Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ሻዕቢያ ለኢትዮጵያ አዲስ የጥምር ፓርቲ ቦርድ ሊያቋቁምላት ነው፤ “ ከጉባዔው በፊት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ተለያዩ” 
News

ሻዕቢያ ለኢትዮጵያ አዲስ የጥምር ፓርቲ ቦርድ ሊያቋቁምላት ነው፤ “ ከጉባዔው በፊት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ተለያዩ” 

Ethioreview newsEthioreview news—September 24, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የተለያዩ አቋምና ዓላማ ያላቸው የተቃዋሚ ድርጅት አባላትና ግለሰቦች ሃያ አንድ አባላት ያሉት ቦርድ እንደሚያቋቁሙ ተስምቷል። በዚሁ ሻዕቢያ እንደሚያደራጀው በተነገረለት ቦርድ ምስረታ “አክራሪዎችና አስመሳይ ለዘብተኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚባባሉት መለያየታቸው ታውቋል። እንደ መረጃው የሲያትሉ የኦሮሞ ልሂቃን ስብስብ ፈርሷል። 

አቶ ልደቱ ይመሩታል የተባለ፣ ነገር ግን ሻዕቢያ የሚያደራጀው ሃያ አንድ አባላት ያሉበት ቦርድ በመጪው ኦክቶበር 9 ቀን 2025 እንደሚቋቋም ተሰምቷል። በቀጣይ ቦርዱ መተዳደሪያ ህግና የፓርቲ ስያሜ እንደሚያወጣ ታውቋል። ይህ ቦርድ “ኢትዮጵያን ጦርነት አልባ” የሚያደርግ የሁሉም ዓይነት ስብስብ ተደርጎ በሻዕቢያ ስፖንሰርነት በሚነቀሳቀሱ የሚታወቁ ሚዲያዎች ቅስቀሳ እንዲሰራለት ቅድም ዝግጅት መጠናቀቁም ታውቋል። 

ቦርዱ ውስጥ ከሚካተቱት መካከል ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ፣ ጃዋር መሐመድ፣ ልደቱ አያሌው፣ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶ/ር ሚልኬሳ፣ ኢንጂነር ይልቃል፣ አቶ ነዓምን / ሻዕቢያን በቀጥታ በመወከል፣ አቶ ኦባንግና የመሳሰሉት ይገኙበታል። ስብስቡ ከቀደመው የኢህአዴግ አደረጃጀት ጋር የሚመሳሰል ሲሆን የትህነግ የውጭ ክንፍ መሪ የሆኑት የእነ አቶ ስብሃት ቡድንም ተካቶበታል። ትህነግና ሻዕቢያ አብረው እየሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ቦርዱ የሚቋቋምበት ወቅት ሲደርስ እንደተሰማው ከሆነ በሲያትሉ የኦሮሞ ልሂቃን ስብሰባ ላይ ከተገኙት መካከል ከፊሎቹ ራሳቸውን አግልለዋል። ምክንያታቸውም ከሻዕቢያ፣ ትህነግና የፋኖ ተወካዮች ጋር አብሮ መቀመጥ ክህደት መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያን እንደ ቅጭ ገዢ በሜመከተው አጀንዳቸው ሳቢያ ነው።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

