Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ECONOMY  የሊዝ ፋይናንስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሚሰጣቸው ብድሮች አንዱ!
ECONOMY

የሊዝ ፋይናንስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሚሰጣቸው ብድሮች አንዱ!

Ethioreview newsEthioreview news—August 10, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ይህንን የብድር ዓይነት አስመልክቶ ትናንት የለጠፍኩት ማሳሰቢያ ላይ ባንኩ ውስጥ ከሚሠሩ ሠራተኞች ሀሳቤን አብራርቼ እንድገልጽ ተጠይቄያለሁ። በዚህ ጥያቄ መነሻ ሀሳቤን በመጠኑ እንደሚከተለው አብራራለሁ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ #የሊዝ_ፋይናንሲንግ የብድር ዓይነት 20:80 የሚል የብድር ቀመር ይከተላል። ይህም ማለት የሚያስፈልገውን ለካፒታል ዕቃ መግዢያ የሚሆን ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ባንኩ የሚያቀርብ ሲሆን፣ የዚያን የካፒታል ዕቃ 20% የሚሆን ያህል ገንዘብ ለመንቀሳቀሻ ካፒታል (Working Capital) እንዲሆን ባለሀብቱ ያቀርባል ወይም ያስይዛል። ይህ የWorking Capital በባንኩ በኩል በሊዝ ፋይናንሲንግ የተገዛው ማሽን ሲተከል ለጥሬ-ዕቃ መግዢያ የሚለቀቅ ነው።

ነገር ግን በእኔ ምልከታ በዚህች የWorking Capital መጠን አናሳነት ምክንያት ተተክለው ሥራ መጀመር አቅቷቸው የቆሙ ወይም ሥራ ጀምረው ወደፊት መጓዝ ያቃታቸውና የከሰሩ ፋብሪካዎች በርካታ ናቸው። በዚህም ምክንያት ብድራቸውን መክፈል አቅቷቸው ከባንኩ ጋር የሐራጅ ውዝግብ ውስጥ የገቡ ተቋማት እንዳሉ አውቃለሁ።

የዱቄት ፋብሪካ፣ የመኖ ፋብሪካ፣ የወተት ፋብሪካ እና ሌሎችም የፋብሪካ ዓይነቶች በዚህ የWorking Capital ማነስ ችግር ምክንያት ፋብሪካዎቻቸውን ለኪሳራ ባለሀብቶቹንም በእድሜያቸው ያፈሩትን ጥሪት ሊበላ አሳሳቢ አደጋ እንደተጋረጠባቸው አስተውያለሁ። ይህ አካሄድ እርምትና ማስተካከያ ይፈልጋል። ችግሩን ከስሩ አጣርቶ ማረሚያ ማድረግ ያስፈልጋል።

More stories

ትራምፕ በፊሽካ ያስጀመሩት የታሪፍ ጦርነት

February 4, 2025

“የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጁ የውጭ ባንኮች በፋይናንስ ዘርፉ እንዲሠማሩ የወጣውን ፖሊሲ ወደ ተግባር የሚያሸጋግር ነው”

November 13, 2024

“ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞች ደሞዝ 300 እጥፍ ያድጋል”

August 2, 2024

ፓርላማው ለ2018 በጀት ዓመት የ1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት አጸደቀ

July 3, 2025

በሊዝ ፋይናንሲንግ ብድር በማግኘቱ ብቻ ተደስቶ ፋብሪካ ተክሎ ለማምረት ጓጉቶ ነገር ግን ማምረት አቅቶት ባለሀብቱ ሲጨነቅ ማየት ያሳዝናል። የችግሩ ስር ያለው #የWorking_Capital_ማነስ ላይ ነው።

በዚህ ዘመን ማሽን መትከል ብቻውን በቂ አይደለም። እንዴት ፋብሪካውን ተወዳዳሪ አድርጎ እንደሚመራ ካልታወቀ ትርፉ ጭንቀትና ኪሳራ ነው።

በእኔ እይታ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ሀገራችን #ከበቂ_በላይ_ፋብሪካ አላት። ፋብሪካዎቹ ግን በበቂ የማምረት ዓቅማቸው ስለማይሠሩ ከስረው እና ተዘግተው ቆመዋል። ይሄ ለሀገር ትልቅ ብክነት ነው። በዚህ ምክንያት በአንዳንድ የፋብሪካ መስኮች አዲስ ማሽን በውጭ ምንዛሪ ማስገባት አላስፈላጊና የውጭ ምንዛሪ ማባከን ነው። ያሉት መች ተሠራባቸውና?!

