Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የኦሮሞ ብሄርተኞች አዲስ የብሄረሰቦች “ጥምዶ” በትዕዛዝ መሰረቱ፤ ሕዝቅዔል በጠርናፊነት ተሹመዋል
News

የኦሮሞ ብሄርተኞች አዲስ የብሄረሰቦች “ጥምዶ” በትዕዛዝ መሰረቱ፤ ሕዝቅዔል በጠርናፊነት ተሹመዋል

Ethioreview newsEthioreview news—August 20, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ኦሮሚያ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንደሌላቸው የሚታወቁት “የኦሮሞ ልሂቃን” በቅርቡ ሲያትል ተሰብስበው ህብረት መፍተራቸውን በአቋም መግለጫ ቢያስታውቁም፣ አካሄዱ እንደተባለው አለመሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ እየገለጹ ነው። አዲስ የብሔር ብሔርሰቦች “ጥምዶ” እንዲመሰርቱ መታዘዛቸውም ተሰምቷል።

የኢትዮሪቪው የዋሽንግቶን ተባባሪ ያሰባሰበውን መረጃ ጠቅሶ እንዳለው በተቃዋሚነት የሚታወቁት የኦሮሞ ተወላጆች አዲስ የብሔር ብሔረሰቦች ቅንጅት እንዲፈጥሩ የታዘዙት በሻዕቢያ ነው። ይህንን እንዲያስፈጽሙ በዋናነት ኃላፊነቱን የወሰዱት ” ጠርናፊ” ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ ናቸው።

” አሁን በስልጣን ላይ ያለውም መንግስትም ሆነ በአማራዎች በኩል የተጀመረው ህብረት የፌደራል ስርዓቱን የሚያከስሙ ናቸው። እኛ የብሄር ብሄርሰቦችን ነጻነት አክብረን በምንፈጥረው ቅንጅት ውስጥ ልትገቡ ይገባል” በሚል በስልክ የተነገራቸው እንዳሉት፣ ይህ ስብስብ በሳምንት ዕድሜ ውስጥ የዙም ስብሰባ ያደርጋል።

የትግራይ ሕዝብ ጦርነት እንደማይፈልግ፣ ከሻዕቢያ ጋር የተደረገውን አዲስ ቅንጅት እንደሚታወቅ ባማስታወቁ፣ የትግራይ ታጣቂ ኃይሎችም በዚሁ ሳቢያ ተከፋፍለው ለሻዕቢያ ስጋት ስለሆኑበት ነው አዲሱ የኦሮሞ ተወላጆ የሚመሩት ጥምረት እንዲቋቋም የተወሰነው።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

በስልክና በአካል የደቡብና የምስራቅ ኢትዮጵያን ይወክላሉ የሚሉዋቸውን የዲያስፖራ አባላት በማግባባት ላይ ያሉት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ፣ በስልክ ላገኙዋቸው “ከሃረሪ፣ ሶማሊያ፣ አፋርና ደቡብ ክልል የተለያዩ ወኪሎችን ስለምንፈልግ ጠቁሙን፣ ወይም ጋብዙልን” ማለታቸውን ጥሪው የደረሳቸው ምስክረነት ሰጥተዋል።

የትግራይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፣ የኤርትራ ተቃዋሚዎች በአሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ጋር በመሆን የስቴት ዲፓርትመንት ሰዎችን ማግኘታቸውና መምከራቸው በሻዕቢያ ዘንድ እንዲሁም ከሻዕቢያ ጋር የሚሰሩት እነ አቶ ነዓምን ያሉበት ሕብረት ሃዘን ፈጥሯል። እነዚህ አካላት በተደጋጋሚ አሜሪካ እንድታግዛቸው ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበር ከራሳቸው ሳይቀር ምስክርነት ሲሰጥበት የቆየ ጉዳይ ነው።

የኤርትራ የዕድሜ ልክ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ በቅርቡ ስለ ኢትዮጵያ በሁለት ክፍል በሰጡት ዲስኩር ከአሜሪካ ጋር አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ከእሳቸው መግለጫ በሁዋላ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር “ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላኩልን” ባሉት ይፋ ያልሆነ ደብዳቤ፣ አሜሪካ ኤርትራን ልትክስ ቃል መግባቷን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ለዶናልድ ትራምፕ ምርጫ አሸናፊነት “እንኳ ደስ ያለዎ” ሲሉ ለላኩት ደብዳቤ ከዘጠኝ ወር በሁዋላ መልስ ሰጡ ስለተባለለት ደብዳቤ ዋይት ሃውስም ሆነ ራሳቸው ፕሬዚዳንቱ በግል የትሩዝ ገጻቸው የተነፈሱት ነገር የለም።

በወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስትሩን ደብዳቤ ከኤክስ ገጻቸው በመቀባበል የኢትዮጵያ ስም ያላቸው ሚዲያዎችና ታዋቂ ሰዎች ሳይቀሩ “አሜሪካና ኤርትራ ተወዳጁ፣ ብልጽግና አለቀለት” በሚል ተንትነው ነበር፣ ጽሁፍ አጋርተውም እንደነበር አይዘነጋም።