የቦርድ ምስረታውን አስመልክቶ ለኢትዮሪቪው ያስታወቁ አንዳሉት ራሳቸውን ለዘብተኛ ያስመሰሉት እነ ጃዋር ለስም የሰላማዊ ትግል አራማጆች መሆናቸውን እየተናገሩ የፋኖን ኃይሎች ከሚደግፉና ከሚመሩ አካላት ጋር የፈጠሩት ሕብረት በዋናነት ሻዕቢያ የሚመራው እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው ገልጸዋል። ሻዕቢያ አንድ ሆኖ አስመራ የገባውን ኦነግን አራት ቦታ ከፋፍሎ፣ አባላቱ በባርነት ይዞ፣ ድርጅቱን የመደራደሪያ ቁስ አድሮ ዛሬ ለደረሰበት ውድቀት በማብቃቱ የሚከሱት እነዚህ ወገኖች ሻዕቢያ ለኦሮሞ ሕዝብ የሚበጅ በጎ አጀንዳ አለው ብለው አያምኑም። በቅርቡም የማህበረሰብ መጠሪያ የሆነውን ኦሮሙማ የመታገያ ርዕዮት በማስመሰል ኦሮሞነትን ዒላማ ውስጥ የሚያስገባ መርዛማ አጀንዳ ለመትከል በመሞከሩ አብረውት ሊሰሩት አይወዱም። 

የ”ኦሮሙማ እሳቤ አባት” የሚባሉትና ኢትዮጵያን በቅኝ ገዢነት የሚፈርጁት ፕሮፌሰር አሰፋ ኢጀታ፣ አቶ ልደቱ አያሌውን “ ያረጠ ፖለቲከኛ” በሚል የዘለፉትፉት ዶክተር ጸጋዬ አራርሳ፣ የታንዛንያው ተደራዳሪ ጠሃና ፕሮፌሰር መሐመድ በዚህ ሳቢያ ሻዕቢያ ካዘጋጀው አዲስ ሕዝብረት መውጣታቸው ታውቋል። በዚሁ መነሻ የሲያትሉ ተቀናጆች ተበትነዋል።

“የኦሮሞ ምሁራን የፓለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ስምምነትና ውሳኔዎች ሲያትል” በሚል ርዕስ ሐምሌ 31 ቀን 2025 በተሰራጨ መግለጫ፣ “ አሁን በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የኦሮሞን ህዝብ ከዚህ በፊት ታይቶ ለማይታወቅ ሰቆቃ እና ጭቆና እንዳጋለጠው ተገንዝበን ይህ አገዛዝ መወገድ እንዳለበት ተስማምተናል። ይህ ቡድን ፀረ ኦሮሞ ተግባራትንና ፖሊሲዎችን እየፈፀመ  በዚህ ብሄር ውስጥ ለመደበቅ የሚያደርገውን ሙከራ አጥብቀን እናወግዛለን” ሲል የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፉወርቂ የኢትዮጵያ መንግስትን “የኦሮሞን ህዝብ የማይወክል የኦሮሙማ ርዕዮተ ዓለም የሚከተለ” በማለት የሰጡትን የከፋፋይነት አጀንዳ መድገሙ የሚታወስ ነው።

ይህ ስብስብ “  የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶችን (ኦነግ-ኦነሠ: ኦፌኮ እና ኦነግ) በተደራጀ መንገድ አስፈላጊውን ለውጥ በማምጣት መጪውን ሽግግር ስኬታማ ለማድረግ በሚየደርጉት እንቅስቃሴዎች በሁሉም ዘርፍ ለመተባበር ተስማምተናል” ቢልም ኦነግ በገሃድ “አላውቃችሁም በስሜ አትነግዱ” በሚል ተቃውሞ ማሰማቱ የሚታወስ ነው።

የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመነበርነቱ ስለመነሳቱ ድርጅቱም ሆነ ራሱ ጃዋር በይፋ ሳያስታውቅ በዚህ አዲስ ፓርቲ ውስጥ ማንን ወከሎ በኦሮሞ ስም እንደሚሳተፍ በራሱ ጥያቄ እንደሚሆን የሚያነሱ፣ ኦፌኮ እንደ ኦነግ ግልጽ አቋም ሊይዝ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸው አይዘነጋም። በፓርቲው አመራሮች ውስጥም ይህ ጉዳይ ልዩነት መፍጠሩና በርካታ አመራሮች ፓርቲውን ለቀው እስከመውታት መድረሳቸውን ገልጸን መዘገባችን አይዘነጋም።