ለመሆኑ ለአንድ ፋብሪካ የሚያስፈልገው የWorking Capital መጠን ስንት ነው? የWorking Capital መጠን እንዴት ይተመናል? የሁሉም ፋብሪካ የWorking Capital መጠንስ ከካፒታሉ 20% ነው ወይ?

#Working_Capital የጥሬ-ዕቃ መግዢያን፣ የዱቤ ሽያጭ መጠንን፣ ለአቅራቢዎች የሚከፈል ቅድመ-ክፍያን፣ የደሞዝ ነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ወጪዎችን ታሳቢ በማድረግ የሚሰላ ነው።

ለመሆኑ አንድ ፋብሪካ ምርት ሳያቋርጥ፣ ዋጋው ሳይዋዥቅና ገበያው ሳይረበሽ እንዲሠራ ምን ያህል የጥሬ-ዕቃ በክምችት መያዝ አለበት? ይህ ከኢንዱስትሪ ኢንዱስትሪ የሚለያይና እንደ ድርጅቱ የቢዝነስ ሞዴልና ዓቅም የሚለያይ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንስ ዋና ችግር የWorking Capital መጠንን ለሁሉም ፋብሪካ የካፒታሉን 20% ያህል ነው ብሎ ማሰቡ ነው። ይሄ ትልቅ ስህተት ነው። ይህ ታሳቢ ብዙ ፋብሪካዎችን ለችግር እና ኪሳራ ብሎም ለሐራጅ እየዳረገ ያለ ዋና ችግር ነው።

የWorking Capital ፍላጎት መጠን ከኢንዱስትሪ ኢንዱስትሪ ይለያያል። አንዳንድ ፋብሪካ ከማሽን ወጪ ይልቅ የመሥሪያ ካፒታል ፍላጎቱ ብዙ ነው።

ለምሳሌ :- የመኖ ፋብሪካ ማሽንን ከ20-30 ሚሊየን ብር በሚደርስ ወጪ መትከል ይቻላል። አዋጭ በሆነ መንገድ በቂ ጥሬ-ዕቃ ገዝቶ መኖን አትራፊ በሆነ መንገድ ለማምረት ግን 200 ሚሊየን ብርም አይበቃም። ካስፈለገ ዝርዝሩን ቀርቤ አስረዳለሁ።

ለዱቄት ፋብሪካም ተመሳሳይ ነው። የግብርና ግብዓት ለሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች በቂ ጥሬ-ዕቃ በመኸር ጊዜ ዋጋው ዝቅ ሲል መያዝና መሥራት ይጠይቃል።

ለፕላስቲክ ኢንዱስትሪም የፔትሮሊየም ዋጋ ውጣ ውረድን ተከትሎ የጥሬ-ዕቃ ክምችት አያያዝን መመጠን አስፈላጊ ነው።

ታድያ ለዚህ በቂ Working Capital ያስፈልጋል።

የብዙዎቹ የሀገራችን ኢንዱስትሪዎች ችግር #የድሃ_አስቤዛ በሚመስል የWorking Capital መጠን ለመሥራት መሞከር ነው። ይህ #አክሳሪ መንገድ ነው።

ለእንደዚህ ዓይነቶቹ ኢንዱስትሪዎች 80% ለWorking Capital 20% ለማሽን እንጂ አሁን ያለው መንገድ አያሠራም።

የባንኩ ሰዎች ይህንን መሰል ችግሮች አቅርቤ እንዳስረዳ ከፈለጉ ቀርቤ ለማስረዳት ፈቃደኛ ነኝ።

(Via:- Get Toughe Zer)


ECONOMY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የጫኝና አውራጅና የሽፍታ እምባገነንነት!
EU calls for ‘transatlantic unity’ ahead of Trump-Putin summit in Alaska
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ECONOMY

ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

March 29, 2026
ECONOMY

“የስምምነቶች ሁሉ እናት” ህንድ እና የአውሮፓ ህብረትታሪካዊ የንግድ ስምምነት አደረጉ

January 27, 2026
ECONOMY

በኢትዮያ ከ21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ በርላይ የጋዝ ክምችት ተገኘ

October 30, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2