ባለፉት ሳምንታት ከአሜሪካ በይፋ እንደተሰማው የኢትዮጵያ መንግስት ወኪሎችና የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይል አመራሮች በአሜሪካ ተገናኝተው መምከራቸው አይዘነጋም። አቶ ጌታቸው ኝኙነቱን በገሃድ ሲያስታውቁ ዝርዝር ጉዳዮችን ባያነሱም በጋራ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በቀይ ባህር ጉዳይና በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጉዳይ መመከራቸውን የዝግጅት ክፍላችን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።

ከዚህ በሁዋላ ነው ቀደም ሲል ሶማሊያ፣ ቱርክና ኬንያ በመመላለስ በኢትዮጵያ የምስራቁ ክፍል የትጥቅ ተግል ለማድረግ ከሚደራጁት የኦብነግ መሪዎችና “ተባባሪዎቻቸው” ጋር በመገናኘት ተደጋጋሚ ምክክር እንደሚያደርጉ የሚታወቁት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ፣ አዲስ የብሄር ብሔረሰቦች ጥምረት እንዲመሰረት የተያዘውን አቅጣጫ እንዲመሩ ሹመት የተሰጣቸው።

ፊልድ ማርሻ ብርሃኑ ጁላ በቅርቡ ለፓርላማ ሲናገሩ በሶማሌ ለአልሸባብ ሲዋጉ የተገደሉና የተማረኩ ኢትዮጵያዊያን መገኘታቸውን መናገራቸው አይዘነጋም። አክለውም “በዚህ ደረጃ ባንዳ ለመሆን የምንመችበትና የምንስማማበት ፍጥነት ያስገርማል። ግብጽ ብትሄዱ አገሩ ላይ የሚማማል ባንዳ አታገኙም” በማለት ግርምታቸውን አካፍለው ነበር።

በጉዳዩ ላይ የግብጽ እጅ እንዳለበት የሚያውቁ እንዳሉት ጉዳዩን በዜና ሽፋን፣ በመናበብ፣ በክፍያ ሰፊ ሽፋን ለመስጠት ከወዲሁ ደፋ ቀና ማለት የተጀመረ መሆኑን አመልክተዋል።

የስብሰባው ጥሪ በስልክ ከደረሳቸው መካከል አንዱ እንዳሉት የኦሮሞዎቹ ስብስብ በራሱ አንድ አቋም የሌለውና አድሮ የሚፈራርስ እንደሆነ አመልክተዋል። ሲያስረዱም “በሕብረታቸው ውስጥ የትህነግ የቀድሞ ወዳጆች አሉ፣ ኢትዮጵያን ቅኝ ገዢ አድርገው የሚፈርጁና ነጻ ኦሮሚያ የሚሉ አሉ። በየቀኑ የሚገላበጡና አመጽና ሁከት ባለበት ሁሉ የሚቆሰቁሱ አሉበት። እነዚህ ታዲያ እንዴት አድርገው ነው ሁሉን የሚያካትት አዲስ ፌደራሊዝም ሊመሰርቱ የሚችሉት?” በሚል አስበውበት ሌሎች ሳይሳሳቱ ቆም ብለው እንዲያስቡ ቢጠቅም በሚል እሳቤ መረጃውን ማካፈላቸውን ጠቁመዋል።

በአሜሪካ የአሜሪካ ሬዲዮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ንጉሴ አክሊሉ የሚመሩት ቪዝን ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ህብረት፣ የብሄር ማህበሮች፣ ጥምዶዎችና ” እንዲህ ብሎኝ ነበር” በሚል በመናበብ ፕሮፓጋንዳ የሚሰሩ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ አውታርና የዩቲዩብ ገጾች እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኦሮሞ ተወላጅ ምሁራን ያቋቁሙታል የተባለው የብሔር ብሔረሰቦች “ጥምዶ” ስሙ እስካሁን በይፋ አልታወቀም። ስሙ ባይታወቅም በሳምንት ጊዜ ውስጥ የዙም ስብሰባ በማድረግ ወደ መድረክ ብቅ እንደሚል መረጃውን ያካፈሉት አስታወቀዋል።

ይህ “ጥምዶ” ይፋ ሲሆን ከለውጡ በሁዋላ ትህነግ ካቋቋመው “የፌደራል ኃይሎች” እና አቶ ልደቱ ከሚመስሉትና ከትግራይ ኃይሎች ጋር በመሆንካቋቋመው ሕዝብረት ቀጥሎ ሶስተኛው ይሆናል።


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ጸደይ ባንክ 870 ሚሊዮን ብር ከሰረ፤ “በባንኩ ቅርንጫፎች ገንዘብ ሲኖር ዘራፊዎች መረጃ ይደርሳቸዋል”
የወለኔ አርሶ አደሮች ኅብረት ፓርቲ ዕውቅና ተከለከልኩ አለ፤ የሕግ “ጥሰቶች ፈጽሟል”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2