ያኔ ከራስህ ወዠንባራ ፖለቲካ እና ጨካኝ ቅዠት ውጪ ማንን ልትወቅስ ነው? ማንንስ ብትወቅስ ማን ይሰማሃል?! ማንም! እናም ከጨካኙ ቅዠትህ ንቃ! ያንተ የፖለቲካ ቅዠት አላፈናፍን ያለውን ህዝብ አሁን ካለበት የከፋ ቀጥተኛ ጉዳት፤ ከሚጠብቀው የጠለቀ እና የሰፋ multiplier effect ታደገው።
ስማኝማ በOluma’s Views ነጻ አስተያየት
ወይን፣ ሸንን፣ ፋንን ግን በቅዠት አለም በተፀነሰ አስተሳሰብ፣ በተወዠናበረ የፖለቲካ ግብ እና በከሸፈ “የትግል አማራጭ” እየተጋለብክ፦
- ለሞት እና ለአካል ጉዳት የዳረግኸው የሰው ሃይል፣
- ያፈራረስከው የአካባቢህ መንግስታዊ መዋቅር፣
- ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን ያ(ስ)ደረግሃቸው የትምህርት፣ የጤና እና የሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ተቋማት፣
- ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዲሆኑ የፈረድክባቸው ወደ 10 ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎች፣
- ያደነቃቀፍካቸው የንግድ/ኢኮኖሚ ልውውጦች እና የአካባቢ ልማት ፕሮጀክቶች፣
- የለመድካቸው እና ለህብረተሰቡ ያለማመድካቸው የጭካኔ፣ ህገ-ወጥ እና ጋጠ-ወጥ ድርጊቶች…ወዘተ
ዛሬ ላይ በህዝቡ ላይ ያስከተሉት ውጥንቅጥ ቀጥተኛ (direct) እና እጅግ ከባድ (severe) ጉዳት ግልፅ ነው። ነገር ግን ይሄ ገና የውጥንቅጡ ጅማሬ (tip of the iceberg) መሆኑ አልተገለፅህም። ክልሉ፣ ዞኑ፣ ወረዳው፣ ቀበሌው፣ ከተማው እና ገጠሩ ከደቀቀ በኋላ፤ ድንገት ወድደህም ይሁን ተገድደህ ከአውዳሚው ቅዠትህ ስትነቃ የእጅህ ፍሬ አፍርቶ እና እጅጉን ጎምርቶ (the multiplier effect) ይጠብቅሃል፦
- ሰብአዊ ጉዳዮችን ወደ ጎን ብትተው እንኳን፤ ለሞት እና ለአካል ጉዳት የዳረግኸውን የሰው ሃይል በቀላሉ አትተካውም። ይህን ኪሳራ ለመተካት የሚያስከፍለው ዋጋ ባክኖ ከቀረው ትሩፋት ጋር ሲደማመር ኪሳራው ለትውልድ የሚተላለፍ ሆኖ haunt ያደርግሃል፣
- የመንግስትን መዋቅር በቦታው አታገኘውም። እሱን ወደሚገባው ቦታ ይቅርና፤ ወደ አስፈላጊው ደረጃ በመሰረታዊ መልኩ እንኳን ለመመለስ አመታት ትጠብቃለህ፣
- የትምህርት፣ ጤና እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን መልሰህ ለማግኘት ከወደፊቱ ትውልድ ድርሻ ላይ እየተበደርክ ትገነባለህ፤ ካለህበት ዘመን ደግሞ በንፅፅር ወደኋላ የቀረ ህዝብ ታቅፈህ ትቀራለህ፣
- ከትምህርት ገበታ ያፈናቀልካቸው በርካታ ሚሊየን ዜጎች ከእኩዮቻቸው በትምህርት ደረጃ ብቻ ሳይሆን፤ በሀገራቸው እና በመላው አለም ከሚገኙት ትሩፋት (opportunities) ተገልለው ሲቆዝሙ እና dystopian ህይወት ሲመሩ ታገኛቸዋለህ፣
- የአካባቢህ የንግድ/ኢኮኖሚ ልውውጦች እና የልማት ፕሮጀክቶች ባንተ ወዠንባራ ፖለቲካ ምክንያት የወደፊቱን በመገንባት ፋንታ፤ የፈራረሰውን መልሰው ሲገነቡ ከሌሎች አንፃር እኩል መሆን አይደለም በሌሎች ፍጥነት መራመድ ተስኗቸው በመውደቅ እና በመቆም መሐል ሲንገዳገዱ ከመመልከት ውጪ ምርጫ አይኖርህም፣
- ከሁሉም በላይ በአመዛኙ ፈሪሃ-ፈጣሪ እና ህግ/ወግ አክባሪ የነበረው ህብረተሰብ፤ ጨካኝ (predatory) ሆኖ እና የጭካኔ ድርጊቶችን ተላምዶ ይጠብቅሃል።
ያኔ ከራስህ ወዠንባራ ፖለቲካ እና ጨካኝ ቅዠት ውጪ ማንን ልትወቅስ ነው? ማንንስ ብትወቅስ ማን ይሰማሃል?! ማንም! እናም ከጨካኙ ቅዠትህ ንቃ! ያንተ የፖለቲካ ቅዠት አላፈናፍን ያለውን ህዝብ አሁን ካለበት የከፋ ቀጥተኛ ጉዳት፤ ከሚጠብቀው የጠለቀ እና የሰፋ multiplier effect ታደገው።
በእውነት “ትግልህ” ለህዝብ ከሆነ፤ የቅዠትህ እስረኛ እና seige ያደረግኸውን ህዝብ ፍታው። ነፃነቱን ስጠው!
via – Oluma’s Views

