀርመን መንግሥት ጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎች የሚደርስባቸው ስቃይ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጸው፣ አሁን  የታቀደው ጥቃት ደግሞ ለሚያደርሰው ተጨማሪ መከራ የእሥራኤል መንግሥት እስከዛሬ ከወሰደው ሃላፊነት የበለጠ ተጠያቂነት ሊቀበል ይገባል ፤ በዚህም ምክንንያት ተለዋጭ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የፌደራሉ መንግሥት ጋዛ ውስጥ ለሚደረገው ግጭት የሚውል የጦር መሣሪያ ወደ እሥራኤል እንዲላክ አይፈቅድም።» ብለዋል።    
ሜርስ ስለ መንግሥታቸው እርምጃ ARD ለተባለው የጀርመን የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስም መንግሥታቸው ለእስራኤል በተለይም ጋዛ ውስጥ የምትጠቀምባቸውን የጦር መሣሪያዎች ማቅረብ አቆማለሁ ያለበትን ምክንያት አስረድተዋል።  «የእስራኤል ካቢኔ በጋዛ ሰርጥ የሚካሄደውን ወታደራዊ ግጭት እንደገና የሚያባብስ እኛን ያስገረመን ውሳኔ አሳልፏል። ከኛ በኩል ደግሞ በእነዚህ ግጭቶች ጥቅም ላይ የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችን አቅርቦት የማቆም የአጸፋ እርምጃ ተወስዷል።»

ታዲያ በዚህ እርምጃ  ጀርመን እሥራኤልን  ወደ ጎን አያደረገቻት ነው? እያንዳንዱ የጀርመን መንግሥት ለእስራኤል ህልውናና ደኅንነት የሚሰጠው ልዩ ድጋፍ እና ጥብቅ ቁርጠኝትስ? በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚዎች ቁጥራቸዉ 6 ሚሊዮን  የተገመተ የሁዲዎችን ከጨፈጨፋ በኋላ ጀርመን ታሪካዊ ሃላፊነት ወድቆባታል። ይህስ? የሚሉ በርካታ ትችቶች በሳምንቱ መጨረሻ ከቀረቡ በኋላ ሜርስ ለARD በሰጡት ቃለ ምልልስ በዚህ የጀርመን እርምጃ ጀርመን ሥለ እስራኤል የምትከተለዉ ፖሊሲ መርሆዎች አይለወጡም ብለዋል።

« ሀገሪቱ ራስዋን እንድትከላለከል መርዳታችንን እንቀጥላለን። ድጋፋችንን አጠናክረናል። ሆኖም ግጭቱን ሙሉ በሙሉ  በጦር ኃይል ለመፍታት ለሚወሰደው እርምጃ የጦር መሣሪያ ልናቀርብ አንችልም። ምክንያቱም ይህ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊጎዳ ስለሚችል ፣የመላ ጋዛን ከተማ ሕዝብ ከአካባቢው ማባረርን የሚጠይቅም በመሆኑ። ሰዎቹ ወዴት ነው የሚሄዱት? ይህን ማድረግ አንችልም፤ አናደርገውም እኔም ብሆን አላደርገውም።»

More stories

ጓደኛቸውን ገድለው  ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው የተሰወሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

May 21, 2024

የብሪክስ ፕላስ የመረጃና እና የባህል ሚዲያ ማዕከል ተመሰረተ

October 15, 2024

” የሎንግ ኦነግ ሸኔን መክዳት ከዜና በላይ ነው” – የሸኔ የሎጂስቲክ መረጃ መንግስት እጅ ገባ

February 18, 2024

“የቴህራን የአየር ክልል በኛ ቁጥጥር ስር ሆኗል” እስራኤል

June 16, 2025

ሜርስ፣ ጀርመን የእስራኤል ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች። ነገር ግን ወዳጅነት አሁን የደረሰውን ዓይነት አለመስማማትንም መቋቋም የሚችል መሆን አለበት ሲሉም ገልጸዋል። ሜርስ ይህን ቢሉም የጀርመን ውሳኔ የእሥራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁን ቅር አሰኝቷል። ነታንያሁ ጀርመን የወሰደችው እርምጃ ለሀማስ የልብ ልብ የሚሰጥ ነው ሲሉ ነቅፈዋል። ሜርስ በበኩላቸው ጀርመን፣ እሥራኤል የምታሳልፈውን ውሳኔ ሁሉ ትቀበላለች ማለት እንዳይደለ ነው ያስረዱት። 