የኢትዮሪቪው የዋሽንግቶን ተባባሪ በወቅቱ ያሰባሰበውን መረጃ ጠቅሶ እንዳለው በተቃዋሚነት የሚታወቁት የኦሮሞ ተወላጆች አዲስ የብሔር ብሔረሰቦች ቅንጅት እንዲፈጥሩ የታዘዙት በሻዕቢያ ነው። ይህንን እንዲያስፈጽሙ በዋናነት ከሻዕቢያ ኃላፊነቱን የወሰዱት “ጠርናፊ” ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ ሲሆኑ አቶ ነዓምን በቋሚነት የሻዕቢያ ተወካይ ሆነ በሁሉም አግባብ መመሪያ የሚያስፈጽሙ መሆናቸው በተለያዩ አግባቦች የሚገልጽ ነው። ሕዝቄል ገቢሳ በሶማሌ ያለውን የሻዕቢያ ተልዕኮ የሚያስፈጽሙና ለዚህ ስራ በተደጋጋሚ ኬንያ፣ ቱርክና ሶማሊያ፣ ሶማሊ ላንድ መጓዛቸውን መረጃዎች ይመስክራሉ። በተመሳሳይ ከትህነግ ጋር በቋሚነት የሚሰሩና የሚታገሉ ታማኝ መሆናቸውን የትህነግ ደጋፊዎች ሳይቀሩ የሚመሰክሩላቸው ናቸው። 

በኦክቶበር 9 ይቋቋማል የተባለው ሃያ አንድ አባላት ያሉት ቦርድ በህግ የሚመዘገብና የፓርቲ መጠሪያ ስም እንደሚበጅለት በምስረታው ላይ የተጋበዙ ለኢትዮሪቪው አስታውቀዋል። ግብዣውን ያልተቀበሉም አሉ። ግብዣውን ያልተቀበሉት ሁሉም መመሪያና ዕቅድ የሚወጣው ከሻዕቢያ ስለመሆኑ መረጃ ስላላቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።

እነ ጃዋር “ከማንም ጋር ይሁን አብይን ለመጣል እንሰራለን” በሚል ራሳቸውን ለዘብተኛ የኦሮሞ ታጋይ አስመስለው ቢያቀርቡም፣ መነሻቸው፣ ሲነሱ ሲፈጽሙ ከነበረው፣ እንዲሁም አዲስ አበባ በገነበሩበት ወቅት ያስመዘገቡት የከፋ ሪኮርድ የቅርብ ጊዜ ትዝታ በመሆኑ፣ ሌሎችን “አክራሪ” የማለት ሞራል እንደሌላቸው በመርህ የተለዩት ክፍሎች ይናገራሉ።

አቶ በቀለ ገርባ፣ ፕሮፌሰር መረራ፣ አቶ ጁሃርና ባልደረቦቻቸው በተሰየሙበት ስብሰባ ህዝብ እያየ፣ “አማራ አታግቡ፣ አማራን አትወዳጁ፣ ያገባችሁ ፍቱ” እየተባለ ትምህርት ሲሰጥ እነሱ እንዳልነበሩ የሚናገሩት እነዚህ ወገኖች፣ “ በአማርኛ አትገበያዩ” በማለት በግልጽ የተናገሩ የፖለቲካ አመራሮች “የጠላትህ ተላት ወዳጄ ነው በሚል ዛሬ ለዘብተኛ ነን ቢሉ ማን ያምናቸዋል?” በማለት ይጠይቃሉ። በርካታ ዘርን መሰረት ያደረጉ ጥፋቶችን፣ ውድመቶችን፣ ግድያዎችን፣ መፈልናቀሎችን የሚያነሱ ጃዋርን “አልጸጸትም” በሚልው መጽሐፉ ክፉኛ መዝለፋቸው አይዘነጋም። 