« ከእስራኤል ጋር መተባበር፣ ማለት ፣ መንግሥት የሚያሳልፈውን እያንዳንዱን ውሳኔ እናጸድቃለን፣ የጦር መሣሪያ ወታደራዊ ድጋፍን ጭምር እንሰጣለን ማለት አይደለም። ይህን አናደርግም ፤ይህን ማድረግም አንፈልግም። ይህ የሁል ጊዜ አቋማችን ነው።» ይህ የጀርመን መንግሥት ውሳኔ እሥራኤልን በተመለከተ ጀርመን ከምትወስዳቸው አቋሞች ጠንካራ መሆኑ ትኩረት ስቧል። ስለውሳኔው አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና የሕግ ባለሞያ ዶክተር ለማ ይፍራ ሸዋም ከነበረው ባህል የተለየ ሲሉ ነው የጀርመንን እርምጃ የገለጹት ። እርሳቸው እንዳሉት ከውሳኔው በፊት ጀርመን የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ስታደርግ ቆይታለች።

ጀርመንና እስራኤል የረዥም ጊዜ ዝግጅት አድርገው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ከ20 ዓመታት በኋላ ነው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረቱት። ዘንድሮ  ግንኙነታቸው 60ኛ ዓመት ታስቧል። በናዚ ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት  ቁጥራቸው 6 ሚሊዮን እንደሚጠጋ የተነገረ አይሁዶች መጨፍጨፋቸው ፣ በጦርነቱ የተፈጸመው ግፍ ጠባሳ በቀላሉ እንዳይሽር ማድረጉ አልቀረም። ታዲያ ባለፈው ዓረብ የጀርመን መንግሥት፣ በጋዛ ጥቃት የሚፈጸምበት የጦር መሣሪያ እሥራኤል እንዳይገባ ቢያግድም ጀርመን በእሥራኤል ላይ የምትከተለው ፖሊሲ አይለወጥም ሲሉ መራኄ መንግሥት ሜርስ ተናግረዋል። ሆኖም የጀርመን እርምጃ የሁለቱን ሃገራት 60 ዓመት የዘለቀ ግንኙነት ላይ ተጽእኖ አያሳድር ይሆን ጀርመን የተማሩትና ለሚሰሩት የፖለቲካ ሳይንስና የሕግ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ እርምጃው በሁለቱ መንግሥታት ግንኙነት ላይ የሚያመጣው ችግር አይኖርም ብለዋል።


 የCDU እህት ፓርቲ CSU የሜርስን ውሳኔ ተችቷል። የፓርቲው የውጭ ፖሊሲ ጠቢብ ሽቴፋን ማየር ታገስ ሽፒግል ለተባለው ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ጋዛ ሰርጥ ውስጥ ሁለት ሚሊዮን እንደሚጠጋ የተገመተውን ሕዝብ ስቃይ እንደሚያዩ ጥያቄው የጦር መሣሪያ አቅርቦትን በከፊል ማቆሙ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ፣ አይደለም የሚለው መሆኑን ጠቅሰው ሌሎች ባልደረቦቻቸውም የተለየ አመለካከከት እንዳላቸው ተናግረዋል። ማየር ከእስራኤል ወደ ጀርመን የሚገባ የጦር መሣሪያ ሊቀንስ መቻሉን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፣ጀርመን ከእስራኤል በሚገቡ የጦር መሣሪያዎች ላይ በከፍተኛ ደረጃ የምትተማመን መሆኑን ገልጸው ይህም በርሳቸው እምነት አደገኛ እንደሚሆን አሳስበዋል። በርሳቸው አስተያየት ጀርመን የሳይበር ጥቃት መከላከያ፣ የድሮኖች መከላከያ ፣የመከላከያ ጋሻ እና የስለላ ትብብር ያስፈልጋታል። በርሳቸው እምነት ጀርመን በእስራኤል ላይ የጣለችው ከፊል የጦር መሣሪያ አቅርቦት እገዳ በጣም ውጤታማ የሚባልም ሆነ አስፈላጊ እርምጃ አይደለም።

DW amharic


home
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“የትግራይ ኃይሎች የጨበጣ ውጊያ አድርገዋል” ጄነራሉ
አሌክሳንደር ኢሳክና የዝውውር ውዝግቦች…
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2