ዶክተር ኢታና ዛሬ ተመልሰው ከጃዋር ጋር ቢሰለፉም፣ “ጃዋር እንዲሁ አልተፈታም። በይቅርታ ሲፈታ ምን አደርጋለሁ ብሎ ነው የተፈታው” በሚል እሱን ማመን ጉም የመዝገን ያህል እንደሆነ በተናገሩበት ቃለ ምልልሳቸው ላይ “ ጃዋር የሚወራጨው የተያዘበት በሚሊዮን የሚቆጠር ብር እንዲለቀቅለት ነው” ብለው እንደሚያምኑ መናገራቸውን የሚያነሱ፣ አሁን ላይ ጃዋር ይህን ለማሳካት “ ለዘብተኛ” የሚለውን ካባ መልበሱን ያስታውቃሉ።

ጃዋር ቅማንት፣ አገው፣ ቤኒሻንጉል ወዘተ ለሚባሉ የነጻ አውጪ እያደራጃጀቶችን ባሉት ሚዲያዎቹ ሁሉ የአየር ሰዓት ሰጥቶ እየቀሰቀሰ ክልሉን ሊያፈርሰው ሲሰራበት እንደነበር የሚያስታውሱም፣ ዛሬ ለአማራ ክልልና ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ መስሎ በመቅረቡን አይቀበሉም። 

ከትህነግ በላይ ትህነግ የሚባለው አቶ ልደቱም ቀደም ባሉት ጊዜያት ሻዕቢያን በመዝለፍና በመቃወም የሚታወቁ ቢሆንም፣ ሻዕቢያና ትህነግ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ተከትሎ በውስጥ ይቅርታ ጠይቆ ከነ አቶ ነዓምን፣ አንዳርጋቸውና ፕሮፌሰር መሐመድ ጋር አብሮ እንደሚሰራ ጠንቀቀው እንደሚያውቁ የሚያስታውቁት ስብሰባውን ያተቀበሉ ክፍሎች፣ “ይህ ቦርድ ልክ እንደሌሎቹ ተቋቁመው እንደሚፈርሱት ወይም እንደሚረሱት ዓይነት አደረጃጀቶች ከመሆን አያልፍም” ብለዋል።

“ ቅድሚያ ኦሮሞ Oromo first” መፈክሩና በሜንጫ ፖለቲካ ወደ የዲያስፖራውን ትግል የተቀላቀለው ጃዋር መሐመድ ለዘብተኛ የተባሉትንና እየመራ በቦርዱ ውስጥ ቢሳተፍም አመራሩን ስለመያዙ የታወቀ ነገር የለም።  “ሞሃ ተዋህዶ” የሚባለው የፋኖ አደረጃጀትም ሆነ የአማራ ትግል አመራሮች “ ቤታችን አራት ኪሎ ነው፤ አራት ኪሎ መዳረሻችን ነው” በማለት ስልጣን አማራ እጅ ብቻ መውደቅ እንዳለበት በይፋ ስለሚያስታውቁ አቶ ጃዋር የመሪነት ስፍራውን እንደምያዙ ከወዱሁ ግምት አለ። ሻዕቢያም ያለውን መነግስት በትኖ አገሪቱን ማፍረስ ቁልፍ አጀንዳው በመሆኑ ይህን እያወቀ ወደ ጥምረት እንዳመታቸው እነዚሁ ወገኖች ተናግረዋል።

በቅርቡ የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፉወርቂ “የምናደርገውን እናውቃለን” በማለት መናገራቸውን የሚጠቅሱ “ተላላኪዎች እስከተገኙ ድረስ ኢሳያስ ኢትዮጵያን እያወኩ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል”


NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ዩኤስ አይዲ በመዘጋቱ በድብቅ እየከፈሉ መረጃ የሚያገኙ ሚዲያዎች ወሬ እያጡ ነው
ደቡብ አፍሪካ በቅኝ ገዥዎች የተወሰዱባት የሰው ቅሪተ አካላት እንዲመለሱላት ጠየቀች
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2